tgoop.com/Islam_and_Science/6158
Last Update:
ይቀጥልበታል፡፡ ይህም እውነታ የዝሙትን ድርጊት እጅግ አደገኛና የማይወጡት የወንጀል አዙሪት ያደርገዋል፡፡ ለዚህም ነው «ዝሙትን አትቅረቡት» የሚባለው፡፡
🌙🌙 ታላቁ ሊቅ ኢማም ኢብኑል ቀይም እንዲህ ብለዋል፡- ስሜትን ከዚና መቆጣጠር ምንዳው ጀነት ነዉ
ዩሱፍ (ዐ.ሰ) መጀመሪያ ባሪያ ነበር፡፡ የዓለም ግማሽ ቁንጅና እንደፈሰሰበት ይነገርለታል፡፡ እርሱን በባለቤትነት የያዘችው የባለሥልጣኑ ሚስትም በፍቅሩ ናወዘች፡፡ ለዝሙትም ገፋፋችው፡፡ እርሷ ውበትና ሥልጣን ያላት ሴት ናት፡፡ እርሱ ግን እምቢ አለ፡፡ ስሜቱንም ተቆጣጠረ፡፡ ከዚያም ተዶልቶበት ወደ ዘብጥያ ተላከ። ነገር ግን የኋላ ኋላ የግብጽ ገዥ (ዐዚዝ) ሆነ፡፡ ስሜቱን የሚቆጣጠር ሰው ምንዳ ይሉሀል ይሄ ነው::
♦ አላህ ሱወ በተከበረ ቁርአኑ ላይ በሱረቱል ናዚዓት ላይ እንዲህ ብሏል
በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ፤ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ (አን-ናዝዓት፡40-41)
╔══════════════════════╗
95%በላይ ሴቶች ይህን የሀቢቡና ሙሀመድﷺሀዲስ በተደጋጋሚ ሰምተዉታል ╚═══════════════════════
ማንኛዉም ሽቶን ተቀብታ በሰዎች ፊት የምታልፍና ከማዕዛዋ የምታደርግ ሴት እርሷ ዛኒያ(ዝሙተኛ)ናት፡፡
ግን ሽቶ ሳይቀቡ አይንቀሳቀሱም..ሴቶች ሆይ ማወቅ ያለባችሁ ግዴታ ሽቶ ብቻ ሳይሆን የምትቀቡት ፌር ጥፍር ቀለም ሊፒስቲክ ቻፕስቲክ ሽታ ስላለዉ ሽቶ ጋር እንደሚካተት ልታቁ ይገባል፡፡
✨✨ዝሙት ስንሰራ አላህ እንደሚያየን ልናቅ ልንገነዘብ ይገባል፡፡አሏህ ሱወ አንዲት ቅጠል የምወድቅበትን ቦታ የሚያቅ ጌታችን ዝሙት ስንሰራ ጀሊሉ ፊት ወንጀል እየሰራን እንደሆነ ልናስተነትን ይገባል፡፡
አላህ (ሱ.ወ) ወንጀልን ለሚሰሩ ባርያዎቹ እንዲህይላል፦
እነርሱ ያንን ቀን ሩቅ አድርገዉ ያያሉ፡እኛም ቅርብ ሆኖ እናየዋዉለን(አል መዐሪጅ 6-7)
ሰአቲቱ እነርሱ የማያዉቁ ሆነዉ በድንገት ልትመጣባቸዉ እንጅ ይጠባበቃሉን(አል ዙህሩፍ 66)
⚠️ አንዲት ሴት ከብረ ንፅህናዋን መጠበቅ እንዳለባት ካላወቀች ለነገ ህልም ከሌላት ድንግልና ለጥብቅ ሴቶች የትዳር ዋስትና መሆኑን ካላወቀች ሀያዕ ከሌላት ህይወቷ በዝሙት ምክንያት ምስቅልቅሉ ይወጣል፡፡ ክብረ ንፅህናዋን ለመጠበቅ ደግሞ ሐያእ (የእፍረት ስሜት) ወሳኝ ባህሪ ነው፡፡ ሴት ልጅ ከሐያእ ከተራቆተች ለክብረ ንፅህናዋ ተገቢውን ከለላ አላደረገችም ማለት ነው፡፡
☞ከኢኽቲላጥ ከተቃራኒ ፆታዎች ልቅ ቅልቅል ካራቀች ለዝሙት መንገድ ከፍታለች ማለት ነው፡፡
☞ዕይታዋን ዝቅ ካላደረገች ለዝሙት መንገድ ከፍታለች ማለት ነው፡፡
☞ምላሷን መቆጣጠር ካልቻለች አሁንም ለዝሙት መዳረሻ መንገድ ከፍታለች ማለት ነው፡፡
☞ከምንም በላይ ሴት ልጅ ጆሮዋን ከዘፈን ካልጠበቀች ለዝሙት የመጋለጥ ዕድሏ ሰፊ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ፆታዊ ፍቅር ወደሴቶች የሚገባው በዋናነት በጆሮ ሲሆን ወደ ወንዶች ደግሞ በዓይን ነው፡፡
♦ለወንዱም ቢሆን ዕይታውን መቆጣጠርና ዓይኖቹን ዝቅ ካላደረገ የዝሙት መዳረሻ መንገድን ተዳፈረ ማለት ነው፡፡
♦ጥብቅነቱን መጠበቅ እንዳለበት፣ አልያም አቅሙ ከቻለ ካልፆመ ከተቃራኒ ጾታዎች ጋር ከተቀላቀለ የዝሙትን መዳረሻ መንገዶች ተዳፈረ ማለት ነው፡፡
♦ከሴት ጋር የርሷ መሕረም አጠገቧ በሌለበት ሁኔታ እሷ ጋር ከሆነ የዝሙት መንገድን ተዳፈረ ማለት ነው፡፡
በጥቅሉ ደግሞ ዝሙት ሐራምና መንገድነቱም የከፋ መሆኑን እያወቀ የሚያጠፋ፣ ትዳር የተቀደሰና የተባረከ ሕይወት መሆኑን፣ ከትዳር በፊት የወንድም ሆነ የሴት ጓደኛን መያዝ ሐራም መሆኑን የሚያዉቅ አዉቆ ጠፍ በዝሙት ላይ የመውደቅ ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ ስለዚህ የዚህ አዉቆ ጠፍ ከዝሙት የመራቁ ጉዳይ ከባድ ነው፡፡
ሰይዲና ሙሀመድ ﷺ ዝሙትን ቀጥታ ከኢማን ጋር አያይዞታል፡፡ እንዲህም ሲሉ ተናግረዋል፡-
«ዝሙተኛው ዝሙትን በሚሠራበት ጊዜ እርሱ ሙእሚን ሆኖ አይደለም (የርሱ ኢማን ከርሱ ጋር የለም)፡፡» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል፡፡
ዝሙት በምንም መልኩ አሁን በርካታ ወጣቶች እንደሚያስቡት የመዝናኛ ዓይነት ሳይሆን ቀጥታ ከኢማን ጋር የተያያዘ ነገር መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን አለማወቅ በወንጀሉ ውስጥ ለመውደቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡
⚠️በኢትዮጵያ ሀገራችን የዝሙት ጉዳይ በጣጣም አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ደርሷል ፡ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች እንዳመለከቱት ከአዳጊዎች መካከል ከ21.5%-24.8% የሚሆኑት በወሲብ ንቁ ናቸው፡፡ እንዲሁም የመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አማካይ ዕድሜ ከ15-16 ዓመት ነበር፡፡ ይህም ችግር ሥር የሰደደ ሲሆን የቅድመ ጋብቻ ወሲብ የማህበራዊ ጤና ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡ አዳጊዎች በለጋነት ዕድሜያቸው ወሲባዊ መነሳሳቶች ውስጥ በሚገቡበት ጊዜ ያልታሰቡ በርካታ ማህበራዊ ችግሮች ይከሰታሉ፡፡ ለምሳሌ
☞ በአዳጊነት ውስጥ የእናትነት ሕይወትን መምራት፣
☞ለነጠላ ወላጅነት መዳረግ፣
☞ ለአባላዘር በሽታዎች መጋለጥ ናቸው፡፡
ግን እንደዚህ ሁነን ወደየት ወደየት እያመራን ነዉ???
🙄እኛ ኢትዮጲያን የነጃሺ ሀገር በአለም ሁለተኛ ሙስሊም የተቀበልን የኢትዮ ግማሽ ፐርንሰንት በላይ ሙስሊም ነን ..ዲነኛ ነን ኪታብ ቀርተናል ..መስጊድ ተነካ..ኢስላም ተደፈረ ..ወዘተ በምላስ እንላለን በጎን ዚና እንሰራለን ዚናን መከላከል አልቻልንም
ክርስቲያኖች ኢትዮ የሙሴ ፅላት አለ ..አርባ አራት ታቦት አለ ..ኢትዮ ገማደ መስቀሉ አለ ይሄን ያህል ገዳም አለን.. ኢትዮ የኛ ናት የክርስቲያን ደሴት ናት ይባላል በጎን ዚና እንሰራለን🤔ዚናን መከላከል አልቻልንም፡፡
ወዴት እያመራን ነው? ያልተፈታ የዘመናችን እንቆቅልሽ ...
#ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ ሸርሙጣ፣ ሴተኛ አዳሪ፣ የቡና ቤት ሴት፣ ሸሌ፣ ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ ሂያጅ፣ አመንዝራ፣ ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን
⚡️#በቀጣይ_ክፍል በዝሙት እንዴት ሴቶች ጉዳት እንደሚደርስባቸዉ እንዳስሳለን
#ምዕራፍ ➋
ይቀጥላል......
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ለሌሎች ማከፈልዎን አይዘንጉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6158