tgoop.com/Islam_and_Science/6152
Last Update:
#በታሪክ_ትልቁ_ሶላት_አልጀናዛ
ሱልጧን ሱለይማን አልቃኑኒ ከእለታት በአንዱ ለሊት
አንድ ህልም አዩና ተደናግጠው ከእንቅልፋቸው ተነሱ
የቅርብ ዘባቸውን ተጣርተው
ፈረስ እንዲያዘጋጅላቸውና ሲነጋ ጎዳና ላይ ወጥተው
የህዝቡን የቀን እንቅስቃሴ ማየት እንደሚፈልጉ አስረዱት
ከነጋ በኋላ በተዘጋጀላቸው ፈረስ ብቻቸውን ጎዳና ላይ
በመውጣት የህዝቡን እንቅስቃሴ መቃኘት ጀመሩ በዚህ
መካክል አንድም ሰው ያልተከተለው አንድ አስከሬን
በጎዳናው ላይ ሁለት ሰዎች ብቻ ወደ መቃብር ሲወስዱት
ተመለከቱ
ሱልጧን ሱለይማንም ቀርብ ብለው ይሄ ብቻውን ወደ
መቃብር የሚሸኘው አስከሬን የማነው? ብለው ሲጠይቁ
ይሄማ ዝሙተኛና ኸምር ጠጪ ከሚስቱ ውጭ ልጅም ሆነ
ቤተሰብ የሌለው ግለሰብ አስከሬን ነው ስለዚህ የዚህን
ዝሙተኛ እና መጠጥ ጠጪ አስክሬን ማንም ሰው
ሊሸኘውና ሊሰግድበት ፍቃደኛ የሆነ ሰው የለም ይሏቸዋል
ሱልጣን ሱለይማንም በጣም ይቁጡና ይሄማ እንዴት
ይሆናል የሙሀመድ ኡመት አይደለምን? ይሉና አስከሬኑን
ተሸክመው ወደ ባለቤቱ ይመልሱታል
እዛም እንደደረሱ ባለቤቱ እጅግ አዝና ታነባለች ሱልጣኑም
በመገረም እንዴት እንደዚህ ታለቅሻለሽ ባለቤትሽ
ዝሙተኛና ጠጪ አልነበረም አንዴ? ይሏታል
የሟች ሚስትም የሚጠይቃት ሰው ሱልጣን ሱለይማን
መሆናቸውን አታውቅም
ባለቤቴ አላህ ይዘንለትና አላህን የሚፈራ ነበር ልክ
እንደሱ አላህን ፈሪ ልጅ ይመኝ ነበር ነገር ግን ሞት
ቀደመው ትላቸዋለች
ሱልጣኑም ባለቤትሽ ከዝሙተኝነቱና ከጠጪነቱ ውጭ
ምን የተለየ ነገር ይሰራ ነበር ? ይሏታል
ሚስትም ባለቤቴ ሁልጊዜም በእየመንደሩ እየዞረ መጠጥ
ወደሚገኝበት ቦታ በመሄድ መጠጦችን በብዛት በመግዛት
ወደ ቤት ያመጣና ግቢ ውስጥ ባዘጋጀው ጉድጓድ ውስጥ
ይደፋውና አልሀምዱሊላህ ዛሬ ለብዙ ሙስሊም ወጣት
ወንድሞቼ ብዙ ወንጀልን ቀነስኩላቸው እያለ ጌታውን
ያመሰግን ነበር
በማስከተልም ሁልጊዜ ምሽት በሆነ ቁጥር ወደ ሴተኛ
አዳሪዎች መንደር በመጓዝ ለብዙ ሴተኛ አዳሪዎች ዝሙት
ሰርተው የሚጋኙትን ሙሉ የቀን ገቢያቸውን ክፍያ
ከሰጣቸው በኋላ ወደቤታቸው እንዲመለሱ ያደርግና እቤቱ
መጥቶ አልሀምዱሊላህ ዛሬ ለብዙ ሙስሊም ወጣት
ወንድሞቼ የዚናን ወንጀል ቀነስኩላቸው እያለ ጌታውን
ያመሰግን ነበር
እኔም ሰዎች ከላይ የምትሰራውን ብቻ ነው የሚመለከቱት
አንድ ቀን መሞትህ አይቀርም ያኔ ጀናዛህን አጥቦ ሶላተል
ጀናዛ የሚሰግድብህና የሚቀብርህ አንድም ሰው አታገኝም
እለው ነበር
እሱም እያሰቀ ጀናዛየን ሱልጣን ሱለይማን አጥቦ በጀናዛየ
ላይም ሱልጣን ሱለይማን ከእነ ሰራዊቱ ከእነ
ምኒስትሮቹና ከታላቅ የሀገሪቱ ሼኮች ጋር ሆኖ የሀገሪቱ
ሁሉም ሙስሊሞች ሲሰግዱብኝ ታያለሽ እያለ ይነግረኝ
ነበር በማለት የባሏን የህይወት ታሪክ አጠገቧ ለቁመው
ሰው ትነግረዋለች
ሱልጣን ሱለይማንም ከልቡ በማልቀስ አዎ ልክ ነው እኔ
ሱልጣን ሱለይማን ነኝ እኔው እራሴ ጀናዛውን አጥበዋለሁ
ይለና የዚህን ምርጥ የአላህ ባሪያ ጀናዛ እራሱ ካጠበ
በኋላ
ለሀገሪቱ ሙሉ ሰራዊት ለሀገሪቱ ሙሉ ባለስልጣናት
ለሀገሪቱ ሙሉ መሻኢኾች ለሀገሪቱ ሙስሊሞች በሙሉ
ትዕዛዝ በማስተላለፍ በዚህ የአላህ ባሪያ ጀናዛ ላይ
እንዲገኙ በማድረግ ሱልጧን ሱለይማን አልቃኑኒ በታሪክ
ትልቁን ሶላተል ጀናዛ በዚህ ድንቅ የአላህ ባርያ ላይ
አሰገዱ።
ውጭ ላይ ለእኛ በተገለጠልን ነገር ላይ ብቻ ተመርኩዘን
የአላህን ባሮች መለካት መመዘን ደረጃን መስጠት ከባድ
ነገር ነው ከእኛ እውቀትም ውጭ ነው...
በዚህ አስተማሪ ታሪክ ብዙዎች ሊማሩበት ይችላሉና ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ሳያደርጉ አይለፉ!!
ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6152