tgoop.com/Islam_and_Science/6147
Last Update:
#አይነስዉሩ_ልጅ
✍አሚር ሰይድ
አንድ ሰውዬ ነበር ሁለት ልጆች አሉት በዲኑ ላይ ብዙም አይደለም፡፡ብዙን ጊዜ በሰዎች በማሾፍና በማላገጥ የተጠመደ ነው።አንድ ቀን መንገድ ላይ የሚሄድ ዐይነ ሥውር አጋጠመው ሰዎችን ሊያስቅበት ብሎ ከጎኑ እየሄደ በዚህ ሰው ማላገጥ ጀመረ፡፡በዚህን ጊዜ ዐይነ ስዉሩ ሰው ልቡ ተሰበረበ እጅጉ😔ተሰማው፡በውስጡ ያለውን ደግሞ አላህ ይወቅ፡፡ከወራት በኋላ ይህ ሰው ዐይነ ስውር የሆነ ልጅ ተወለደለት፡፡ በዚም የተነሳ ተደናግጦና ሃሳብ ገብቶት ከዚህ ልጅ ጋር ግንኙነቱን አቋረጠ፡፡ እሱን ትቶ ለሌሎቹ ሁለት ልጆች ትኩረት ሰጠ፡፡ አዲሱን ልጁን ለእናቱ በመተው የሚያስፈልገውንም ወጭ ለሷ መስጠት ያዘ።ሆኖም ግን ውስጡ በእጅጉ ተጎድቶ ነበር፡፡ ይህ ልጅ ለመጥፎ ድርጊቶቹ መቀጫ ይሆን ዘንድ የተላከበት መሰለው፡፡የአባትነትን ፍቅር ለልጁ ነፈገዉ
ህፃኑ ልጅ ስድስት ዓመት ሞላው።አንድ ቀን እናት ከሁለት ልጆቹ ጋር ወጣ ብላ ስለነበር አባት ከዐይነ ስውር ልጁ ጋር ብቻውን ቤት ውስጥ ቀረ፡፡ቀኑ ጁሙዓ ነውና ልጁ አባቱ ወደ መስጊድ እንዲወስደው ጠየቀ፡አባት የስድስት ዓመት ልጁ የሚሰግድ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ደነገጠ፡ከዚህ በፊት መስጅድ ይወስደው የነበረ ማን እንደሆነ ጠየቀው። ልጁም እናቱ እንደሆነች ነገረው፡፡ አባት ልጁን ወደ መስጅድ ይዞት መሄድ ጀመረ።
አንድ የሚያውቀው ትልቅ ሽማግሌ ይዞ የሚሄድ ዓይነት ተሰማው። ልጁ ከቁርአን የአል ከህፍን ምዕራፍ እያነበበ ነበር፡፡ አባት ይህን ሲሰማ ማልቀስ ጀመረ፡፡ በልጁ ሰበብ አላህን አወቀ፡፡ ልጁ በቃሉ ቁርኣንን መሸምደዱ ገረመው፡፡
ስብራቱ የነበረው ልጅ በዚህ መልኩ ወደ ፀጋ የተለወጠ ሆኖ አገኘው:: ሱብሀነሏህ፡
ትበድልና ይሰብርሃል፡፡ ትግጎዳለህም፡፡ወደሱ ተጠግተህ በለመንከው ጊዜ ግን ስብራቱን ወደ ፀጋ ይለውጥልሀል፡፡
💚እናትነት ይህ ነዉ
BY ISLAMIC SCHOOL

Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6147