tgoop.com/Islam_and_Science/6146
Last Update:
ድል ያለ ሰርግ ተደግሶ ባል እና ሚስት ቃለ መሀላ ለመፈጸም እየተዘጋጁ ሳለ ነው ባል ቃል ከመግባታችን በፊት መናገር የምፈልገው ነገር አለ በማለት ማይኩን የተቀበለው።
ቀጠለናም የታሸገ ፖስታ ለሁሉም የሰርጉ ታዳሚዎች እንዲሰራጭ እና ታዳሚዎቹም ፖስታውን ከፍተው እንዲመለከቱት ያደርጋል፡፡
የታሸገው ፖስታ ውስጥ ያለው ሚስቱ ለመሆን ቃለመሃላ ለመፈፀም እየተቁነጠነጠች ካጠገቡ የቆመችው ሴት እና አንደኛ ሚዜው የኔ ፍቅር የኔ ውድ እየተባባሉ ሲማግጡ የሚያሳይ ፎቶ ነበር፡፡
ሙሽራው አሁንም ማይኩን እንደያዘ “በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ምስል ውዷ እጮኛየ እና የልብ ጓደኛዬ ማንም አያየንም ብለው ተደብቀው ሲማግጡ የሚያሳይ ነው። ታዲያስ ከእንደዚች አይነት ሴት ጋር ትዳር ባልመሰርት የሚፈርድብኝ አለ?!"ብሎ ታዳሚውን ጠየቀ።መልስ አላገኘም።
ኋላም ሙሽሪት በድንጋጤ በቆመችበት ደህና ሁኚ ብሏት ከቤተሰቦቹ ጋር የሰርጉን አዳራሽ ጥሎ ወጥቷል፡፡
☞ የዴይሊ ሜይል ዘገባ ነው
#ከዝሙት እንጠንቀቅ እንቶብት...ዝሙት ዛሬም ነገም ከነገ ወዳም መዘዙ ሰፊ ነዉ፡፡ለ15 ሰከንድ የሀራም እርካታ የ40 የ50 አምት ፕላናችንን አናበላሽ፡፡
አላህን አምፀን አላህ በዱንያ ዋጋችንን ያስከፍለናል ብድር በምድር‼️
ነገ እኛም በዝሙት ላይ ያለን እኛን በምን እንደሚያዋርደን አይታወቅም፡፡
ወላሂ ዝሙተኛ ሰዉ ሰላም የለዉም...በዱንያ ድህነት ጭንቀት ነዉ፡፡ሴቷም እራሷን ዝቅ ታደርጋለች.ዝሙተኛ ሴት ቤተሰብ የማያቃት ሴተኛ አዳሪ ማለት ነች..ለምን ዚና ስትሰራ ቤተሰቧ ሳያያት ነዉ፡፡ልጄ ጎበዝ ናት ዲነኛ ናት ይላል ቤተሰብ..እሷ ግን ቤተሰብ የማያቃት ሴተኛ አዳሪ ነች
ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL

Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6146