tgoop.com/Islam_and_Science/6145
Last Update:
#የኪፍል_ተዉበትና_የአሏህ_አቀባበል
✍አሚር ሰይድ
ማንኛወም ሰዉ ከተዉበት ተዘናግተናል..በተለይ ብዙዎቻችን አሁን ላይ ቦይፍሬድ ገርልፍሬንድ ስም በተጨማለቅንበት በዝሙት ላይ ሁነን ለመቶበት አንዴ ገብተንበታል በሚል አስተሳሰብ የብስ በወንጀል ላይ ወንጀል እየደራረብን ነዉ፡፡ነገ ይሄን ዛሬ ሞቻችንን ሳናቀዉ በጊዜያዊ ደስታ ዱንያችንን አኼራንም እያጣን ነዉ...እስኪ ዝሙት የሚሰራዉ በአራጣ በቁማር ወንጀል ላይ የነበረዉ ኪፊል ለሊት ሙቶ አደረ አላህም ተዉበቱን ተቀበለዉ በምን ይሆን ተዉበተን የተቀበለዉ??እስኪ የሀቢቡና ሙሀመድ የተናገሩትን ሀዲስን ልጋብዛችሁ
ዐብደሏህ ቢን ዑመር(ረ.ዐ)እንዳወሩት እኔ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከሰባት ጊዜ በላይ እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:-
በበኒ አስራኤል ውስጥ ኪፍል የሚባል ሰው ነበረ:: ይሄ ሰው ማንኛዉም ወንጀል በመሥራት ይታወቃል። አላህን የማይፈራ የለየለት ሙጅሪም ሰው ነበረ፡፡ ያገኘውን ሀጥያት የሚሠራ ሰው ነበረ፡፡
አንድ ቀን አንዲት ሴት ተቸገረችና (መቼስ አላህ ድህነትን ያላለጠበት ሰው ፈተናው ከባድ ነውና) እርሱ ጋ መጥታ ገንዘብ ጠየቀችው፡፡ እርሱ ሃብታም ሰው ነበር፡፡ ወንጀል የሚባል ግን አንድም የቀረው ነገር የለም፡፡ ከዚያም ስድሳ ዲናር ሊሰጣትና እርሷ ደግሞ ለዚና እራሷን ልታመቻችላት ዘገድ እነጋገራት፡፡ እንግዲህ አስቡት! በዚያን ጊዜ 60 ዲናር ማለት በጣም ከፍተኛ ብር ነው፤ በኃይለኛው ያማልላል፡፡
ይህች ሴትም ፈቃደኛ ሆነች ተቸግራለችና ድህነቱ አስገደዳት)፡፡ ከዚያም ስድሳወጣም ዲናር ሰጣት፡፡ ከዚያም እርሷ እራሷን አመቻቸች፡
እርሱም ዚና ለመስራት እላይዋ ላይ ተቀምጦ ሳለ ይህች ሴት ከመቅፅበት ተንቀጠቀጠች አለቀሰች😢 ተርገበገበች፤ ተንዘፈዘፈችና በኃይለኛውም አነባች፡፡
.... ኪፍልም ምን ነካሽ? ብዙ ገንዘብ አይደል እንዴ የሰጠሁሽ? አስገድጄሻለሁ እንዴ? በፍላጎትሽ አይደለም እንዴ? እናም ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሺዉ?? አላት፡፡
....ከዚያም ይህች ሴት ወሏሂ! እኔ ይህንን የዚና ኃጢአት በዕድሜዬ እኮ ሠርቼው አላውቅም፤ ችግሩ አስገድዶኝ ነው እንጂ። ፈፅሞ ሠርቼው የማላውቀው ወንጀል ስለሆነ አሁን አላህን ፈርቼ ነው የማለቅሰው አለቸው፡፡ ......አርሱም አላህን ፈርተሽ ነው የምታለቅሺውን??
...... አላት፡፡ አዎ› አለችው፡፡
አስቡት አንግዲህ! ይሄ ዕድሜ ልኩን ወንጀል ሲሠራ የኖረ ሰው ነው፡፡ መች ይህ ብቻ እንድም መልካም ሥራ ሠርቶ አያውቅም፡፡ የዚህች ሴት ተቅዋና የርሷ መንቀጥቀጥ ልቡን ነካውና ወዲያው ይህንን ሁሉ ስድሳውን ዲናር ውሰጂው፡፡ እኔ አሁን ተወብት ገብቻለው እናም አልነካሽም ዚና አልሰራሽም፡፡ እኔ ካሁን ጀምሮ አበደን አላህን አልወነጅልም፡፡ ኃጢአት፣ ዝሙት፣ ፀያፍ ድርጊት የሚባል ነገር ካሁን ወዲያ ምንም አልሠራም፡፡ አንቺ ችግሩ እያለብሽ፣ ገንዘቡንም ለመውሰድ እየፈለግሽ ግን የአላህ ፍራቻው ገታሽ፡፡ አኔም ከዚህ በኋላ አላህን ፈፅሞ አላምፅም አለ፡፡
ከዚያም ነብዩ ﷺ እንደተናገሩት ይህ ሰው በዛቸው ለሊት ሞቶ አደረ፡፡ መሞቱም በበሩ ላይ ተፅፎ በተገኘዉ ፁሁፍ ተረዳ፤ በአላህ መላእክት አማካኝነት፡፡
አላህ ለኪፍል ምሮታል የሚል ዐ.ነገር በበሩ ላይ ለየት ባለ ጽሑፍ ተፅፎ ተገኘ፡፡» (ቲርሚዚ ዘግበዉታል)
⚠️⚠️ ከዝሙት እንቶብት አሁን ዝሙትን መሥራት ውሃን የመጠጣት ያህል እና እጮኛን መያዝ ሻንጣን የመያዝ ያህል ቀላል በሆነበት ዘመናዊት ዓለም ውስጥ በመዘናጋት ያለተዉበት ሞትን እየጠበቅን ነዉ...ይቺ ነገ እንቶብታታለን ያልናት ቀን ነገ ሳትደርስ ሞት ቀድማን ከነገ ወዳ ያለዉን የአኼራ ህይወት የቀብር ህይወት የነኪርና ነኪር ጥያቄ ...አላህ ፊት ያለ አስተርጓሚ ለጥያቄ ለመቅረብ ምን ያህላችን ዝግጁዎች ነን??
ምን ያህሎቻችን ለመቶበት ዝግጁዎች ነን??
ሼር በማድረግ ኢስላማዊ ግዴታዉን ይወጡ..በዚህ ፁሁፍ የተነሳ አንድ ሰዉ ቢቶብት ትልቅ ነገር ነዉና...
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6145