tgoop.com/Islam_and_Science/6142
Last Update:
⚠️#ኢስላምን_በዉርስ_ያገኘነዉ_ሀይማኖት_ስለሆነ_ዝሙትን_ተዳፈርን
✍ አሚር ሰይድ
«በአሜሪካ ያሉ ሰለምቴ ሙስሊሞች ከምንም በላይ ከሁለት ወንጀሎች በግልፅ እንደራቁ አስረግጦ መናገር ይቻላል፡፡ አዎን! ማንኛውም ሰለምቴ አሜሪካዊ ሙስሊም ከሪባ የራቀ ነው፡፡ እንዲሁም ማንኛውም ሰለምቴ አሜሪካዊ ሙስሊም ከዝሙት የራቀ ነው፡፡» (ኑእማን አሊ ካን - አሜሪካዊ ዳዒይና የቁርኣን ተንታኝ)
እንደሚታወቀው አብዛኛው የሀገራችን ሙስሊም ኢስላምን የሚወርሰው ከቤተሰብ ነው፡፡ ቤተሰቡ ሙስሊም የሆነ ልጅ እርሱም ሙስሊም ይሆናል፡፡ ከዚህም የተነሳ ኢስላምም በውርስ የሚያገኝ ሃይማኖት ይሆናል፡፡ ኢስላምን በውርስ የሚያገኝ ልጅ ደግሞ ስለእምነቱ ይህንን ያህል የበዛ ትኩረት ሰጥቶት ላያጠናው ይችላል፡፡
ነገር ግን አሜሪካዉያን ሙስሊሞችን በምሳሌነት ብንወስድ እነርሱ ዘንድ አብዛኞቹ ኢስላምን የተቀበሉት አንብበው፣ አጥንተው፣ ተመራምረው፣ አነፃፅረውና እዉነቱን አንጥረው ካወቁ በኋላ ነው፡፡ ከዚያም በዚህች ምድር ላይ ብቸኛው እውነት ብቸኛው መለኮታዊ ሀይማኖትና ታላቁ ፀጋ ኢስላም መሆኑን ስለሚረዱ ወደ ኢስላም ሲመጡ ዲኑን በሚገባ ለመተግበር ነው፤ በሙሉ ልባቸው፡፡
በተለይም ምዕራባዉያን ዜጎች ሙስሊም ከሆኑ በኋላ አንዳች ሲሠሩት የነበረው ነገር በኢስላም የተከለከለ መሆኑን ካወቁ ወዲያው ያንን ነገር ይተውታል፡፡
⚡️⚡️አሜሪካዊው ታላቁ ዳዒይና በቁርኣን ተፍሲር ትልቅ ዕውቅናን ያገኘው ኑእማን አሊ ካህን በበኩሉ በምዕራቡ ዓለም እጅጉን የተንሰራፉ ነገሮች በተለይ ወለድና ዝሙትን የመሳሰሉ ኃጢአቶች እነሱ ዘንድ ከሞላ ጎደል እንደማይታወቁ ይናገራል፡፡ በተለይም ከጥቂት ዓመታት በፊት የደረሰውን የምዕራቡን ዓለም የገንዘብ ቀውስን አስመልክቶ ቀውሱ ሙስሊሞችን እምብዛም እንዳላጠቃቸው በመጥቀስ አሜሪካዊው ሙስሊም ከወለድ የራቀ መሆኑን እንደማሳያ ያነሳል፡፡
#ቀጥሎም ዝሙትን አስመልከቶ አሜሪካዉያን ሙስሊሞች ከዚህ መራቃቸውን እንደ ማሳያ የሚያነሳው ነገር ቢኖር የመስሊም ሴቶችን ታላቅ ግብረገብነትና የሒጃብ አለባበሳቸውን በመጥቀስ ነው::
በዚህች ሀገር የሴቶች ትልቁ መከበሪያቸው ሒጃብ ነው:: የራስ መተማመናቸውና ለኢስላም ያላቸው ፍቅር ያስደንቅሃል፡፡ ሴቶቹ እንዴ ከሰለሙ በኋላ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን ሊከተሉ ቀርቶ ከቶውኑ አያስቡትም፡፡ ቀድሞውኑ ኢስላምን አጥንተውትና መርጠው ስለሚመጡ ሰዉ ምን ይለኛል የሚለውን ነገር ከመጤፍ አይቆጥሩትም፡፡ ወንዶቹም ቢሆኑ አብዛኞቹ ያገቡ ስለሆኑ ስለዝሙት አይነሳባቸውም፡፡
✨✨እንደውም በአንድ አጋጣሚ የተከሰተውን ነገር ለምን አልነግራችሁም? በአንድ ወቅት አንዲት ደምቃና የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ተሸሞንሙና የወጣች እንስት ከአንድ ወጣት ሙስሊም ጋር በባቡር ላይ ይገናኛሉ፡፡ ሰዉ ሁሉ አተኩሮ ያያታል፡፡ እርሷም እየተገማሸረች የምትወጣው ለዚህ ነው፡፡ ወንዱ ሁሉ በአድናቆትና በምኞት ይመነጥራል፡፡ ይህ ወጣት ግን አንዳችም ትኩረት ላይሰጣት ቀረ፡፡ እርሷ ግን አልፎ አልፎ ትገረምመዋለች፡፡ እርሱ ወይ ፍንክች አላለም፡፡ ታዲያ ተሳፋሪው ቀስ በቀስ እየወረደ ሲቀንስ እርሷ አውቃ የወጣቱ ዓይን ውስጥ ለመግባት ተጠጋችው፡፡ እርሱ ግን አሁንም ከምንም አልቆጠራትም፡፡ ወዲያ ወዲህ ብትቀበጥም አላተኮረባትም፡፡
..... በመጨረሻም በኃይለኛው ተቆጥታ ለመሆኑ አንተ ወደኔ አንዴም የሚታየው እኔ ይህን ያህል ቀፋፊ ነኝ እንዴ? ቆይ እንዲህ ከሆነ እኔ ለማነው ተጋጊጬ የምወጣውን ስትል አቧረቀችበት፡፡
እርሱ ግን በተረጋጋና የራስ መተማመን መንፈስ በተሞላበት ሁኔታ ይህንን ለምን እንደማያደርግ አስረዳት፡፡ አየሽ! እኛ ሙስሊሞች ዕይታችንን እንድንቆጣጠር ታዘናል፡፡ ስለዚህ ወደ ባዳ ሴት ሆነ ብሎ መመልከት የተከለከለ ነው፡፡ ለዚህ ስል ብቻ ነው እኔ ወደ አንቺ የማላየው፡፡ ከዚህ ውጭ በግል ምንም ያደረግሸኝ ነገር የለም፡፡ የእምነት ጉዳይ ሆኖብኝ ነው ወዳንቺ የማልመለከተው አላት፡፡ ልጅቷ በሰማችሁ ነገር ተገረመች፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰውና እምነት እንደዚያ ሰይጣንን አብዝታ በምታበረታታው ሀገረ አሜሪካ መኖሩ አስደነቃት፡፡ እምነት ሰውን ከብልግና ሲታደግ አስተዋለች፡፡ እናም ለመሆኑ ያንተ እምነት ምንድነው? ስትል ወጣቱን ጠየቀችው፡፡ እርሱም እምነቱ ኢስላም መሆኑን ነገራት፡፡ ስለኢስላምም አንዳንድ ነገሮችን ነገራት፡፡ ከዚያም ስልክ ተለዋወጡና በዚሁ ተለያዩ፡፡
ልጅቷ በሰማቸውና ልጁ ላይ ባየችው እፁብ ድንቅ ምግባር እጅጉን ተደምማለች፡፡ እንዲህ ዓይነት ወጣት ገጥሟት ስለማያውቅ ስለርሱ እምነት ልታጠና ጓግታለች፡፡ ወዲያው በነጋታው ደውላ የቁርአንን ኮፒ እንዲሰጣት ጠየቀቸው:: እርሱም የቁርአን ኮፒ ሰጣት ልጅቷም ቁርአንና ሌሎችንም ኢስላማዊ መጻሕፍት ለስድስት ወራት አከታትላ አጠናችው፡፡ ስድስት ወሩ እንዳለቀም ለልጁ ደወለችና ኢስላምን መቀበል እንደምትፈልግ አበሰረችው፡፡ እሱም ወደመስጊድ ወሰዳትና ሰለመችም፡፡ የአላህን አንድነትና ብቸኛ አምላክነቱን መሰከረች፡፡ገና ልትሰልም ስትመጣ እራሱ ሒጃቧን በወጉ ለብሳ ነበር፡፡ እናም አሁን በኛ ማዕከል ውስጥመደበኛ ሴት ዳዒይ ስትሆን በርሷ ሰበብም በርካታ ሴቶች ወደ ኢስላም መጥተዋል፡፡
(ምንጭ፡- ቮይስ ኦፍ ኢስላም - አሜሪካ)
በመጨረሻም ኑእማን አሊ ካን አያይዞም እንዲህ ይላል፡-
«በአሜሪካ ፊትናው ከባድ ነው:: ግና የሰለምቴው ንቃተ ሕሊና ከፍተኛ ነው::
ሙስሊሙ ሐራምና ሐላልን በሚገባ ለይቶ ያውቃል፡፡ እዚህ በአላህ (ሱ.ወ) ሕግ ማቻቻል የሚባል ነገር የለም፡፡ አንዳች ነገር ሐራም መሆኑን ካወቁ ከቤተሰብ ጋር የሚያለያይ እንኳን ቢሆን ለኢስላም ሲሉ ያደርጉታል፡፡,, (ምንጭ፡- ቮይስ ኦፍ ኢስላም - አሜሪካ)
✏️አላዋቂነት ለሁሉም ኃጢአት አብይ ምክንያት ነው፡፡ በተለይ ዝሙት ላይ የድንቁርና አሻራ እጅጉን ይጎላል፡፡ የሰው ልጅ ዓይን ስላለው በጭለማ ውስጥ እንደማያይ ሁሉ ጭንቅላት ስላለው ብቻ ዕውቀት አለው ማለት አይቻልም፡፡ ዕውቀት ከሌለው ደግሞ ድንቁርና መጥቶ እንደ ወቃቢ ይሰፍርበታል፡፡ በርግጥም ከድንቁርና የበለጠ ክፉ ውቃቢ የለም፡፡ ታዲያ የድንቁርና ውቃቢ ያለበት ሰው ቢያንስ በአራት መንገዶች ዝሙት ላይ የወድቃል በአይኑ በምላሱ በእጁ...
🙄እኛ ኢትዮጲያን የነጃሺ ሀገር በአለም ሁለተኛ ሙስሊም የተቀበልን የኢትዮ ግማሽ ፐርንሰት በላይ ሙስሊም ነን ..ዲነኛ ነን ኪታብ ቀርተናል ..መስጊድ ተነካ..ኢስላም ተደፈረ ..ወዘተ በምላስ እንላለን በጎን ዚና እንሰራለን🤔
☞ክርስቲያኖች ኢትዮ የሙሴ ፅላት አለ ..አርባ አራት ታቦት አለ ..ኢትዮ ገማደ መስቀሉ አለ ይሄን ያህል ገዳም አለን ኢትዮ የኛ ናት በጎን ዚና እንሰራለን🤔
✍✍ ለወደፊት የማዘጋጀዉ ፁሁፍ አዲስ አበባ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም አራተኛ የዝሙት ሀገር መሆኗን በአለም ተረጋግጧል በዚህ ሰፋ ያለ ፁሁፍ ጊዜ ሳገኝ አዘጋጃለሁ፡፡
ግን ኢትዮጲያ አዲስ አበባ ያለዉ ሀይማኖተኛ ሀይማኖት ያለዉ ነዉ ግን ከአፍሪካ 1ኛ የዝሙት ሀገር ነዉ...ኢንሻ አሏህ ስለ አዲስ አበባ የማይታመኑ 100% እዉተኛ ነገሮች በፁሁፍ ይቀርባሉ፡፡ሀይማኖት በልብም በተግባር ነዉ
ፈጣሪ የምላስ ሀይማኖተኛ አስመሳይ ከመሆን ይጠብቀን፡፡
ከዝሙት እንጠንቀቅ ..በዝሙት መስመር ያለን እንቶብት!!!
#ምንጭ ☞በዝሙት አንዘምን መፅሀፍ
ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6142