tgoop.com/Islam_and_Science/6139
Last Update:
#በሰባት_ጣዖታውያን_ላይ_ያደረጉት_ዱዓ
ቡኻሪና ሙስሊም ኢብኑ መስዑድን በመጥቀስ እንደዘገቡት፡
«ነቢዩ ﷺ ከዕባ ውስጥ ይሰግዱ ነበር። አቡ ጀሀልና ባልደረቦቹ ተቀምጠዋል። «ሙሐመድ ሱጁድ ሲያደርግ ፈርስ የሚያፈስበት ማን ነው?» ተባባሉ። ከመካከላቸው ይበልጥ ተንኮለኛው ፈርስ ይዞ መጣ። ሱጁድ እስኪያደርጉ ጠበቀና ከጀርባቸው ላይ አፈሰስባቸው፡፡ እኔ ሁኔታውን እከታተል ነበር። ምንም ላደርግ አልቻልኩም። ጉልበት ቢኖረኝ ኖሮ ይህ ነገር በነቢዩ ላይ እንዳይደርስ በተከላከልኩ ነበር።
ሰዎቹ ይሳላቁ ጀመር። አንተ ነህ አንተ ነህ እየተባባሉም ይቀልዱ ጀመር። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሱጁድ እንዳደረጉ ናቸው" ራሳቸውን ከሱጁድ አላቀኑም። ልጃቸዉ ፋጡማ(ረ.ዐ) መጣችና ቆሻሻውን ከጀርባቸው አስወገደችላቸው። ራሳቸውን ቀና አደረጉና፡ «አላህ ሆይ! ቁረይሾችን ተበቀልልኝ» በማለት ሦስት ጊዜ በመደጋገም ዱዓ አደረጉ።
እርግማኑን ሲስሙ ሰዎች ተጨነቁ። በዚያ ሀገር ውስጥ የሚደረግ ዱዓ ተቀባይነት እንዳለው ያምኑ ነበር። ነቢዩ በመቀጠልምሰዎችን በስም ጠርተው ዱዓ አደረጉባቸው፡፡ እንዲህ አሉ «አላህ ሆይ!
>አቡ ጀህልን ተበቀልልኝ።
> ዑትበት ኢብኑ ረቢዓህን'
>ሸይበት ኢብኑ ረቢዓህን፡
>ወሊድ ኢብኑ ዑትባህን
>ኡመያ ኢብኑ ኸለፍንና
> ዑቅበት ኢብኑ አቢ ሙዒጥን ተበቀልልኝ»
አንድ ሰውም ጨምረው ጠሩ። ስሙን አላስታወስኩትም።
ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ፣ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ስማቸውን ጠቅሰው የረገሟቸው እነዚህ ሰዎች በድር ላይ ተገደሉ። ገደል ውስጥም ተጣሉ።
ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6139