tgoop.com/Islam_and_Science/6119
Last Update:
#ትልቅ_አስተምህሮ
✍አሚር ሰይድ
ዐብዱረሕማን ኢብኑ ሰሙራህ (ራዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺአንድ ቀን ወደኛ መጥተው የሚከተለውን ነብያዊ ንግግር አደረጉልን። እንዲህም አሉን-
“ዛሬ ቀን አንዳች የሚገርም ሕልም አይቻለሁ እርሱም
➊. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ የሞት መልአክ ሕይውቱን ሊነጥቀው ወደርሱ _ መጣ _ ለወላጆቹ የነበረው ቅን ታዛዥነት ወደርሱ በመምጣት የሞት መልአክ የሰውየውን ሕይወት እንዳይወስድ ሲከለክልለት ተመልክቻለሁ !
➋. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ ሰይጣኖች ከበውት ሳለ የአላህ ማስታወስ ወደርሱ በመምጣት ሰይጣኖችን ከርሱ አባረረለት፤
➌. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ የጀሀነም መላእክት ከበውት ሳለ የሚሰግዳት ሰላት ወደርሱ በመምጣት ከእጃቸው ስትነጥቀው ተመልክቻለሁ
➍. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ በጥም ሳቢያ ከአንድ ኩራ አጠገብ ሊጠጣ ሲል ተባረረ፡፡ ጾም ወደርሱ በመምጣት ሲያጠጣው ጥሙንም ሲያረካለት ተመልክቻለሁ
➎. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ ነብዮች በቡድን በቡድን ተቀምጠው ሳለ ወደ አንድ ቡድን በሄደ ቁጥር እንዳይቀመጥ ይከለከልና ይበረር ነበር፡፡ ለጀናባ ያደረገው ትጥበት ወደርሱ በመምጣት ከኔ ጐን ሲያስቀምጠው ተመልክቻለሁ !
➏. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ ከፊት ለፊቱም፣ ከጀርባውም፤ ክቀኙም ከግራውም _ ከሁሉም : አቅጣጫው : ጨለማ አካብቦት ነበር፡፡ ያደረጋቸው ሐጅና ዑምራ መጥተው ከጨለማ አውጥተው ወደ ብርሃን ሲያስገቡት ተመልክቻለሁ
➐. ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ በእጆቹ የእሳት ነበልባልን ሲከላከል የሰጣት ምጽዋት ወደርሱ መጥታ በእሱ ላይ ጥላ ስትሆን ተመልክቻለሁ
➑. ከሕዝቦቼ መካከል አንድ ሙእሚኖችን ሲያናግር እነሱ ግን አያናግሩትም ነበር። ሲቀጥለው የነበረው ዝምድናን የመቀጠል ተግባር ወደርሱ በመምጣት ሙእሚኖች ሆይ! እሱ ዝምድናውን ሲቀጥል የነበረ ሰው ነውና እናግሩት ጨብጡትም ሲላቸው ተመልክቻለሁ
➒. ክሕዝቦቼ መካከል አንዱ የጀሀነም ዘበኞች አዋክበውት ላለ ሲፈፅመው የነበረው በመልካም የማዘዝና ከመጥፎ የመከልከል ተግባር ወደርሱ በመምጣት አከዘበኞቹ እጅ ነፃ ሲያደርገውና ወደ እዝነት መላእክት ሲያስረክበው ተመልክቻለሁ!
➓.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ ከፊት ለፊቱ አንዳች ግርዶሽ ኖሮ ሳለ መልካም ሥነ-ምግባሩ ወደርሱ በመምጣት እጁን ይዞ ወደ ጌታው ሲያስገባው ተመልክቻለሁ
➊➊.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ የሠራው ሥራ መዝገብ በግራ እጁ መጣለት፡፡ ለአላህ ያለው ፍራቻ ወደርሱ በመምጣት መዝገቡን በቀኝ እጁ ሲያደርግለት ተመልክቻለሁ፤
➊➋.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ የመልካም ሥራዎቹ ሚዛን ክብደት ሲያንስ ከአብራኩ የተገኙት ልጆቹ ሲሞቱ ያደረጋቸው ትዕግስቶች ወደርሱ በመምጣት ክብደቱ ከፍ እንዲል አደረጉ፡፡ በዚህም ከቅጣት ሲድን ተመልክቻለሁ፤
➊➌.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ በእሳት ላይ ሲንሳፈፍ አላህን ፈርቶ ያፈሰሳት እንባው ወደርሱ መጥታ ያለበትን እሳት በማጥፋት ከእሳት ነፃ ስታወጣው ተመልክቻለሁ፣
➊➍.ከሕዝቦቼ መካከል እንዱ በጀሀነም አፋፍ ላይ ሳለ አላህን በፅኑ የመፈለጉ ባሕሪው ወደርሱ በመምጣት ከጀሀነም እንዲርቅ ሲያደርገው ተመልክቻለሁ፤
➊➎.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ በሲራጥ ላይ ልክ ኃይለኛ ነፋስ ሲመጣ ከወዲያ ወዲህ እንደምትወዛወዝ የቴምር ዛፍ እሱም ሲንቀጠቀጥ በአላህ ላይ ያለው መልካም ጥርጣሬ ወደርሱ በመምጣት እንዲረጋጋና ባለበት እንዲረጋ ሲያደርገው ተመልክቻለሁ፤
➊➏.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ ሲራጥ ላይ በደረቱ ሲሳብና ሲድህ በኔ ላይ ያደረገው ሶላት (አላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመድ) ወደርሱ በመምጣት በትክክል በሲራጥ ላይ እንዲሄድ ስታደርገው ተመልክቻለሁ፤
➊➐.ከሕዝቦቼ መካከል አንዱ ከፊት ለፊት የጀነት በሮች ሲዘጉ በእርግጥ ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው አምላክ የለም እኔም የአላህ መልዕክተኛ መሆኔን አረጋግጦ የሰጠው ምስክርነት ወደርሱ በመምጣት የጀነት በሮችን ከፍታ ጀነት እንዲገባ ስታደርገዉ ተመልክቻለሁ ብለዉ ተናግረዋል፡፡
ይህ ነብያዊ ሐዲስን አቡ ሙሳ አል-መድየኒይ (ረ.ዐ) “አት-ተር ጊቡ ፈር-ል- ኺሷል አል-መንጂይያህ" በተሰኘው መፅሀፋቸው የዘገቡት ሲሆን ኢብኑ ተይሚይያህ (ረ.ዐ) ይህን ነብያዊ ሐዲስ ትልቅ ቦታ ከመስጠታቸው ባሻገር "ለትክክለኛነቱ በርካታ ማስረጃዎች አሉ'' በማለት ተናግረዋል፡፡
ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6119