tgoop.com/Islam_and_Science/6117
Last Update:
#ምን_የቀረ_ምክር_አለ⁉️
✍አሚር ሰይድ
ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት አንድ የገጠር ሰው ወደ አላህ መልዕክተኛ ﷺ መጣና “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በምድርም ሆነ በዘልአለማዊው ዓለም (አኺራህ) የሚጠቅመኝ ነገር ልጠይቅህ መጣሁ” አላቸው፡፡ እሳቸውም “ያሻህን ጠይቅ" አሉት፡፡
እሱም
✔ከሰዎች በላይ አዋቂ ለመሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡ እሳቸውም
>>“አላህን ፍራ ከሰዎች በላይ አዋቂ ትሆናለህ' አሉት፡፡
✔ከሰዎች የበለጥክ ሀብታም ለመሆን እፈልጋለሁ” አላቸው፡፡
>>“አላህ የሰጠህን ነገር በፀጋ የምትቀበል ሁን፤ ከሰዎች የበለጥክ ሁብታም ትሆናለህ" አሉት፡፡
✔“ከሰዎች የበለጠ ፍትሀዊ ሰው መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>“ለራስህ የምትወደውን ለሌሎች ሰዎች ውደድ! ከሰዎች የበለጠ ፍትሀዊ ሰው ትሆናለህ' አሉት፡፡
✔ከሰዎች የበለጥኩ መልካም መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>"ለሰዎች ጠቃሚ ሁን፤ ከሰዎች በበለጠና መልካም ትሆናለህ" አሉት፡፡
✔ከሰዎች በበለጠ ወደ አላህ የቀረብኩ መሆን እፈልጋለሁ” አላቸው፡፡
>>“አላህን ማስታወስን አብዛ፣ ከሰዎች በበለጠ ለአላህ የቀረብክ ትሆናለህ" አሉት፡፡
✔እምነቴ ምሉእ እንዲሆን እፈልጋለሁ” አላቸው፡፡
>>“ሥነ-ምግባርህን መልካም አድርግ ! እምነትህ ምሉእ ይሆናል" አሉት፡፡
✔መልካም ከሚፈፅሙት መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>"አላህ የማታየው ብትሆንም እንኳ እሱ ያይሃልና እንደምትመለከተው አድርገህ ተገዛው፧ መልካም ከሚፈጽሙት ሰዎች መሆን ትችላለህ" አሉት፡፡
✔ “አላህን በቅን ከሚታዘዙት መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው::
>>“አላህ ግዴታ ያደረገብህን ተግባራት ፈፅም፣ አላህን በቅን ከሚታዘዙት ትሆናለህ" አለት፡፡
✔“አላህን ከኃጢአት የጠራሁ ሆኜ ለመገናኘት እፈልጋለሁ አላቸው፡፡
>>“ሚስትህ ጋር ግብረ-ሥጋ ግንኙነት ከፈፀምክ በኋላ ለመንፃት ብለህ ታጠብ፤ ከኃጢአት የፀዳህ ሆነህ አላህን ትገናኘዋለህ" አሉት፡፡
✔“በትንሳኤ ቀን (የውመል ቂያማህ) ብርሃን ውስጥ ሆኜ ከሞት መቀስቀስ እፈልጋለሁ'' አላቸው፡፡
>>“ራስህን አትበድል፤ ማንንም ሰው አትበድል፡ በትንሳኤ ቀን በብርሃን ውስጥ ሆነህ ትቀሰቀሳለህ" አሉት፡፡
✔ ጌታዬ በትንሳኤ ቀን እንዲያዝንልኝ እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>> “ለራስህ እዘን፤ ለባሪያዎቹም እዘን፤ በትንሳኤ ቀን ጌታህ ያዝንልሃል" አሉት፡፡
✔ኃጢአቶቼ እንዲያንስልኝ እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>> “ምሕረት መጠየቅን አብዛ፤ ኃጢአቶችህ ያንሱልሃል" አሉት፡፡
✔"ከሰዎች በበለጠ ቸር ለመሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>“ችግሮችህን ለፍጡራን አቤት አትበል፤ ከሰዎች በበለጠ ቸር ትሆናለህ" አሉት፡፡
✔"ከሰዎች በበለጠ ብርቱ መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>"በአላህ ላይ ተመካ፤ ከሰዎች በበለጠ ብርቱ ትሆናለህ" አሉት፡፡
✔“አላህ ሲሳዬን እንዲያሰፋልኝ እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>“ንፅሕናን አብዛ፤ አላህ ባንተ ላይ ሲሳይህን ያሰፋልሃል'' አሉት፡፡
✔“አላህንና መልዕክተኛውን ከሚወዱ ሰዎች መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>“አላህና መልዕክተኛ የሚወዱትን ውደድ፤ አላህንና መልዕክተኛውን ከሚወዱ ሰዎች ትሆናለህ" አሉት፡፡
✔ “በትንሳኤ ቀን ከአላህ ቅጣት የተጠበቅኩ መሆን እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>> “አላህ ከፈጠራቸው ፍጡራኖች በአንዱም ላይ አትበሳጭ" አሉት፡፡
✔“ዱዓዬ ተቀባይነት እንዲያገኝ እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>>“ሁሉንም ክልክል የሆኑ ነገሮች ከመመገብ ራቅ፧ ዱዓህ ተቀባይነትን ያገኛል" አሉት፡፡
✔“ጌታዬ በትንሳኤ ቀን እንዳያጋልጠኝ እፈልጋለሁ" አላቸው፡፡
>> “በትንሳኤ ቀን ጌታህ እንዳያጋልጥህ ከፈለግክ ብልትህን ከዝሙት ጠብቅ” አሉት፡፡
✔ “ጌታዬ በትንሳኤ ቀን ገመናዬን እንዲደብቅልኝ እፈልጋለሁ” አላቸው፡፡
>>የወንድሞችህን ገመና ደብቅ፡ አላህ ያንተን ገመና በትንሳኤ ቀን ይደብቅልሃል" አሉት፡፡
✔ከኃጢአቶችና ከስህተት ነፃ የሚያደርግ ነገር ምንድን ነው?” አላቸው፡፡
>>"እንባ፣ ቅን ታዛዥነትና በሽታዎች ናቸው" አሉት፡፡
✔በአላህ ዘንድ በላጩ ምንዳ የትኛው ነው? አላቸው፡፡
>>“መልካም ሥነ-ምግባር፣ መተናነስና በመከራ ጊዜ ትዕግስት ማድረግ ናቸው˚ አሉት፡፡
✔ በአላህ ዘንድ በጣም ትልቁ ኃጢአት የትኛው ነው?" አላቸው፡፡
>>መጥፎ ሥነ-ምግባርና ስግብግብነት ናቸው አሉት፡፡
✔በምድራዊውና በዘልዓለማዊጡ ዓለማት የአላህን ቁጣ የሚያበርዱ ነገሮች የትኞቹ ናቸው?" አላቸው::
>> "በድብቅ የምትሰጥ ሰደቃህ (ምፅዋት) እና ዝምድናን መቀጠል ናቸው" አሉት፡፡
✔ በትንሳኤ ቀን የጅሀነምን እሳት የሚያጠፋ ነገር ምንድን ነው?" አላቸው፡፡
>>“በምድራዊው ዓለም ችግርና መከራ ሲያጋጥም ትዕግስት ማድረግ ነው” አሉት፡፡"
ሀምሌ17/11/2016
ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6117