tgoop.com/Islam_and_Science/6106
Last Update:
በአንድ የቁርአን አያ ደንግጦ የሞተዉ ወጣት
✍አሚር ሰይድ
አቡበከር ወራቅ ቁርአን የሚያጠና አንድ ትንሽ ልጅ ነበራቸዉ፡፡ አንድ እለት ከመማሪያ ቦታዉ ፊቱ ገርጥቶ ጠዉልጎና እንየተንቀጠቀጠ በጊዜ ተመለሰ፡፡ አቡበከር የልጁን ሁኔታ ሲያስተውል በመደነቅ፡- “ምን አጋጠመህ የእኔ ልጅ? ምንድን ነው ሰውነትህን እንዲህ የቀያየረው? በጊዜስ የተመለስከው ለምንድን ነው?'' በማለት ጠየቀው፡፡
በልጁ ትንሽዬ ልብ ውስጥ የአላህ ፍራቻ እያቆጠቆጠ ስለነበር እንደ በጋ ቅጠል ሁለመናውን አጠውልጎት እንዲህ አለ፡- “አባቴ ሆይ! ዛሬ መምህራችን አንድ የቁርዓን አንቀጽ አስተማሩን፡፡ እኔም ትርጉሙን ሳሰላስል እንዲህ ለመሆን በቃሁ። ''
“የትኛው አንቀጽ ነው የእኔ ልጅ?” አለ አባት፡፡ ልጁ የሚከተለውን አንቀጽ አነበበ፡-
{ فَكَیۡفَ تَتَّقُونَ إِن كَفَرۡتُمۡ یَوۡمࣰا یَجۡعَلُ ٱلۡوِلۡدَ ٰنَ شِیبًا }
ብትክዱ ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገውን ቀን (ቅጣት) እንዴት ትጠበቃላችሁ፡፡(አል ሙዘሚል 17)
ቆየት ብሎ ይህ ልጅ በዚህ የቁርአን አያ ትርጉም ምክንያት ታመመ:: የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ከቆየ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሞተ😔፡፡ አባትዬው በዚህ ክስተት ክፉኛ ነበር የተናጠው። በተደጋጋሚ ወደ ልጁ መቃበር እየሄደ በማልቀስ ለራሱ እንዲህ ይል ነበር-
"አቡበከር ሆይ! ልጅህ ቁርዓንን አንብቦ መልዕክቱን በመገንዘብ አላህን በመፍራት ነፍሱን አስረከበ፡፡ ይሁን እንጂ አንተ ግን ይህን ሁሉ ዘመን ስታነበበው ብትቆይም የልጅህን ያክል እንኳን አላህን ልትፈራ አልቻልክም እያለ ሁሌ ራሱን ይወቅስ ነበር
ምን ያህሎቻችን ነን የቁርአን አያ ትርጉም አዉቀን እራሳችንን የምንፈትሸዉ⁉️
ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6106