tgoop.com/Islam_and_Science/6089
Last Update:
1979 ሀረም ላይ ምን ተፈጠረ?
ክፍል 3
«ሀይአት ኪባረል ዑለማ» የሰዑዲ ፈታዋ ምክር ቤት በሀረም ከባቢ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲደረግ የሚፈቅድ ፈታዋ ሲሰጥ እንዲህ ቀላል አልነበረም። ምክኒያቱም ከአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) የተገኙ ትክክለኛ እና ግልፅ ሀዲሶች በሀረም ዙርያ ወታደራዊ እርምጃዎችን ይከለክላሉ። ስለዚህ ፈታዋቸው ከትችት የነፃም ሆነ የዓለም ዑለማዎችን በ2 ጎራ ከፍሎ ከማነታረክ ሊተርፍ አይችልም።
ዞሮዞሮ ፈታዋው ከተሰጠም በኋላ በትንሽ ሰብአዊ ኪሳራ ሀረምን ከእገታ የማዳኑን ሀላፍትና ማን ይውሰድ የሚለው ለንጉስ ኻሊድ ሌላ ራስ ምታት ሆኖበታል። የሀገሬው ፖሊስ የሞከራቸውም ፤ የሀገሬው ሰራዊት አሳክቼዋለው የሚለው አንድም ፍሬ ነገር ማቅረብ አልቻለም።
ስለዚህ ከውጪ ሀገር ኮማንዶዎች ይህንን ተግባር አቀላጥፎ የሚጨርስ መረጣ በጠረጴዛ ዙርያ ሲጣል ሲነሳ ከቆየ በኋላ የፈረንሳይ ኮማንዶ ተመረጠ። ኮማንዶው አለኝ የሚለውን ዘመናዊ መሳሪያ አንግቦ የሱዑዲያ ምድር ከተመ። ግን ስራውን ገና ሳይጀምር ከበድ ያለ ፈተና ገጠመው። የሀረም ክልል ውስጥ ሙስሊም ያልሆኑ ሰራዊቶች እንዴት ሊገቡ ይፈቀድላቸዋል? የሚል። ጥያቄው በምን መልኩ እንደተፈታ ብዙ መላምቶች ቢሰነዘሩም የፈረንሳይ ኮማንዲ ቡድን ሀረምን ከእገታ በማስለቀቁ ላይ የአምበሳውን ድርሻ እንደወሰደ የትኛውም ተራኪ የማይክደው እውነታ ነው።
ኮማንዶው ሀረም የገባው ሸሀዳ ይዞ ነው ፤ ኮማንዶው አመራር እና ሎጅስቲክ ላይ ብቻ ነው የተሳተፈው እና ሌሎችም ተብሏል።
ኮማንዶው በሀረም የመሬት ስር መንገድ በመግባት መርዛማ ጪሶችን ወደ ሀረም ክልል አስወነጨፈ። የሀረም እንግዶች በከባድ ሳል እየተጨነቁ የድረሱልን ሰቆቃ ድምፅ ያሰማሉ። በጪሱ ነቦልቧል የተጨነቀው ሀረም በላዩ ላይ የጥይት እሩምታ ታከለበት። ሰላማዊው ክልል የጦር አውድማ ሆነ።
BY ISLAMIC SCHOOL

Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6089