tgoop.com/Islam_and_Science/6054
Last Update:
🔰 #እየሩስ_አሌምን_ለገና_ስጦታ_አድርስልኝ 🔰
#የመጨረሻዉ_ክፍል
✍ አሚር ሰይድ
#በሙስሊሙ_ወጣት_ላይ_የስነምግባር_ብልሹነትን_ማስፋፋት
የሙስሊም ወጣቶችን ባሕሪ ለማበላሸት አውሮፓውያን እና አሜሪካዉያን በህብረት እኢአ ከ200 ጀምሮ 57 ቢሊየን ዶላር መድበዋል፡፡
✏️ከዚህ ውስጥ 12 ቢሊየን ዶላር ስሜት ማራኪ ስልቶች ለመጠቀም፣
✏️ 20 ቢሊየን ዶላር የቪዲዮ ፈልም ማምረቻ!
✏️11 ቢሊየን ዶላር ቅምጥ ሴቶችን ማዘጋጃ፣
✏️ 7.5 ቢሊየን ዶላር የብልግና መጽሄቶች ማዘጋጀት እና ማሰራጨት፣
✏️ አምስት ቢሊደን ዶላር መሽታ ቤት ማዘጋጀት
✏️2.5 ቢሊየን ዶላር የብልግና ማሰራጫ ጣቢያዎች
✏️ 1.5 ቢሊየን ዶላር ሲዲዎች ማዘጋጃ፣
✏️ 1 ቢሊየን ዶላር የስልከ መስሮች ማዘጋጃ፣
✏️ 1.5 ቢሊየን ዶላር የተለያዩ የወሲብ ቀስቃሽ መልእክቶች ማዘጋጃ ላይ ይውላል፡፡
#የሙስሊሙን_ህብረተሰብ_የሚያበላሹ_የብዙሀን_መገናኛዎች
ሙስሊሙ ህብረተሰብ በተለይ ወጣቱ ከእስልምና እንዲዘናጋ የተሊያዩ የብዙሃን መገናኛ ጣቢያዎችም ፈጥረዋል፡፡
አሜሪካ በሚገኘው ሆሊውድ ማእከል እስከዛሬ ድረስ ከዘጠኝ መቶ ያላነሱ ዓረብ እና ሙስሊሞችን እሚያንቋሸሹ ፊልሞች ተሠርተዋል፡፡ በ1942 የተመሰረተው የአሜሪካ ድምፅ የሬድዮ ጣቢያ የዓረብኛ ቋንቋን ሶስተኛ ቋንቋ አድርጎ በመጠቀም ረጅም ሰአትን ባሕል በራዥ እምነት ከላሽ ፕሮግራሞችን ያቀርባል፡፡
☞ ሳዋ የሚባለው የሬድዮ ጣቢያ ዝግጅቱም ከ30 አመት በታች ላሉ ሙስሊም ወጣቶች የተዘጋጀ ነዉ፡፡በስርጭቱም 80% ዘፈንና ድራማ ይጠቀማል፡፡ የሚጠቀምባቸውም የአረብኛ ቋንቋ ዘዬዎች የግብፅን የዒራቅን የሱዳንን የገልፎችን አካባቢ የዓረብኛ ቋንቋ ነው።
🟢 #ሐይ... በመባል የምትታወቀው ወርሃዊ መፅሄት
ለተመሳሳይ ዓላማ የተመሰረተች ናት፡፡ የተመደበላትም ዓመታዊ በጀት በአሁኑ 4 ሚሊየን ዶላር ደርሶዋል፡፡ 70 ገጽ ያላት ሲሆን ከ28 እስከ 35 እድሜ ላላቸው ሙስሊም ወጣቶችን ስሜት የሚቀሰቅሱ ፁሁፎችን ታወጣለች፡፡ በአምዱዋም ጭፈራን፣ ስፖርትን አቅፋለች፡፡ በአንድ ጊዜ ከ50 ሺ ያላነሰ ኮፒ ታትሞ በነፃ ለሙስሊም ወጣቶች እንድትደርስ ይደረጋል፡፡
🟢 #አልሁራ_ቲቪ
እኤአ በ2004 የተመሰረተ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር በቀን 14 ሰዓት ብቻ ስርጭት ነበረው፡፡ ይህንን በማሳደግ ወደ 24 ሰአት ስርጭት እንዲኖረው ተደረገ፡፡ በዚህ ጣቢያ ውስጥ ከ200 ያላነሱ ዓረብኛ ተናጋሪ ወጣቶች እንዲሳተፉ ተደረገ፡፡ በዓመት 63 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተመድቦለታል፡፡ ስርጭቱም በዓረቡ ዓለም እና በሙስሊሙ ዓለም እንዲደርስ ተደርጓል፡፡ በዒራቅ ለተከፈተው ቅርንጫፍ 40 ሚሊየን ዶላር በጀት ተመድቦለታል፡፡
ከላይ የዘረዘርናቸው የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ሁሉም እሚያተኩሩት አሜሪካን በማሞገስና በማወደስ፣ እስልምና እና ሙስሊሞችን ማንቋሸሽ ነው::
ሙስሊሞች ማለት ሰይፈኞች፣ አሸባሪዎች፣ ተዋጊዎች፣ ፅንፈኞች፣ ዘራፊዎች፣ ሴቶችን በዳዮች፣ አውሮፕላን የሚያጋዩ፣ አይሁዶችን ባህር ውስጥ ለመወርወር ያቀዱ ተደርገው በድራማዎችና ፊልሞች ሲሳሉ፤
ዓረብ ማለት ደግሞ ማሰብ የማይችል፣ የመጠጥ ሱሰኛ፣ ከነዳጅ ገቢ ባገኘው ገቢ በዶላር የተሞላ፣ እውቀት አልባ የሆነ ጨካኝ፣ ራሱን የሚወድ ነጭ ሴቶችን እሚያድን ማለት ነው የሚለውን ነው የሚያንፀባርቁት፡፡
>> በተጨማሪም _ በአውሮፓ _ እና _ በአሜሪካ _ ለሚመረቱ የብልግና ፊልሞች በዓረቡ ዓለም የሚያሰራጩ አጋሮች በመፍጠር ከ510 ያላነሱ የዘፈን ቻናሎች በአረቡ ዓለም እንዲሰራጩ አደረጉ፡፡ ለዚህም የተመደበው በጀት ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ሆኖዋል፡፡ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ያሉትን ዘመን ያፈራቸውን ዘፋኞች እስፖርተኞች ጨፋሪዎችን በመጋበዝ በተለያዩ ዓረብ ከተማዎች መሸታ ቤቶች እንዲከፈቱ አደረጉ፡፡
✍ አሜሪካ በአፍጋኒስታን ላይ ባደረገችው ወረራ እና ዘመቻ የተቃውሞ ሰልፍ የወጣው ወጣቱ ሙስሊም ከ4 ሚሊየን አይበልጥም #ዲያና_ከራዞን የምትባለውን ዘፋኝ ለመቀበል ከ50 ሚሊየን ያላነሰ ሙስሊም ወጣት ወጥቷል፡፡ ልክ ህንድን ለከፈተው ሙሀመድ አልቃሲም
ወይም ቁስጠንጢኒያን ለከፈተው ሙሀመድ አልፋቲህ አቀባበል የሚያደርጉ ነበር የሚመስለው፡፡
☞ 78% ዘፈንን የሚመለከት
☞7% የሀይማኖት ቻናሎችን የሚመለከት
☞ 80% ጭፈራን ስፖርትን የሚመለከት ሆኖዋል፡፡ ቀደም ሲል የረጅም ጊዜ የሙስሊም ታሪክ ፈጣሪን እሚያስከፋ አንድ ወንጀል ብቻ ነበር የሚታየው::
በአሁኑ ጊዜ ግን የተበላሸ ወጣት፣ የተበላሸ ህብረተሰብ፣ የተበላሸ ፖለቲካ፣ የተበላሸ ኢኮኖሚ፣ የተበላሸ ማህበራዊ ኑሮ ሁሉም የተበላሸ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለፈጣሪ አጋር መፍጠር፣ ጥንቆላ፣ በዲን ላይ ፈጠራ፣ ኹራፋት ተንሰራፍቶ እናገኛለን፡፡
🟢#የዓረቡ_አለም_ወጣት_ሙስሊሙ_ስለ_ትምህርት_ያለው_ግንዛቤ
በአረቡ ዓለም 325 ሚሊየን አረብ ሲኖር የዩንቨርስቲዎቻቸው ብዛት ግን 400 ብቻ ነው:: 300 ሚሊየን የሚሆኑ አሜሪካውያን 3400 ዩኒቨርስቲ አላቸው::
130 ሺ የሚሆኑ የሳውዲ ወጣቶች በተለያዩ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ዘመናዊ እውቀት ለመቅሰም በእስኮላርሺፕ ሽፋን ተሳትፈው ይገኛሉ፡፡ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች እውቀትን ከማስተማር ይልቅ ትኩረት የሚያደርጉት የሚከፍሉትን ገንዘብ ግምት በማስገባት በነፃነት እንዲማግጡ ይለቋቸዋል፡፡
✍ የሳውዲ ወጣቶች ለትምህርት በሚል በአሜሪካ ዩንቨርስቲ ውስጥ በአመት ከአርባ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ያወጣሉ፡፡ተማሪዎቹ ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በከፍተኛ ማእረግ እንደተመረቁ ተደርገው ይሸኛሉ፡፡ ምክኒያቱም ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በከፍተኛ እርከን እና ሀላፊነት ስለሚመደቡ ተገዢነታቸውም ለቆዩበት ሀገር እና ዩኒቨርስቲ ይሆናል፡፡
የገልፍ ነዋሪዎች ለልጆቻቸው አረብኛ ቋንቋን ከመማር ይልቅ እንግሊዘኛን መማር ያስቀድማሉ፡፡ በዚህም የተነሳ በየዓመቱ ልጆቻቸውን ወደ አውሮፓ ሀገራት በመላክ ከዛም የአውሮፓውያን ቤተሰቦች እንዲቀበሉዋቸው እና በቤታቸው እንዲያሳርፉዋቸው አስፈላጊውን ማረፊያ በማዘጋጀት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቻ የሚያናግሩዋቸው
ወጣት ሴቶችን በመመልመል ጓደኛቸው እንዲሆኑ አጋጣሚዎችን ያመቻቻሉ፡፡
ለዚህም ከፍተኛ ክፍያን ይጠይቃሉ እነኚህም፡፡ የሙስሊም ወጣት ቤተሰቦችም ክፍያውን ይፈፅማሉ፡፡ ያም ለጋ ሙስሊም ወጣት በቆይታው ቋንቋ መቅሰም ብቻ ሳይሆን ካረፈባቸው ቤተሰቦች ባህላቸውን ወጋቸውን ልምዳቸውን ብልግናውንም ጭምር እንዲያውም አንዳንዶቹ እምነታቸውን ሳይቀር ቀስመው ይመለሳሉ፡፡ እስልምና ሀይማኖቱን እና ቅርሱን ታሪኩን ያፍሩበታል፡፡
ምዕራባዊያን በቢሊየን የሚመደብ ብር በጅተዉ እንዲበላሹ ጀለብያ ለብሰዉ አምሮባቸዉ ዉስጣቸዉ ግን ለሙስሊም የማይጠቅም የማይጎዳ ትዉልድ ሁነዋል፡፡
⚡️⚡️ዛሬም በእኛ ኢትዮጲያ አረቦች ከዲናቸዉ እንዳስወጧቸዉ በእኛም አሁን ባለንበት ዘመን እየተንሸራተትን እንገኛለን👇👇
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6054