tgoop.com/Islam_and_Science/6048
Last Update:
አሜሪካ በሁለቱም የዓለም ጦርነቶች ባደረገቻቸው ተሳትፎዎች ሁለቱም ጦርነቶች ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል፡፡ የዚህ አስረጂ እንዲህ ነው፡፡ ሁለቱም ጦርነቶች በዋናነት የአዉሮፓዊያን ጦርነቶች ናቸው:: አሜሪካ እንደሶስተኛ ወገን ዳኛ ሆና እንድትቀርብ ነበር የተፈለገው:: የመጀመሪያው ጦርነት ላይ በቀጥታ እርዳታዋን በማግኘታቸው እንግሊዝና አጋሮቿ ለድል በቅተዋል፡፡ በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ደግሞ ራሷን ወደ ኃያልነት ጎራ ማሳደግ ችላለች፡፡
ዛሬም ስለመካለኛው ምስራቅ ቀውስ ወይም ስለእየሩሳሌም ከተማ ቅድስና የሚሰማንን ስናስብ ማስተዋል የሚገቡን ጉዳዮች አሉ፡፡ ከተማዋ የሶስት ታላላቅ ኃይማኖቶች ማዕከል ናት፡፡ ይሁን እንጂ ከሙስሊሞች አስተዳደር ተወስዳ ወደ አይሁዶች መንግስት እንድትገባ በተደረገውና በሚደረገው ጥረት ላይ በዓለም ያሉ አይሁዶች፣ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች አመለካት ብዙ ያልጠሩ መረጃዎችን ያማከሉ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል፡፡ በቅርቡ ዶናልድ ትራምፕ እየሩስአሌም የአይሁዶች ከተማ እንድትሆን የነበረውን አቋም ሲናገር ብዙ ከርስቲያኖች ደግፈዉታል፡፡ እውን ሊደግፉት ይገባ ነበር?
የምናየው ዓለም ብዙ ያልተነገሩ ታሪኮች ዉጤት ሆኗል፡፡ ከእውነቱ ይልቅ ፖለቲካዊ ፈጠራዎች በዓለም ማህበረሰብ ላይ ፍጹም እውነት መስለው ቀርበዋል፡፡ በእየሩሳሌም አስተዳደር ሙስሊሞች፣ አይሁዶችና ክርስቲያኖች በአንድነት በየራሳቸው ቅዱስ መንደሮች እንደየእምነቶቻቸው ይኖሩ የነበረው ሙስሊሞች ባስተዳደሩባቸው ዘመናት እንደነበር ብዙ ማሳያዎች ማቅረብ ይቻላል፡፡
በሌላም በኩል ዛሬ የተመሰረተው የአይሁዶች ከተማ ከሙስሊሞች በመነጠቁ አብዛኛው የዓለም (አይሁድና ክርስቲያን) ማህበረሰብ ከተማዋ ከአህዛቦች ነፃ
እንደወጣች ያስባሉ፡፡ ሙስሊሞች በተለይ ከ1970ዎቹ ወዲህ በዓለም የተሳሉበት ሁኔታ አሉታዊ ጭብጥ ያዘለ በመሆኑ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች በየቀኑ ያላቸው ጥላቻ እየጨመረ መጥቷል፡፡
ኢስላሞፎቢያ የተሰኘ አመለካከትም ተወልዷል፡፡ ከ9ኛው ክፍለ ዘመን ማበቂያ ጀምሮ አንቲሴሜቲዝም የተሰኘ አይሁዶችን የመጥላት አባዜ ተፈጥሮ እንደነበረው ይኼው ከአንድ ክፍለ ዘመን በኋላ አስተሳሰቡ በሙስሊሞች ላይ አማከለ፡፡ ባንፃሩ ከዚያው ከ1970 በኋላ የክርስቲያን መብትና በእግዚያብሄር የተመረጠ ህዝብ የሚል አስተሳሰብ በአሜረካ ወንጌላዊ ጽዮናዊያን ተጀመረ። በሙስሊሞች ላይ የተወለደውን ጥላቻ ጣሪያ ለማስነካት የነዚህ ቡድኖች ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡ በእስልምና የ14 ክፍለ ዘመን ታሪክ ያልታየ ፕሮፖጋንዳ በሰፈው ተሰራጨ::
ዛሬ ያለውን በሙስሊሙና የክርስትና ሀገራት መሃል የተፈጠረ የግንኙነት መሻከር ምን እንዳመጣው ለማወቅ የምናነሳቸው ጉዳዮች ቢኖሩም ከ1970ዎቹ ወዲህ የምዕራቡ ዓለም ኃያል ሀገራት የተከተሉትን የዉጪ ጉዳይ ፖሊሲ ተከትሎ የተፈጠሩ የሚዲያና የአስተሳሰብ ተዛንፎሾች ማየት ቁልፍ ሚስጢሮችን ይገልጣል፡፡ ወደ ኋለኛው ምዕራፎቻችን የምናያቸው ተጨባጭ ማሳያዎች ስላሉን ይህም ጥናት የሚሰጠው ጠቃሚ መረጃ ይኖራል፡፡ የእስራኤል ምስረታም ሆነ የእየሩሳሌም ዉሳኔ ፍፁም ከኃይማኖት ፍላጎት ዉጪ መሆኑን ባጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡ ምከኒያታችን አንድ ነው፡፡ አንድ አይና (አክራሪ የአንድ ክንፍ) አመለካከቶች በስፋት ከተስፋፉበት ዘመን ላይ እንደመሆናችን ያልተነገሩ ሌላኛ ከንፎችን ማሳየት የሚኖረውን ዋጋ ማሰብ አይከብድም፡፡
እስራላዊ ፕሮፌሰር አቪ ሽሌይም እንዳሉት“የእስራኤል ምስረታ የእንግሊዝ ኢምፓየር የሀኛው ክፍለ ዘመን ፍጹም ስኬታማ የዉጪ ጉዳይ ፖሊሲ ዉጤት ነው፤ በሌላ በኩል የአይሁዶችን የቆየ ዓላማቸውን የማሳመን ኪሂሎትም ማሳያ ነው፡፡" ብለዋል፡፡
በቀጣይ ክፍል #አሜሪካ_ለምን_እስራኤልን_ለፓለቲካዋ_መጠቀም_ፈለገች??? በኢዝኒላህ ነገ ይጠብቁኝ...
#ክፍል ➎
ይቀጥላል......
ለአስተያየት🔽
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6048