tgoop.com/Islam_and_Science/6041
Last Update:
🔰 #እየሩስ_አሌምን_ለገና_ስጦታ_አድርስልኝ 🔰
#ክፍል ☞ሁለት 2⃣
✍ አሚር ሰይድ
ሱልጣኑን መጣል ስለሚቀድም ብቻ ተግባብተው አለፉ፡፡የኦቶማን ኢምፓየር በተለይ በዓረቦች አመፅ መነሳት ፍጹም እንደሚወድቅ የአዉሮፓ ሹማምንት አምነዋል፡፡ በጋሊፖሊ የባህር ዳርቻ ሁለት ጊዜ የተደረገው የወረራ ሙከራ በሽንፈት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ በዓረብ በኩል ያለው ሁኔታ ግን በተቃራኒው ለአዉሮፓዊያን እየሰመረላቸው ነው:: የዓረቦችን አመፅ በአግባቡ ተጠቅመው ሱልጣኔቱን ድባቅ መምታቸውን ቀጥለዋል፡፡
1916 ፀኃያማው የበጋ ወቅት የድል ዜና ፈጥሮላቸዋል፡፡ እንግሊዝ በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ ሰር ማርከ ስካይስ የተባለ ወኪሏ ከጦርነቱ በኋላ ዓረቢያን ከሌሎች ኃያል ቡድኖቿ ጋር በምትቃረጥበት ሁኔታ ለመማከር ኃላፊነት ወሰደ፡፡ በዚህም ከፈረንሳዩ ዲፕሎማት ፒኮት ጋር በሚስጢር ተገናኝተው በጥንቃቄ ይወያዩ ጀመር፡፡ በዓረቢያ ነፃ የቅኝ ግዛት መሬት የመገኘቱ ነገር እውነት መሆኑ እርግጠኞች ሆነዋል፡፡
ስለዚህ ሁለቱም በግላቸው የደረሰብትን ጥናት ታከው የዓረቦችን ምድር በራሳቸው አስምረው ተካፈሉት፡፡ ራሺያም የምድባቸው አካል ስለነበረች ድርሻ ተቸራት፡፡ በስምምነቱ መሰረት
☞ እንግሊዝ ዒራቅና ሂጃዝን
☞ ፈረንሳይ ታላቋን ሶሪያ ለመዉሰድ ሲመዳደቡ
☞ለራሺያ ደግሞ ለብዙ መቶ አመታት የናፈቀችውን ኢስታንቡል ትወስድ ዘንድ የሚገልፅ ድብቅ ዉል ተፈራረሙ::
ይህ ስምምነት እንግሊዝ ቀደም ብላ ከዓረቡ የሂጃዝ መሪ ሸሪፍ ሁሴን ካደረችው ስምምነት ጋር ይጋጫል፡፡ ምከንያቱም ከሸሪፉ ጋር ያደረገችው ስምምነት ሙሉ ዓረቢያን በነፃነት እንዲመራ የምታመቻችለት መሆኑን የሚገልፅ ነው:: የዓረቦችም ዓመፅ ሰፊ የዓረብ መንግስት ለመፍጠር ከማለም የመነጨ ነው:: ከላይ ያየነው የዲፕሎማቶች ስምምነት ግን አካባቢውን እንዴት መከፋፈል እንደሚችሉ የሚያሳይ ነው፡፡ አዉሮፓዊያኑ ያደረጉት ዓረቡን የመከፋፈል ዉል #የስካይስ_ፒኮት_ሚስጢራዊ_ዉል ተብሎ ይጠራል፡፡ ባጭሩ የስካይስ ፒኮት ስምምነትም ይባላል፡፡
ይህን የሚስጢር ሴራ አረቦች በጭራሽ አላወቁም ነበር
በዚያው ዓመት በሰኔ ወር 1916 የዓረቦች ዓመፅ በይፋ ታወጀ፡፡ በኦቶማን ሱልጣን ስር የነበሩ የዓረብ ቀጠናዎችን ወረሩ፡፡ ጦሩ የሸሪፍ ሁሴንና የልጁ የፈይሰል ጦሮች ናቸው፡፡ እንግሊዛዊያን የጦር መኮንኖች ይህን ጥቃት ለዓረቦች መርጠዉላቸው ነው:: በነሱ እምነት ዓረቦች በቀጠናቸው ሲያምፁ የኦቶማን ጦር ይከፋፈላል፡፡ ሙሉ ኃይሉን ተጠቅሞ እንግሊዝ ከግብፅ በመነሳት ልትከፍት ያሰበችውን ወረራ አይዋጋም፡ ፡ ከዓረቦች የሚጠብቁት ይህን ነበር፡፡ እንደጠበቁት ሙስሊም ዓረቦች በሙስሊም ሱልጣናቸው ላይ አምፀው ጦር እነሱ፡፡
>>>>> ዓረቦች ከጥንት ጀምሮ ፈታኝ በሆኑ አመፅ፣ ሙስናና የእርስ በርስ ጥል ይታወቃል፡፡ ከነብዩ ሙሃመድ (ሰዐወ) መምጣት በፊት ያለውን ማየት እንችላለን፡፡ ከእስልምና ማበብ በኋላ ደግሞ በአንደኛው ዓለም ጦርነት የሆነውን ማስተዋል እንችላለን፡፡ ሁለቱ ዘመናት የሚያመሳስላቸው ብዙ ከስተት አለ፡፡ ሙስና፣ ዓመፅና ለጠላት ደጋፊ ሆኖ የግል ጥቅምን ማሳዳድ፡፡
የእንግሊዝ ደጋፊ ሆነው በሱልጣኑ ላይ ጦር የከፈቱት በራሳቸው በእንግሊዝ በቂ ድጋፍና ስልጠና መስጠቷ እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው፡፡ የዓረብ መንግስት የመፍጠር ጥማቸው ጣሪያ ስለነካ ከእንግሊዝ ወታደሮች እስኪያገኙ አልጠበቁም:: በቀጥታ ወረራቸውን ጀመሩ:: እንግሊዝ ከዚህ በላይ ስለማትጠብቅ ለዕዋቂው ጀንራሏ አርበርድ ሙሪ ከግብፅ ወደ ሶሪያ የሚወስደው የአቶማን ክፍል ለማጥቃት ለመቆጣጠር ጦሯን እንቀሳቀሰች፡፡ ባልተጠበቀው የዓረቦች ወረራ የኦቶማን ጦር በየአቅጣጫዉ ተከፋፈለ፡፡
ሱልጣኑ ከሲናይ ሽንፈት በኋላ ዳግም በጠላት ወረራ ፍጥጫ ዉስጥ ገባ
የዓረቦችን አመፅ ጠብቆ በግብፅ የስዊዝ ቦይን አቋርጦ ፍልስጤም የገባው የጀነራል አርቸበርድ ሙሪ ጦር የኦቶማንን ጦር ድባቅ ለመምታት ጥሩ ሁኔታዎኛ ተመቻቹለት፡፡ ዓረቦች በከፈቱት ወረራ የአቶማን ኃይል ተዳከመ፡፡ የሂጃዝ የባቡር መስመርና የጅዳ ወደብ በቁጥጥራቸው ስር ገባ፡፡
የአርቸቦርድ ሙሪ ጦር በሙሉ ኃይሉ ተጠናክሮ ፍልስጤም ላይ ወረራ ከፈተ። በጋሊፖሊ ያጡት ድል በዚህኛው ጦር ፍፁም ይቅርታ አያገኝም፡፡ ማሸንፍ ብቻ ነዉ ምርጫቸው:: በአዉሮፓ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ሁለት አመት ቢያልፈውም ለእንግሊዝ የምታስበውን ድል አላጎናፀፋትም፡፡ የጀርመን ኃይል ጠንካራ ሆኖባታል። ያላት አማራጭ ደካማ ግንባር የተባለውን የምስራቅ ቀጠና ወይም የኦቶማን ኺላፉ ማፈራርስ ነበር፡፡ ይህን በማድረጓ በአዉሮፓ ብርቱ ሆኖ ድል እየነሳት የሚገኘውን የጀርመን ጦር ማዳከም ትችላለች፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ያቀደችውን የቅኝ ግዛት ፕሮጀከትም በቀላሉ ትፈፅማለች፡፡
ይሁን በአርቸቦርድ ሙሪ የተማራውም የእንግሊዝ ጦር ዉጤት ማምጣት ሳይችል ቀረ፡፡ የቱርክ ወታደሮች የበላይነቱን ያዙባቸው፡፡ በዚህ የተበሳጩት የለንደን አለቆች ወዲያው ጀነራሉን አስወግደው በአረመኔነትና በበሳል የጦር አመራሩ የሚታወቀውን ኤድመንድ አለንቢ ሾሙ፡፡ የጦርነት መዘወርም ወዲያው ተቀየረ፡፡ ፍልስጤምን በመዉጋት በቀጥታ ወደ መሃል ሶሪያ ለማቅናት ዘመቻው በከፍተኛ ዝግጅት ቀጠለ፡፡
ጋዛም እንደጋሊፖሊ ፈታኝ ጦርነት ውስጥ ወደቀች፡፡ የእንግሊዝ ወታደሮችና ዘመናዊ መሳሪያዎች በከተማዋ ላይ የእሳት ጉም አጎሙባት፡፡ ለዘጠኝ ወራት ያህል የፈጀ ከባድ ጦርነትም ሆነ፡፡ የቱርከ ወታደሮች የትግል ፅናትና ቁርጠኝነት የእንግሊዝን ሰራዊት አርበደበደ፡፡ ለአንድ አመት ሶስት ወራት የቀሩት የጦርነት ጊዜም አሳለፈ፡፡ በመጨረሻ ግን በቂ መሳሪያ ማግኘት ተሳነው፡፡ ዘመናዊውን የእንግሊዝ ጦር የሚመከቱ መሳሪያዎች ማግኘት አልቻለም፡፡ከጠቀሱት ወራት በኋላ የአቶማን ምስራቃዊ ድንበር ተደረመሰ፡፡
#ጋዛ_በጠላት_እጅ_ወደቀች፡፡ ይኼው ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ዛሬም ድረስ ከፉ መከራ እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ጀነራል ኤድመንድ አለንቢና የድል ጮቤ ረገጣ!
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ለጀነራል አለንቢ ከባድ መልዕክት ላከ #እየሩስአለምን_ለገና_ስጦታ_አድርስልኝ
በክርስትና እምነት ተከታዮች የላቀ ቅድስና ያለው ስፍራ ነው ድል የተገኘበት፡፡ወደ ቅድስት እየሩሳሌም ዘልቆ ለመግባት የሚያስችለውን የጋዛ ድል በቀላሉ አላለፉትም፡፡ እንግሊዝና ወዳጆቿ በትልቅ ሀሴት ዘምረውለታል፡፡ አለንቢ ግን ስጋት አለው፡፡ኃያሉ የቱርክ ጦር አንዳች የመልሶ ማጥቃት ከፈፀመ ሰራዊቱ አይሆኑ ቅጣት ተቀቶ ወደመጣበት እንደሚመለስ ገብቶታል፡፡ የቱርክ ወታደሮች ሞትን አይፈሩም፡፡ ለመሞትም ነው የሚዋጉት፡፡ ለዚህ ነው የተለየ ጀግንነት የሚታይባቸው:: ያጡት ወኔ ሳይሆን በቂ መሳሪያና ሰራዊት ነበር፡፡
አለንቢ ውጊያውን ማቆም አልፈለገም፡፡ ቀጠለ፡፡ ከጋዛ ድል በኋላ በቀጥታ ፊቱን ወደ ቁድስ (እየሩሳሌም) አዞረ፡፡ከለንደን ቤተ መንግስት ለጀነራል ኤድመንድ አለንቢ የተላከ ጠንካራ መልከት እየሩሳሌምን ለገና በዓል ሰጦታ እንዲያደርስ የሚያዝ ነበር፡፡ በእንግሊዛዊያን ባህል ክርስትና ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ከሺህ አመት በፊት ጀምሮ የእየሩሳሌም ጠበቃ ለመሆን እንደሌሎች አዉሮፓዊያን ሲታገሉ ኖረዋል፡፡ አሁን ደሞ እድል ቀንቷቸው ብቻቸውን ባለድል ሊሆኑ በብርቱው ጀነራል አለንቢ ጦራቸው ከጫፍ ደርሷል።👇👇
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6041