tgoop.com/Islam_and_Science/6030
Last Update:
ከመፅሀፍ ገፅ ➒
#የተበደለ_ሰው_ዱዓ_መሬት_ጠብ_አይልም
✍አሚር ሰይድ
ነቢዩ ሰዐወ በእርሱና በአላህ መሃከል ምንም ዓይነት ግርዶ የለምና የተበደለን ሰው ዱዓ ፍሩ” ማለታቸውን ኢብኑ ዐብባስ አውርተዋል፡፡ ስለዚህ ሰዎች ሲበድሉን መፍትሔው መበሳጨት ወይም ለሌሎች ሰዎች መናገር ሳይሆን የአላህን እገዛ በነርሱ ላይ መሻት ነዉ፡፡
አርዋ ቢንት ዑወይስ ከእርሻ መሬቷ የተወሰነው በሰዒድ ኢብኑ ዓምር ኢብኑ ኑፈይል ተወስዶብኛል በማለት ለአሚር ሙሐመድ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ ሐዝም አቤቱታ አቀረበች፡በአላህ ይሁንብኝ የነጠቀኝን መሬት በአስቸኳይ የማይመልስልኝ ከሆነ በነቢዩ ሰዐወ መስጂድ ውስጥ ጀመዓው ፊት አዋርደዋለው በማለትም ዛተች፡፡ ሙሐመድ ግን- "እባክሽን የአላህ መልዕክተኛ ባልደረባ የሆኑትን (ሰዒድ ኢብኑ ዐምር) አትጉጂኣቸው፡፡ ሰዒድ የሚበድልሽ ወይም መብትሽንም የሚነካ ሰው አይደለም የሚል ምክር ሰጧት፡፡ አርዋ በዚህ ምላሽ ባለመርካቷ ወደ ዑመይራህ እና ዐብደላህ ኢብኑ ሰላማህ በመሄድ ተመሣሣይ አቤቱታና ዛቻ ሰነዘረች: ዑመይራና ዐብደላህ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ሰዒድ ዘንድ ሄዱ፡፡ ሰዒድ በእርሻ ቦታው ላይ ሆነው ወደሳቸው የመጡትን ሁለት ሰዎች ሲመለከቱ- 'ምን ጉዳይ ገጥሞኣችሁ ነው ወደኔ ልትመጡ የቻላችሁት?" በማለት ሲጠይቁ
....አርዋ ስለሳቸው የምታቀርበውን ክስ ለማጣራት መሆኑን ነገሯቸው፡፡ ሰዒድ ኢብኑ ዓምር በሰሙት ነገር በማዘን “የአላህ መልዕክተኛ ሰዐወ የሌላ ሰው ሐቅ የሆነችን የእጅ መዳፍ የምታክል መሬት እንኳን ብትሆን በሕገ-ወጥ መንገድ የወሰደ ሰው በቂያማ ቀን ከሰባቱ መሬቶች የዚያችን ቦታ የሚያክል ሸክም ይንጠለጠልበታል ማለታቸውን ስለሰማሁ ትምጣና የኔ ሐቅ ነው የምትለውን መሬት ትውሰድ” ካሉ በኋላ " #አላህ_ሆይ! ይህች ሴት በሐሰት ወንጅላኝ ከሆነ ሳትሞት የዓይኗን ብርሃን ነስተሃት የሞቷንም መንስዔ ዓይነስውርነቷ እንድታደርግ እጠይቅሃለሁ የሚል ዱዓ አደረጉ፡፡ ለሰዎቹም ያደረጉትን ዱዓ ለሴትየዋ እንዲነግሯት ጠየቁ።
.... አርዋ ያሸነፈች መስሏት ሰዒድ በመሬቱ ላይ የነበረን ጎጆ በማፍረስ በምትኩ የራሷን ቤት ሠራች። ይሁን እንጂ ይህን እንዳደረገች ብዙም ሳትቆይ ዓይኖቿ ጠፉ፡፡ የምትንቀሣቀሰውም በአገልጋይዋ ድጋፍ ሆነ፡፡
አንድ ቀን ውኃ ለመቅዳት ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ብቻዋን በመሄዷ ጉድጓዱ ውስጥ ገብታ ሕይወቷ አለፈ፡ የተበደለ ሰው ዱዓ በአላህ ዘንድ ይህን ያህል ተቀባይነት አለው፡፡
ሰዉን ከበደል አደራ አደራ እንጠንቀቅ!!!
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6030