tgoop.com/Islam_and_Science/6028
Last Update:
ከመፅሀፍ ገፅ ➑
#የኢብን_ቀይም_ወርቃማ_አባባሎች
✍አሚር ሰይድ
ኢብን ቀይም እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል- “አንድ የአላህ ባሪያ ከእንቅልፉ ሲነቃ ብቸኛው ምኞቱ አላህን ለማስደሰትና እርሱን ለመገዛት ከሆነ አላህ ወዲያው የዚህን ሰው ፍላጐቶች ሊያሟላለትና የሚያበሳጩትን ነገሮች ሊያስወግድለት ይወስናል። ይህ ብቻ አይደለም፨ አላህ የዚህ ሰው ልብ እርሱን ብቻ እንዲያፈቅር፣ ምላሱ እርሱን ብቻ እንዲዘክር፣ ሰውነቱ እርሱን ብቻ እንዲገዛ ያደርጋል፡
ባሪያው ሲነጋ ጭንቀቱ ሁሉ የዚህ ዓለም ጉዳይ ከሆነ አላህ የሰውየውን ጭንቀቶችና ሸክሞች ለራሱ (ለሰውየው) ይተወዋል። ልቡን በጭንቀት፣ ውሎውን በመከራና በብስጭት ይሞላል፡፡ ፍቅሩን ከዚህ ዓይነት ሰው ስለሚያርቀው የሰውየው ፍቅር ለምድራዊ ነገሮች ብቻ ይሆናል። ምላሱ ስለሌሎች ሰዎችና ሌሎች ነገሮች በማውራት ይገደባል። ሰውነቱ ያምጻል፡ ለተለያዩ ስሜቶችና ፍላጐቶች ተገዢ ይሆናል። ልፋቱ የአህያ ዓይነት ልፋት ይሆናል፡፡ ፊቱን ከአላህ ፍቅር፡ ዒባዳና
ታዛዥነት ያዞረ ሰው ደግሞ ሕይወቱ በምድራዊ ደስታዎችና ፈንጠዚያዎች፣ ለፍጡራን በመገዛትና በማጐብደድ የተሞላች ትሆናለች- አላህ ﷽ “አር-ረሕማንን ከማውሳት ራሱን ያገለለ ሰይጣንን የቅርብ ወዳጁ ይሆን ዘንድ እናዘጋጅለታለን" (ቁርኣን 43:36) ብሏልና፡፡
ኢብን ቀይም ይህ እንዳይከሰት የሚከተለውን እንድናደርግ ይመክሩናል- “በሦስት ሁኔታዎች ውስጥ ስትሆኑ ልቦቻችሁን ፈልጉ
➊ ቁርኣንን ስታደምጡ፣
➋ ዚክር ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል ስትቀመጡና
➌ ለብቻችሁ ስትሆኑ˚ በእነዚህ ሦስት ሁኔታዎች ውስጥ ሆናችሁ ልባችሁን ለመግዛት (ለመሰብሰብ) ካልቻላችሁ አላህ ልብ ይስጣችሁ*
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6028