tgoop.com/Islam_and_Science/6022
Last Update:
ከመፅሀፍ ገፅ ➎
#ሙእሚን_ከአንድ_ጉድጓድ_ሁለቴ_አይነደፍም
✍አሚር ሰይድ
የበድር ጦርነት ወቅት አቡ ዐዝዛህ አል-ጁመሂ የተባለ ባለቅኔ በምርኮነት ሙስሊሞች እጅ ወደቀ፡፡ አቡ ዐዝዛህ የግጥም ተሰጥኦውን ተጠቅሞ በሙስሊሞች ላይ ቁረይሾችን ሲያነሣሣ የነበረ ሰው ነበር። ከተማረክ በኋላ ወደ ነቢዩ ሙሐመድ ሰዐወ ዘንድ ቀርቦ “እኔ ብዙ የቤተሰብ አባላትን የማስተዳድር ደሃ ስለሆንኩ ምሕረት አድርገውልኝ ይልቀቁኝ, ይዘኑልኝ• በማለት ተማፀናቸው፡፡
ነቢዩም ሰዐወ አዝነውለት እንዲለቀቅ አዘዙ፡፡ ሌላ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ግን ከቁረይሽ መሪዎች አንዱ የሆኑት ሶፍዋን ኢብኑ ኡመያህ ለአቡ ዐዝዛህ 'ያ አቡ ዐዝዛህ አንተ ትልቅ የግጥም ችሎታ አለህ ይህን ችሎታህን ተጠቅመህ ተከታዮቻችን ሙስሊሞችን በመውጋት ላይ ጽናት እንዲኖራቸው ቀስቅስልን∶ በማለት ተማፀነው፡፡ አቡ ዐዝዛህ ነቢዩ ሰዐወ እሱን በመልቀቅ የዋሉለት ውለታ ስላለ ውለታቸውን ውድቅ በማድረግ የሚጐዳቸው ነገር ላይ ለመሳተፍ እንደማይፈልግ ቢነግረውም ሶፍዋን ኢብኑ ኡመያህ አቡ ዐዝዛህ በቅስቀሣው ዘመቻ የሚረዳቸው ከሆነ- “ከጦርነቱ በሰላም ከተመለስክ ከሃብቴ አካፍዬህ ሃብታም አደርገሃለሁ፡፡ በጦርነቱ ላይ ከተገደልክ ሴቶች ልጆችህን ከእኔ ሴቶች ልጆች ጋር የተቀማጠለ ኑሮ እንደማኖራቸው ቃል እገባልሃለሁ ብሎት አሳመነው፡ በተገባለት ቃል የጓጓው አቡ ዐዝዛህ ወደተባለው ጦርነት ሄደ። ለሁለተኛ ጊዜም የሙስሊሞች ምርኮ ሆነ፡፡ እንደ በፊቱም ነቢዩ ሰዐወ ፊት ቀርቦ ምሕረት እንዲያደርጉለት ጠየቃቸው፡፡ ነቢዩ ግን “በአላህ ይሁንብኝ ከእንግዲህ ጉንጮችህ ዳግም መካን አይነኩም። በርግጥ ሙሐመድን ሁለቴ አታለሃል፡፡ አንድ ሙእሚን ደግሞ ከአንድ ጉድጓድ ሁለቴ አይነደፍም፡ ካሉት በኋላ ወደ ዙበይር ዞር ብለው ዝብይር ሆይ! ይህን ሰው ሰይፈው አሉት፡፡ ሁለቴ ለማታለል የሞከረው አቡ ዐዝዛህ በገዛ ቅጥፈቱ ምክንያት ሕይወቱን አጣ፡፡
http://www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6022