tgoop.com/Islam_and_Science/6015
Last Update:
ከመፅሀፍ ገፅ ➋
#ነፍስያውን_ያሸነፈው_ወጣት
✍አሚር ሰይድ
ኢብን ሐዝም በጣም ይዋደዱ ስለነበሩ ሁለት ጓደኛሞች ታሪክ አስተላልፈውልናል፡፡ ሁለቱ ጓደኛሞች ከመዋደዳቸው የተነሣ በመካከላቸው ምንም ገደብ አልነበራቸውም። ከዕለታት አንድ ቀን ጓደኛሞቹ በአንደኛው ቤት ተቀምጠው ሳለ መሸ። ከጓደኛው ጋር ሲጫወት የነበረውና የቤቱ ባለቤት የሆነው በድንገት ለአስቸኳይ ሥራ ወጥቶ ለመመለስ ባለመቻሉ በቤቱ የቀረው ጓደኛው እዚያው የማደሩ ነገር እርግጥ ሆነ። በቤቱ ውስጥ እሱና የጓደኛው ሚስት ብቻ ቀሩ፡፡የሁለቱን ጥብቅ ጓደኝነት የማታውቀው ሚስት እኩለ ለሊት ሲደርስ ከባሏ ጓደኛ ጋር የመተኛት ፍላጐት ስላየለባት እሱ ወደተኛበት ክፍል ዘልቃ በመግባት እንዲገናኛት ወተወተችው፡ በመጀመሪያ ላይ የጠየቀችውን ለማድረግ ልቡ ቢነሣሣም የጓደኛው አመኔታ ሲታወሰው ስሜቱን ለመግታት ያልተለመደ እርምጃ ለመውሰድ ተነሣ፡፡ የጓደኛው ሚስት ስታስቸግረውና የእሱም ስሜት ሲነሣሣ አንደኛውን የእጁን ጣት አጠገቡ በነበረው ኩራዝ ላይ እያስቀመጠ “ከጀሃነም እሳት ይህ ይሻልሃል' ይል ጀመር፡፡ ሴትየዋ ይህንንም እያየች ወጣቱን ለወሲብ መፈለጓን አልተወችም፡፡ እሱም እሷ ባስቸገረችውና ስሜቱ በተቀሰቀሰበት ቅፅበት የእጆቹን ጣቶች በኩራዝ መለብለቡን ቀጠለ። ሲነጋ ከእጆቹ ጣቶች አንደኛው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኖ ነበር፡፡
ጓደኝነት ይህ ነው
join👇👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/6015