tgoop.com/Islam_and_Science/5977
Last Update:
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉 ዘጠኝ 9⃣
🟢 #ስንፈተ_ወሲብ(መሰናክለ ወሲብ)
መሰናክለ ወሲብ ማለት፡- ጤነኛ ሰዉ ሚስቱን መገናኘት አለመቻል ማለት ነዉ፡፡
መሰናክለ ወሲብ በወንዶች ላይ እንዴት ሊከሰት ይችላል?
በድግምት የተወከለዉ ጂኒ በወንዱ አእምሮ ዉስጥ ይቀመጣል፡፡
በተለይ ወሲባዊ መነሳሳትን በሚቆጣጠሩ እና ወሲባዊ መነሳሳትን በሚመለከት መልዕክት ወደ ወሲባዊ አካላት በሚልከዉ የአእምሮ ክፍል ዉስጥ ይቀመጣል፡፡
ጂኒዉ ይህ የአዕምሮ ክፍል መደበኛ ስራዉን እንዲያከናዉን ይተወዋል፡፡ ነገር ግን ሰዉዬዉ ሚስቱን ለመገናኘት ሲጠጋ ይህን የአእምሮ ክፍል ያሰናክለዋል። የወንዱን ብልት ዝግጁ ለማድረግ ደም እንዲረጭ የሚያደርጉትን የአእምሮ መልእክቶች አንዳይተላለፉ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህ ሳቢያ / ለግንኙነት ዝግጁ የሚያደርገዉ ደም ወደ ወንዱ ብልት አይደርስም፡፡ በወንዱ ብልት ዉስጥ ያለዉም ደም ይመለሳል፡፡ በዚህም ሳቢያ የወንዱ ብልት ጨርቅ ይሆናል፡፡
ለዚህም ነዉ አንድ ባል ከሚስቱ ጋር ቅድመ ወሲብ ልፍያ በሚያደርግበት ጊዜ ብልቱ ዝግጁ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ብልቱን ወደ ብልቷ ሲያስጠጋ ድንገት ይሟሽሽና ግንኙነቱ ሳይሳካ ይቀራል፡፡
♠ እንዲህም ያጋጥማል፡- ባል ሁለት ሚስቶች ይኖሩትና ከአንደኛዋ ጋር ወሲባዊ ተራክቦ ሲፈጽም ደህና ይሆናል፡፡ ከሁለተኛዋ ጋር ግን መሰናክለ ወሲብ ያጋጥመዋል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ድግምት የተሰራበት ከሁለተኛዋ ሚስቱ ጋር እንዳይገናኝ ለማድረግ ነዉ ማለት ነዉ፡፡
ባል ሁለተኛ ሚስቱን ለመገናኘት ሲቀርባት የድግምቱ እንደራሴ ሰይጣን ጂን ያሰናክለዋል፡፡ ምክንያቱም ሰይጣኑ የታዘዘዉ ከሁለተኛ ሚስቱ ጋር እንደይገናኝ እንዲያሰናክለዉ በመሆኑ የታዘዘዉን ብቻ ይፈፅማል፡፡
🟢 #የሴቶች_መሰናክለ_ወሲብ
በወንዶች ላይ የሚከሰተዉ የመሰናክለ ወሲብ ዓይነቱ ይለያይ እንጂ በሴቶች ላይም ይከሰታል፡፡ በሴቶች ላይ የሚከሰት መሰናከለ በአምስት ይከፈላል፡፡ እነሱም፡-
➊ #መከልከል
ይህ የሚከሰተዉ ሴቷ ጭኖቿን እርስ በርሳቸዉ በማቆላለፍ እንዲይገናኛት ስታደርግ ነዉ። ይህም በሴቷ ፍላጎት የሚከሰት ሳይሆን ክፍላጎቷ ወጪ በዉጫዊ ሀይል የሚከሰት ነዉ። አንድ ወጣት በዚህ ዓይነት ድግምት መለከፏን ሳያዉቅ ሚስቱን ለምን እንዲህ ታደርጊያለሽ እያለ ሲጨቀጭቃት እንዲህ ትመልስለት ነበር እኔኮ ፈልጌ አይደለም የማደርገዉ ጭኖቼ እንዳይቆላለፉ ከፈለክ ግንኙነት ከማድረጋችን በፊት እግሮቼን በሰንሰለት ለያይተህ እሰራቸዉ" አለችዉ፡፡ እንዳለችዉም አደረገ ነገር ግን ምንም መፍትሄ ሊያመጣ አልቻለም፡፡ ሊገናኛት በሚፈልግበት ወቅት ማደንዘዣ መርፌ እንዲወጋት ጠቁማዉ አደረገዉ፡፡ መፍትሄ ቢገኝም አንደኛዉን ወገን ብቻ ነበር የጠቀመዉ፡፡ ከዚያም የቁርዓን ህክምና በመከታተል ተፈወሰች፡፡
➋ #ወሲባዊ_ስሜት_ማጣት
በድግምት የተወከለዉ ጂኒ የሴቷን የወሲብ ስሜት በሚቆጣጠረዉ የአእምሮ ክፍል ዉስጥ ይቀመጣል፡፤ ባለቤቷ ሊገናኛት ሲቀርብ የወሲብ ስሜት እንድታጣ ያደርጋታል። በዚህም ሳቢያ ወሲባዊ እርካታ አታገኝም ለባሏ ፍቅር ምላሽ መስጠት ይሳናታል፡፡ ባለቤቷ የሻዉን ቢያደርጋት እንኳ የሞተ ገላ ትሆንበታለች፡፡ በተጨማሪም ለግንኙነት ብልት የሚያለሰልሰዉ ፈሳሽ አስፈላጊ የሆነዉ እና የሴቷን ብልት እይመነጭም፡፡ በዚህ ሳቢያ ወሲባዊ ተራክቦዉ ሳይሳካ ይቀራል።
➌ #በወሲባዊ _ግንኙነት_ወቅት_ደም_መፍሰስ
ከተለመደዉ የወር አበባ ቀናት ዉጪ ደም መፍሰስን በተመለከተ በዚህ ቀደም አይተናል፡፡ በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ደም መፍሰስ ከዚህ አንድ ነገር ይለያል፡፡ ይኸዉም በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ደም መፍሰስ የሚከሰተዉ በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ብቻ ሲሆን ከተለመደዉ የወር አበባ ቀናት ዉጪ ደም መፍሰስ ደግሞ ከወሲባዊ ግንኙነት ጋር ተያያዥነት የለዉም እንዲያዉም ለበርካታ ቀናት ያለማቋረጥ የሚዘልቅ ነዉ፡፡
በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ደም መፍሰስ ማለት አንድ ባል ሚስቱን ሊገናኝ ሲል ሰይጣን ደም እንዲፈሳት ያደርጋታል፡፡ በዚህ የተነሳ ባል ለመገናኘት አይችልም፡፡
አንድ ወታደር እንዲህ ብሏል፡- ለእረፍት ወደ ቤቴ መጥቼ ገና ከቤት ስደርስ ባለቤቴ ደም መፍሰስ ይጀምራታል፡፡ ደሙም ቤት ዉስጥ ባለሁባቸዉ የእረፍት ቀናት ሁሉ ይቆይባታል። የእረፍት ፈቃዴን ጨርሼ ወደ ጦሩ ስቀላቀል ግን ደሙ ይቋረጣል፡፡ እንዲያዉም ገና ቤቴን ሲለቅ ነዉ ደመ የሚቆመዉ፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ነዉ፡፡ ከዚያም ሴትየዋ የቁርአን ህክምና በመከታተል ተፈወሰች።
➍ #የሴቷ_ብልት_በስጋ_መሸፈን
ባል ሚስቱን ለመገናኘት ሲጠጋ በብልቷ አካባቢ የሚያግደዉ እና ሊበጥሰዉ የማይችለዉ ስጋ ያጋጥመዋል። በዚህ ሳቢያ ወሲባዊ ተራክቦዉ ሳይሳካ ይቀራል፡፡
➎ #ድንግልናን_ማድበስበስ
አንድ ባል ድንግል ያገባል፡፡ ነገር ግን በግንኙነት ወቅት ድንግልና የሌላት ሆና ያገኛታል፡፡ በዚህም ጥርጣሬ ላይ ይወድቃል፡፡ ነገር ግን ከቁርዓን ህክምና በኋላ ድግምቱ ሲከሽፍ ድንግልናዋ ይመለሳል።
⚫️ #የመሰናክለ_ወሲብ_ህክምና
መሰናክለ ወሲብን ለማከም በርካታ ዘዴዎች አሉ እነርሱም፡-
🌙 #ዘዴ_አንድ 1⃣
የአል ሩቅያ አንቀፆችን በታማሚዉ ላይ ትቀራበታለህ፡፡ በዚህም ጂኒዉ ከለፈለፈ ድግምቱ ስለሚገኝበት ቦታ ትጠይቀዉና ድግምቱን አዉጥተህ እንዲከሽፍ ታደርገዋለህ፡፡ ከዚያም ጂኒዉ ከሰዉዬዉ አካል እንዲወጣ ትነግረዋለህ። ከወጣ ድግምቱ ከሸፈ ማለት ነዉ፡፡ ነገር ግን የአል ሩቅያ አንቀፆችን ስትቀራበት ጂኒዉ ካልተናገረ ከዚህ በታች ከምናያቸዉ ዘዴዎች ዉስጥ ትጠቀማለህ፡፡
🌙 #ዘዴ_ሁለት 2⃣
ሱረቱል አእራፍ 117-122 የቁርአን አንቀፅን በዉሃ ላይ ሰባት ጊዜ ደጋግመህ ትቀራለህ፡፡ ከዚያም ታካሚዉ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ከዚህ ዉሃ ይጠጣለታል ይታጠብበታልም፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱ ይረክሳል።
🌙 #ዘዴ_ሶስት 3⃣
ሰባት አረንጓዴ የቁርቁራ ቅጠሎችን ታመጣና በሁለት ድንጋይ መሃል ትጨቀጭቃቸዋለህ፡፡ ከዚያም በዉሃ ዉስጥ ትጨምራቸዉና ዉሀዉን ወደ አፍህ አስጠግተህ ቅጠሎቹን በእጅህ እያገላበጥ አያት አል ኩርስይ፤ አል ኢኽላስ አል ፈለቅ እና አል ናስን ሰባት ጊዜ በመደጋገም ትቀራበታለህ፡፡ - ከዚያም ታካሚዉን ለሰባት ቀናት አንዲጠጣና እንዲታጠብበት ታደርጋለህ፡፡ ይህንንም ሲያደርግ በዚህ ዉሀ ላይ ሌላ ዉሃ መጨመርም ሆነ በእሳት ማሞቅ የለበትም... በፀሀይ ማሞቅ ግን ይችላል። ከታጠበ በኋላም አጣቢዉን በቆሻሻ ቦታ ላይ ማፍሰስ የለበትም፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱ ከሽፎ መሰናክሉ ወሲቡ ይድናል፡፡
🌙 #ዘዴ_አራት 4⃣
የአል ሩቅያ አንቀጾችን በታማሚዉ ጆሮ ላይ ትቀራለህ፡፡ ከዚያም በእጆቹና በእግሮቹ ጫፎች የመደንዘዝ ስሜት እስኪሰማዉ ድረስ ከዚህ በታች የተጠቀሰዉን የቁርአን አንቀጽ መቶና ከዚያ በላይ ደጋግመህ በጆሮዉ ላይ ትቀራበታለህ፡፡ ይህንንም ጤንነት እስኪሰማዉ ድረስ ለበርካታ ቀናት ትደጋግምለታለህ፡፡ ችግሩ ከተወገደለት ድግምቱ በአላህ ፈቃድ መክሸፉን ታረጋግጣለህ፡፡ ይህም አንቀጽ የሚከተለዉ ነዉ።👇👇👇
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5977