tgoop.com/Islam_and_Science/5972
Last Update:
⚠️⚠️ በዚህ ዙርያ ሷሂሮትን የሚለዩባቸው አጋጣሚዎች እነሆ፡፡ ይህን ሲህር የሰራቦትን ሰው ሲያዩ፡፡
♦️ ልቦ መፍራት መምታት ይጀምራል፡፡
♦️ ጭንቀት ይወሮታል፡፡ አጠገቡ መቀመጥን አይቻሎትም፡፡
♦️ ያ ሰው የፈለገውን ነገር አድርገው መገላገል ምኞቶ ነው፡፡ በተቃራኒ ግን ያ ሰው እጅግ እርጋታ የተሞላበት ሁኖ ያገኙታል፡፡ ምክያቱም ለግዜው አሸናፊ የሆነ ስለሚመስለው ነው፡፡ አሏህም ካርታውን ያጠፋበታል፡፡ አንዴ ሩቅያህ ከጀመሩ ኋላ፡፡
♦️ ከሱ ጋር ላለመገናኘት የማያደርጉት ጥረት አይኖርም ሰውየው ግን ሁሌም እርሶ ባሉበት ስፍራ አይጠፋም፡፡ ይህም ከብዙዎቹ በጥቂቶቹ ላይ የሚታይ ነው፡፡
====== ===== ==== ===== ===== =====
🟢 #ከተለመደዉ_የወር_አበባ_ቀናት_ዉጪ ደም እንዲፈስ የሚያደርግ ድግምት አንዴት ይከሰታል?
>>> ይህ ዓይነት ድግምት በሴቶች ላይ ብቻ የሚከሰት ነዉ፡፡ አንድ ጠንቋይ ድግምት ወደ ሚደረግባት ሴት ደም እንዲፈሳት እንዲያደርጋት ጂኒ ይልካል፡፡ ጂኒዉም በሴትየዋ ዉስጥ በመግባት በደም ስሮቿ ዉስጥ ይዘዋወራል።
.... ይህን በማስመልከት ነብዩ እንዲህ ይላሉ ሰይጣን በሰዉ ሰዉነት ዉስጥ ደም እንደሚዘዋወረዉ ይዘዋወራል” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል) ጂኒዉ ወደ ሴቷ ማህፀን የደም ጋን በመድረስ ይረግጠዋል በዚህም ደም ይፈሳታል፡፡
✅ ከተለመዱ የወር አበባ ቀናት ዉጪ ስለሚፈስ ደም ተጠይቀዉ ነብዩ እንዲህ አሉ
>>> “ይህ ዓይነት ደም የሰይጣን እርግጫ ዉጤት ነዉ” (ቲርሚዚ ዘግበዉታል ሃስኑን ሶሂህ ነዉ ብለዉታል)
በሌላ ዘገባም ይህንኑ አስመልክተዉ ነብዩ እንዲህ ይላሉ "የሰይጣን እርግጫ ዉጤት ነዉ፣ የወር አበባ ደም አይደለም፡፡" አህመድና ነሳኢ ቢሰነዲን ጀይድ" ዘግበዉታል)
ከነዚህ ሁለት ዘገባዎች የምንገነዘበዉ ከተለመደዉ የወር አበባ ቀናት ዉጪ የሚፈስ ደም በሰይጣን እርግጫ ሳቢያ ከማህፀን የደም ጋን የሚፈስ መሆኑን ነዉ፡፡
#ህክምናዉ
የእል ሩቅያ አንቀፆችን በዉሀ ላይ ትቀራና ታማሚዋ ትጠጣለች ለሶስት ተከታታይ ቀናትም ሰዉነቷን ትታጠብበት፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ደሙ ይቆማል፡፡
🟡 #ሰዉ_እንዳያገባ_ለማድረግ_የሚደረግ_ድግምት
አንድን ሰው ከትዳር ለማራቅ ሚደረጉ ሲህሮች እጅግ አስነዋሪዎች ናቸው፡፡ ከእነዛ ምልክቶች ዉስጥ
☑️ የውስጥ አለመረጋጋት እጅግ በጣም ለነገራቶች መጨነቅ
☑️ ቀን ላይ ትዳር ፈልጎ የመጣው ሰው ውሳኔ አጥቶ ወድያው መመለስ! አለመፈለግ፡፡ መጀመርያ ፍላጎት ኑሮ ከዛንም ፍላጎት ማጣት፡፡
☑️ ልብ በየቀኑ ‹‹ቀኔ እያለፈ ነው ሲል መጨነቅ፡፡›› ይህ ሁሉም ሰው ይጨነቃል ግን ደግሞ ያንቺ ይብሳል ልብሽ እስኪፈነዳ ድረስ መጨነቅ፡፡
☑️ ብሩህ የወደፊት ተስፋን ‹‹ትዳርን›› ፈላጊ መሆን ግን ደግሞ ትዳር ሲመጣ እጅግ መጥላት!!
☑️ ዶሮ ከመጮሁዋ እና ከመንጋቱ ፊት በተለይ ሱብሂ ሰላት አካባቢ በህልም ከጥቁር መልኩን ከማታውቂው ሰውነቱ ፈርጣማ ከሆነ ሰው ጋር ወሲብ ማድረግ፡፡
☑️ ክንውንን ወይም በውስጠ ህሊና ሀራም ማሰብ ወይም ማስተርቤሽን ማብዛት፡፡ ሃታ ሰላት ላይ ሳይቀር ማስተርቤሽንን ማሰብ! የመሳሰሉት ናቸዉ
📌📌 ምቀኛና ተንኮለኛ የሆነ ሰዉ ጠንቋይ ዘንድ በመሄድ እገሊት የእገሌ ልጅ እንዳታገባ የሆነ ነገር አድርግ ይለዋል፡፡ ጠንቋዩም የልጅቷንና የእናቷን ስም ይጠይቀዋል፡፡ የላቧ ጠረን ያለበትን ልብስ፤ ፀጉር... እንዲያመጣለት ያደርግና ድግምት መስራት ይጀምራል፡፡ ለዚህ ድግምት አንድና ከአንድ በላይ ጂኒዎችን ይወክላል፡፡ ከዚያም ጂኒዉ ወደ ልጅቷ በመሄድ ለመግባት እድል እስከሚያገኝ ድረስ ይከታተላታል፡፡ ከሚከተሉት አራት ምክንያቶች አንዱ ሲከሰት ጂኒ ወደ ስዉ ልጅ ስነት ሊጋባ ይችላል።
➊ ከፍተኛ ፍርሃት ሲኖር
➋ ከፍተኛ ንዴት (ቁጣ) ሲክስት
➌ ከፍተኛ እንቅልፍ ወይም እራስን አለማወቅ በሚኖርበት ወቅት
➍ በማንኛዉም በትንሽም በትልቅ በሀራም ስራዎች ዉስጥ መዘፈቅ
በዚህ ጊዜ ጂኒዉ ሁለት አማራጮች ይኖሩታል፡፡
1⃣ ልጅቷ ዉስጥ በመግባት ለማጨት የሚመጣ ወንድ ስታይ እንድትጨነቅ እና እንድትተወዉ ማድረግ፡፡ ወይም
2⃣ ልጅቷ ዉስጥ ለመግባት ሳይችል ከቀረ ከልጅቷ ዉጪ በመሆን የማስመሰል አስማት መስራት ይጀምራል፡፡ በዚህም ልጅቷን ለማጨት የሚመጣን ሰዉ መልከ ጥፉ መስላ እንድትታየዉ በማድረግ ይወሰዉሰዋል፡፡ ልጅቷንም እንደዚሁ ይወሰዉሳታል፡፡
በዚህም የተነሳ ሊያጫት የሚመጣ ሁሉ ሲተዋት ይስተዋላል፡፡ በመጀመሪያዉ ቀን ሊያገባት የተስማማ ከቀናት በኋላ ሲያፈገፍግ ታየዋለህ፡፡ ይህ እንግዲህ የሚሆነዉ በሰይጣን ውስወሳ ሳቢያ ነዉ፡፡
🌟 የተሰራዉ ድግምት ጠንካራ በሚሆንባቸዉ ሁኔታዎች ልጅቷን ለማጨት የሚመጣዉ ስዉ ገና ወደ ቤት ሲገባ ከፍተኛ ጭንቀት ይሰማዋል። ልክ እስር ቤት እንዳለ ሰዉ ህይወት ትጨልምበታለች፡፡ በዚያዉ ሳይመለስ ይቀራል፤ የዚህ ዓይነት ድግምት በሚቆይባቸዉ ጊዜያት በልጅቷ ላይ ብቅ እልም የሚል እራስ ምታት ወይም ማይግሬን የሚባለዉ የራስ ህመም
(ግማሽ ራስን ከፍሎ የሚያም) ይስተዋላል።
🌟 #ሰዉ_እንዳያገባ_ለማድረግ_የሚደረግ_ድግምት_ሲህር_ምልክቶች
⚡️ መድሃኒት በመዉሰድ የማይሻል ሄድ መጣ የሚል የራስ ምታት
⚡️ከባድ የራስ ምታት (ማይግሬን)
⚡️ደረት ዉስጥ ጭንቅ የሚል ስሜት በተለይም ከአስር ሰዓት በኋላ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ
⚡️ለማጨት የሚፈልገዉን ሰዉ መልከ ጥፉ አድርጎ መመልከት
⚡️በብዛት በሀሳብ መወጠር (የሀሳብ መብዛት)
⚡️ በመኝታ ወቅት ፍርሃት ፍርሃት ማለት
⚡️ ይህ ዓይነት ድግምት በተደረገባቸዉ አንዳንድ ሰዎች ላይ የሆድ ህመም ይከሰታል
⚡️ የጀርባ የታችኛዉ ክፍል ህመም (የጀርባ ላይ ህመም መሰማት
📌📌 #ሰዉ_አንዳያገባ_ የተደረገበት_ ድግምት_ህክምና
✏️የሩቅያ አንቀፆችን ተቀራባታለህ እራሷን ከሳተች ከዚህ ቀደም በተማርነዉ መንገድ ጂኒዉን ታነጋግረዋለህ፡፡
✏️ እራሷን ሳትስት ነገር ግን በአካሏ ላይ የተለየ ስሜት የሚሰማት ከሆነ የሚከተለዉን እንድትከታተል ታደርጋለህ
➢ ሂጃብ መልበስ
➢ ሶላትን በወቅቱ ሳያቋርጡ መስገድ
ሙዚቃም ሆነ መዝሙር ከመስማት መታቀብ
➢ ከመኝታ በፊት ዉዱዕ ማድረግ እና አያት አል ኩርስይን መቅራት
➢ ለአንድ ሰዓት ያህል አያት አል ኩርሲሰይን በመደጋገም በስልክ ላይ በመጫን በቀን አንድ ጊዜ እንድታዳምጠዉ ማድረግ፡፡
➢ አል ኢኽላስ፤ አል ፈለቅ፤ አል ናስ ለአንድ ሰዓት ያህል በካሴት ደጋግሞ በመቅዳት በቀን አንድ ጊዜ እንድታዳምጥ ማድረግ
➢ በዉሃ ላይ የአል ሩቅያ አንቀጾችን ትቀራለህ፡፡ ከዚያም ከዚህ ዉሃ ልጅቷ ትጠጣለች፣ በየሶስት ቀኑ ልዩነት ሰዉነቷን ትታጠብበት፡፡
➢ ላኢላሀ ኢለ አላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሀምድ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ከስብሂ ሶላት በኋላ 100 ጊዜ ማለት
እነዚህን ለአንድ ወር ሙሉ መከታተል ይኖርባታል፡፡ ከዚህ በኋላ ከሚከተሉት አንዱ ይሆናል፡፡
➊ የህመሙ ምልክቶች ጠፍተዉ ህመሙ ድኖ ድግምቱ ይረክሳል።
አልሃምዱ ሊላህ ወይም
➋ ህመሙ ጠንቶባት የህመሙ ምልክቶች አይለዉ ሊሆን ይችላል። በዚህ ግዜ የአል ሩቅያ አንቀጾችን ትቀራባታለህ በአላህ ፈቃድ- እራሷን ትስታለች፡፡ ከዚያም ከዚህ ቀደም ባየነዉ መልኩ ጂኑን እንዲናገር እያረክ ታክማታለህ፡፡
#ክፍል 8⃣
ይቀጥላል....
Join👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5972