tgoop.com/Islam_and_Science/5969
Last Update:
ለሴቶች ጆሮ ሸክም ቃል ቢኖር ሁለተኛ ሚስት ላግባ የምትለዉ ንግግር መችም አትዋጣላቸዉ...ሁለተኛ ያገቡ ወንዶች ብዙዎች ደስታ አጥተዋል ወይ የመጀመሪያ ወይ ሁለተኛዋ ሲህር እያስደረጉባቸዉ
ከአንዷ ጋር ይጣላሉ ቤተሰብ ሲበተን እየተስተዋለ ነዉ፡፡ የሚገርመዉ አንዷ ጋር ሲሆኑ ጤነኛ የሆኑት ሌላ ሚስት ጋር ለመገናኘት አይችሉም ስንፈተ ወሲብ ይገጥማቸዋል፡፡ ብቻ ሁለተኛ ሚስት የሚያገባ አላህ ካዘነለት ከጠበቀዉ በቀር ከባድ ነዉ ፈተናዉ ሙሲባዉ ብዙ ነዉ፡፡
🌐 #መስተፋቅር_በተደረገባት_ሴት_የሚታዩ_ምልክቶች
✏️ ሴቷ ወይም ወንዱ ስለ አንድ ሰው በአንድ ወቅት ስላዩት ይሁን ስለሰሙት ሰው ከምንግዜውም በላይ ማሰብ ማሰላሰል ይጀምራሉ፡፡ ያን ሰው ከዚህ በፊት ሊቀርቡት ይገባል፡፡ ቀርበውትም ከእህትነት ወይም ከወንድምነት የዘለለ ፍላጎት የሌላቸው ሲሆን ይህ ሲህር ከተሰራባቸው ጀምሮ ግን ስለዚያ ሰው ህልም ማየት ማሰብ ፡፡
✏️ ያን ሰው አብዝቶ መናፈቅ ለደቂቃ ከነርሱ ጋር መሆን ከምንም በላይ ለነርሱ ልዩ ስሜትን ይፈጥራል፡፡ ከነርሱ ሲለያዩ እጅግ በጣም መፍራት ይፈጠርባቸዋል፡፡
✏️ ከርሱ ወይም ከርሷ ሲጣሉ እራስን ወደማጥፋት ማምራት ፡፡ ያለ ምንም ጥያቄና ቅድመ ሁኔታ እራስን ወደማጥፋት ሲሄዱ የገዛ ማንነቶ ህሊናዎ እንኳን ሊከላከሎት አይችልም፡፡ ይህን ሲያደርጉ ሰው እንዲያዮት ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ሲህር ለየት የሚለው በድብቅ እራስን ማጥፋት የሚያስፈፅም ሳይሆን በምስክር ፊት እራሶን ሊያጠፉ ይቃጣሉ፡፡
✏️ ድንገት ከመሬት ተነስተው ባልሆነና ባልታሰበ ሁኔታ ስለወደዱት ሰው መጥፎነትና አይረቤነት ቢነገራቸው እንኳን አለመስማት፡፡ ብሎም ይህ ከምቀኝነት የመነጨ ወሬ መሆኑን አምኖ ሰውን በሙሉ ለወደዱት ሰው ሲሉ መራቅና መጣላት፡፡
✏️ ያን ሰው እስከማምለክ መሞከር ፡፡ በዚያ ሰው ይምላሉ በዚያ ሰውም እድለኛ ይሆናሉ፡፡ ያ ሲህር ያደረገባቸው ሰው ላይ ሰው የማያየውን ልዩ እና አስደሳች ፀባዮችን እነርሱ ብቻ ይታያቸዋል፡፡
✏️ ልብ ሊባል የሚገባዉ ነጀር ሲህሩን ያደረገው ሰው ለአፍቃሪው የተለየ ስሜት የለውም ፡፡ በአፍቃሪው ላይ መጥፎ ነገሮችን ሲሰራ ነው የሚታየው አፍቃሪውን ሲያሰቃይ ነው የሚታየው፡፡ ይህ ግን ለአፍቃሪው አይታወቀውም፡፡
✏️ አልፎ አልፎ ጥዋትም ይሁን ከሰአት እንቅልፍ ተኝተው ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ወደ ማንነት መመለስና በሰሩት ስራ በሙሉ መፀፀት እራስን በጣም መጥላት፡፡ እነኚህ ሰዎች በዚህ ወቅት ከሰው ደብቀው የሚያስቀምጡት ዲያሪ ነክ ነገሮች ሊኖሩዋቸው ይችላል፡፡ ፍፁምም ከሰው የተደበቁ ደብተሮች ብዙ ምስጢር የያዙ ነገሮችን ይይዛሉ፡፡ ይህን ግን ለማንም ቢሆን አያሳዩም፡፡ ሞትንም ይመርጣሉ፡፡ ይሁንና ወደ ቀድሞው ማንነት በሚገቡበት በዚያች ቅፅበት ቡና በሚጠጡበትና በቃ ሲገፋፋቸዉ ወ ያን ምስጢር የማሳየት ግፊታቸው ሀይለኛ ነው፡፡
✏️ ጥርሷን በጣም ታፋጫለች ይህም በተኛችበት ጥርስ ጥርሶቿን መብላት ትጀምራለች፡፡
✏️ ከኢማን ከሰላት ከቂርአት ትሸሻለች፡፡ ይህ ሰው ቢርቃት እንኳ ካላገባሁት ሙቼ እገኛለሁ ትላለች፡፡
✏️ ይህ ሲህር ሲጀምር ሰውየውን መፍራት የምትጀምር ሲሆን ያም ፍራቻ ወደ ወሲባዊ ፍቅር ተለዋጭ ነው፡፡
✏️ ጅኖችም በዚህች ሴት አናት ላይ ያረፉ ሲሆኑ ይህች ሴት አብዛኛውን ግዜ የራስ ህመም(ማይግሬን) አለባት በመድሀኒት የማይፈታ፡፡
✏️ ብቻን ማልቀስ ብቸኝነት መሰማት ከሰዎች መሀል ውስጥ ሁና ብቸኝነት ይሰማታል፡፡ ይህም ስለርሱ ላታስብ ትችላለች ግና ብቸኝነቱ ከባድ ነው፡፡
🔰🔰 ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች የተወሰነም ቢሆን ምልክቱ ከአንቺ ጋር ካለ
👉 በመጀመርያ ዳእዋዎችን ማዳመጥ ስለ ቀብር ስለ አላህ ውዴታ የሚያስተምሩ ዳእዋዎችን መከታተል፡፡
👉 በቀጣይም አያተል ኩርሲን መቅራት ያም ልጁን ስታስብ መቅራቱ ይረዳታል፡፡
👉 በመቀጠልም ውዱእን መጠበቅ ከውዱእ ውጭ አለመሆንና
👉 የሰሃቦችን ታሪኮች ማንበብ
👉 ስሜት ቀስቃሽ ከሆኑ ነገሮች በሙሉ ልትርቅ ይገባታል፡፡
⚠️⚠️ እንዲህ አይነት ነገር እንዳይገጥማችሁም ምሽት ላይ በአዳበ ነውም መሰረት እንቅልፍን መተኛት ጥዋትም በሚነሱበት ወቅት አያተል ኩርሲን ማንበብ ተገቢ ነው፡፡
🟢 #የመስተፋቅር_ህክምና
➊ የአል ሩቅያ አንቀጾችን በታካሚዉ ላይ ትቀራለህ፡፡ ከአል ሩቅያ አንቀጾች ዉስጥ የአል በቀራ ምዕራፍ አንቀጽ 102 ን በመተዉ በምትኩ ከአል ተጋቡን ምዕራፍ አንቀጽ 14፣ 15 እና 16 መቅራት
➋ በመስተፋቅር ድግምት የተለከፈ ሰዉ ሲቀራበት አብዛኛዉን ጊዜ እራሱን አይስትም፡፡ ሆኖም በእጆቹና በእግሮቹ አካባቢ የመደንዘዝ ስሜት ይሰማዋል።
>> እራስ ምታት፣
>> ደረት አካባቢ የማፈን
>> ከፍተኛ የ የሆድ ህመም ይሰማዋል (በተለይ ሆዱን የሚያመዉ ድግምቱን በልቶት ወይም ጠጥቶት ከሆነ ነዉ)፡፡ ምን አልባትም : ሊያስመልሰዉ ሁሉ ይችላል፡፡ በተለይ የሆድ ህመም የሚሰማዉ ወይም ለማስመለስ የሚቃጣዉ ከሆነ
☞ ሱረቱ ዩኑስ 81-82
☞ ሱረቱ ዩኑስ81
☞ ሱረቱል ጦሀ 69
☞ ሱረቱል በቀራ 255
☞ የቁርአን አንቀጾች
በዉሃ ላይ ትቀራና ፊት ለፊትህ እንዲጠጣዉ አድርግ፡፡
ታካሚዉ እነዚህ የቁርአን አንቀፆች የተቀሩበትን ዉሃ ሲጠጣ ቢጫ ወይም ቀይ ወይም ጥቁር ነገር ካስመለሰዉ ድግምቱ ፈሰደ (ተፈታ) ማለት ነዉና ምስጋና ለአላህ አድርስ፡፡
ይህ ነገር ካልተከሰተ ደግሞ እነዚህ አንቀች የተቀሩበትን ዉሀ ለሶስት ተከታታይ ሳምንታት ወይም እንደ አስፈላጊነቱ ከዚያ በላይ ድግምቱ እስኪፈታ ድረስ ይጠጣ፡፡ ይህን ሲያደርግ ሚስቱ ማወቅ የለባትም፡፡ ምክንያቱም ህክምና እየተከታተለ መሆኑን ካወቀች ዳግመኛ ልታሳድስበት ትችላለችና፡፡
ሴትም ከሆነች የተደረገባት ባልየዉ ማወቅ የለበትም መልሶ ሂዶ ሊያሳድስ ይችላልና...ከትዳር በፊት ከሆነ የተደረገዉ ዝምታ ነዉ የሚሻለዉ ከሰማ ወይ ከሰማች መልሶ ማሳደሱ በጣም ቀላል ስለሆነ ....
#ክፍል 7⃣
ይቀጥላል.....
አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5969