tgoop.com/Islam_and_Science/5965
Last Update:
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉 አምስት 5⃣
🟢 #የሚለያይ_የሚያጣላ_መተት_ሲህር_ምንነት
ባልና ሚስትን ለማለያየት፣ በጓደኞች ወይም በንግድ ሸሪኮች መካከል ጠብ እና ጥላቻ እንዲፈጠር ለማድረግ የሚሠራ መተት ነዉ።
🔶 #የሚለያይ_መተት _ዓይነቶች
➊ እናትና ልጅን የሚያጣላ
➋ አባትና ልጅን የሚያጣላ
➌ ወንድማማቾችን የሚያጣላ
➍ ጓደኛሞችን የሚያጠላ
➎ የንግድ ወይም በሌላ መስክ የተሰማሩ ሽሪኮችን የሚያጣላ
➏ባለትዳሮችን የሚያለያይ (የሚያጣላ) ይህ ዓይነቱ አስከፊዉና እጅግ በጣም ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡
🔷 #የሚለያይ_የሚያጣላ_መተት_ሲህር_በተስከፈ_ሰዉ_ላይ_የሚታዩ _ምልክቶች
☞ከመዉደድ ወደ መጥላት ያልተጠበቀ የፀባይ ለዉጥ
☞መጠራጠር ማብዛት
☞አንዱ ሲያጠፋ ሌላኛዉ ያለማለፍ (ይቅር አለመባባል)
☞ በጣም ቀላልና ትንሽ ብትሆንም የፀባቸዉን መንስኤ ማግዘፍ
☞በትንሽ በትልቁ መጋጨት
☞ሚስት ለባሏ ያላት ባል ለሚስቱ ያለዉ እይታ መለወጥ፡፡ ምንም ዉብ ቆንጆ ብትሆንም እንኳን ባል ሚስቱ መልከ ጥፉ ትመስለዋለች አስቀያሚ መስላ ትታየዋለች። በተመሳሳይ መልኩ ሚስት ባሏ አስፈሪ መስሎ ይታያታል፡ በተጨባጭ ግን በሚስቲቱ ወይም በባል ፊት በአስቀያሚ ምስል የሚመሰለዉ የድግምቱ እንደራሴ ሰይጣን ነዉ።
☞ ድግምት የተደረገበት ወገን ሌላኛዉ የሚሰራዉን ሥራ መጥላት
☞ ድግምት የተደረገበት ወገን ሌላኛዉ የሚቀመጥበትን ቦታ መጥላት (ከፊቱ ዞር እንዲልለት ይፈልጋል)
#ለምሳሌ፡- ድግምት የተደረገበት ሰዉ ከከቤቱ ዉጭ ሲሆን በጥሩ ሁኔታና ፀባይ ይታያል ወደ ቤቱ ሲገባ የጭንቀትና የድብርት ስሜት ይሰማዋል።
☑️ ይህን በማስመልከት አል ሃፊዝ ኢብን ከሲር እንዲህ ይላሉ... ባለትዳሮች በድግምት የተነሳ የሚጣሉትና የሚለያዩት መጥፎ ወይ አስቃያሚ መልክ፣ እና ሌሎች የሚያጣሉ ነገሮችን አንዱ በሌላዉ ላይ ያየ ስለሚመስለዉ ነዉ፡፡
🟡 #የሚያለያይ_ድግምት_ሲህር_አንዴት_ሲከሰት_ይችላል?
አንድ በአላህ የተረገመ ሰው ወደ ጠንቋይ ዘንድ ይሄድና እገሌ እና ሚስቱን እንዲያለያይለት ይጠይቀዋል፡፡ ጠንቋዩም ድግምት የሚደረግበትን ሰዉዬ ስምና የእናቱን ስም ንገረኝ ይለዋል።
ከዚያም የዚህን ሰዉዬ
>> የላብ ፋና
>> የፀጉሩን
>> የልብሱን
>> የኮፍያዉን፣ የካልሲዉን ቁራጭ ይቀበለዋል፣
የላቡን ፋና ማግኘት የማይችል ከሆነ፣ በፈሳሽ ነገር ላይ ድግምት ይሰራና በስዉዬዉ መንገድ ላይ እንዲረጨዉ ያዘዋል፡፡ ሰዉዬዉ በሚረግጠዉ ጊዜ በድግምቱ ይለከፋል (እስላማዊ የድግምት መከላከያዎችን የሚከታተል ከሆነ ግን በድግምቱ አይለክፍም)፡፡
🟣 #የሚለያይ_የሚያጣላ_ድግምት_ህክምና
☑️ ደረጃ አንድ ቅድመ ህክምና ተገባራት
ህክምናዉ ከመጀመሩ በፊት የሚከተሉትን አድርግ-
➊ የኢማን አካባቢ መፍጠር :- ይህም ማለት ህክምናዉ በሚሰጥበት ክፍል ዉስጥ መላኢኮች መግባት እንዲችሉ ፎቶዎች እና ምስሎች ካሉ ማንሳት እና ንጽህናዉ የተጠበቀ ክፍል ሊሆን ይገባል፡፡
➋ ሂርዝ፣ ክታብ የመሳሰሉ ታካሚዉ የያዛቸዉ ነገሮች ካሉ ማስወገድ እና ማቃጠል
➌ ህክምና በሚደረግበት ክፍል ዉስጥ ሙዚቃ እና የመሳሰሉት ነገሮች መኖር የለባቸዉም
➍ በሸሪዓ ከተከለከሉ ነገሮች ቦታዉ የፀዳ መሆን አለበት ፡፡
ለምሳሌ
>> ወርቅ ያደረገ ወንድ
>> ሂጃብ ያልለበሰች ሴት
>> ሲጋራ የሚያጨስ መኖር የለበትም
➎ ለታካሚዉና ለቤተሰቦቹ በእስልምና እምነት (በአቂዳ) ዙሪያ ትምህርት መስጠት፡፡ ይህም በአላህ ላይ ያላቸዉን እምነት ያፀናላቸዋል፡፡
በአላህ ላይ ብቻ ተስፋ እንዲኖራቸዉ ያደርጋል።
ጠንቋዮች የሚያክመት ከስይጣን ጋር በመተባበር መሆኑን አንተ ግን የምታክመዉ በአላህ ቃል በቁርአን ብቻ መሆኑን ለታዳሚዎች በሚገባ ልታባራራላቸዉ ይገባል።
እንዲሁም የቁርአንን ፈዋሽነት ልታረጋግጥላቸዉ ይገባል፡፡
➏ የህመሙን ሁኔታ በመጠየቅ መመርመር
የህመሙ ምልክቶች በሙሉ ወይም በአብዛኛዉ መኖራቸዉን ለማረጋገጥ ታካሚዉን አንዳንድ ጥያቄዎችን መጠየቅ፡- ለምሳሌ
✔አልፎ አልፎ እንኳን ቢሆን ባለቤትህ(ሽ) አስቀያሚ መስላ(ሎ) ትታይሃለች (ይታይሻል)?
✔ ከባለቤትህ (ሽ) ጋር በትንሽ በትልቁ ትጋጫላችሁን
✔ ቤት በደህና ዉለህ (ሽ) - ወደ ቤት ስትገንቢ የመጨናነቅና የድብርት ስሜት ይሰማሃል (ይሰማሻል?)
✔ከባለቤትህ (ሽ) ጋር በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ጭንቀት ይሰማሀል (ሻል)?
✔ አንተ ወይም ሚስትህ በእንቅልፍ ማጣት ተቸግራችኋልን?
✔አስፈሪ ህልሞች ይታዩሃል?
>>>>እንደዚህ እያልክ ጥያቄህን ትቀጥላለህ፡፡ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሚሆኑ የድግምት ምልክቶች በታካሚዉ ላይ ከተገኙበት ህክምናን ትቀጥላለህ፡፡
1⃣ ህክምና ከመጀመርህ በፊት ዉዱእ አድርግ፡፡ ታካሚዉ እና አብረዉህ የታደሙት ዉዱዕ እንዲያደርጉ አድርግ
2⃣ ታካሚዋ ሴት ከሆነች በሚገባ ትሸፋፈን በህክምና ወቅት እንዳትገለጥ ልብሶቿ ጠበቅ ተደርገዉ ይታሰሩ
3⃣ ከሸሪዓ ዉጭ የለበሰች (ምሳሌ፡- ፊቷን የገለጠች፣የጥፍር ቀለም የተቀባች ሴት አታክም
4⃣ ሙህሪሟ በሌለበት ሴትን አታከም
5⃣ በህክምና ክፍሉ ዉስጥ ከሙሀሪሟ በስተቀር ማንንም አታስገባ
6⃣ ሃይልም ሆነ ብልሃት የአላህ እንጂ አንተ እንደሌለህ አምነህ በአላህ ብቻ ታገዝ
🟠 #ህክምናዉ_በደንብ_እናስተዉል
እጅህን በታካሚዉ ራስ ላይ ታደርግና የሚከተሉትን የቁርአን አንቀጾች በጥሩ አቀራርና ከፍ ባለ ድምፅ በጆሮዎቹ በኩል ትቀራበታለህ፡፡ እነዚህ የቁርአን አንቀጾች የሩቅያ አንቀጾች በመባል ይታወቃሉ፡፡ እነዚህ የሩቅያ አንቀጾች ጂኒዉ ከሰዉየዉ አካል ወጥቶ እንዲሄድ ወይም ቀርቦ እንዲናገር (እንዲለፈልፍ) ያደርጉታል፡፡
መቅራት የማትችል ከሆነ እነዚህን የሩቃ አንቀፆች በሞባይል ወይም በFLASH አድርጎ በጂፓስ ከፍቶ እንዲያዳምጥ ማድረግ ይቻላል፡፡
🔶 #የቁርአን_አንቀፆቹ
➊ ሱረቱል ፋቲሀ
➋ አል በቀራህ 1-5
➌ አል በቀራህ 101-102
➍ አል በቀራህ 163-164
➎ አል በቀራህ 255
➏ አል በቀራህ 285-286
➐ አል ኢምራን 18-19
➑ አል አዕራፍ 54-56
➒ አል አዕራፍ 117-122
➓ ዩኑስ 81-82
➊➊ አል ሙእሚኑን 115-118
➊➋ አስ ሷፍፋቲ 1-10
➊➌ አል አህቃፍ 29-32
➊➍ አር ረህማን 33-36
➊➎ አል ሃሽር 21-24
➊➏ አል ጂን 1-9
➊➐ አል ኢኸላስ
➊➑ አል ፈለቅ
➊➒ አል ናስ
በነዚህ የቁርአን አንቀፆች በጥሩ አቀራር ከቀራህበት በሆላ ታካሚዉ ከሚከተሉት ሶስት ሁኔታዎች ዉስጥ
በአንዱ ሁኔታ ላይ ይሆናል፡፡
1⃣ #አንደኛዉ_ሁኔታ
ታካሚዉ እራሱን ይስታል የድግምቱ እንደራሴ ጅኒዉ መናገር (መለፍለፍ) ይጀምራል፡፡ በዚህ ግዜ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጂኑን ትጠይቃለህ።
➊ ስምህ ማን ነዉ? ሀይማኖትህ ምንድን ነዉ? ሀይማኖቱን ሲነግርህ እንደ ሀይማኖቱ ሁኔታ ታነጋግረዋለህ፡፡ ይህም ማለት ሙስሊም ካልሆነ እስልምናን እንዲቀበል ጥሪ ታቀርብለታለሁ፡፡ ሙስሊም ከሆነ ደግሞ የሚሰራዉ ሥራ ማለትም ጠንቋይን ማገልገሉና መተባበሩ እስልምናን የሚቃረን እና የተከለከለ መሆኑን አስረዳዉ፡፡👇👇
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5965