tgoop.com/Islam_and_Science/5960
Last Update:
✅ ድግምተኛ እና ሰይጣን አላህ ሱ.ወ በማመፅ ላይ የተሰማሩ ሁለት ጥንዶች ናቸው ማለት ነዉ
ሁልጊዜም ማለት ይቻላል በሰይጣንና በአስማተኛ(በድግምተኛ) መካከል የጋራ ስምምነት ይኖራል፡፡ በዚህ ስምምነት ድግምተኛዉ የክህደትና የሽርክ ሀጢያቶችን በግልፅ ወይም በድብቅ ሊፈፅም እና ሰይጣኑ በበኩሉ ድግምተኛዉን ሊያገለግለው ወይም የሚያገለግለው ሌላ ሰይጣን ሊሰጠው ይስማማሉ።
🔰 የዚህ ዓይነት ስምምነት (ውል) አብዛኛዉን ጊዜ የሚደረገው በደጋሚዉና በሰይጣናት የጎሳ አለቃ መካከል ነው።
የጎሳ አለቃ በሚመራዉ ጎሳ ውስጥ ዝቅተኛ ማዕረግ ያለውን ሰይጣን ከእርሱ ጋር ውል የገባውን ደጋሚ እንዲታዘዘዉ እና እንዲያገለግለዉ ያደርጋል፡፡
↪️ ለምሳሌ
>> የተከሰቱ ድርጊቶችን በመንገር፣
>> ሰዎችን በማጣላት፤
>> መስተፋቅር በመስራት፣
>> ባል ሚስቱን ከመገናኘት በማሰናከል እና ሌሎች ችግሮችን ወዘተ ጉዳዮችን እንዲፈፅምለት ያዘዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ደጋሚዉ ይህንን ሰይጣን ለሚፈልጋቸው የመተት ሥራዎች ማስፈፀሚያነት ያውለዋል። ሰይጣኑ አልታዘዝ ካለው ክህደት ያዘሉ እና የሰይጣናት የጎሳ አለቃን የሚያወድሱ የድግምት ቃላት በመድገም ወደ ሰይጣናት የጎሳ አለቃ ይቀርባል። ይህም የጎሳ አለቃ አስማተኛውን አልታዘዝ ያለወን ሰይጣን እየቀጣ እንዲታዘዘው ዳግመኛ ያዘዋል : ወይም ሊታዘዘዉና ሊያገለግለው የሚችል ሌላ ሰይጣን ይሰጠዋል፡፡
ሰይጣኑ ደጋሚዉን የሚያገለግለዉ ተገዶ በመሆኑ ስራውንም ሆነ ደጋሚዉን በእጅጉ ይጠላል፡፡ በዚህም ሳቢ በደጋሚዉና በአገልጋዩ ሰይጣን መካከል ያለዉ ግንኙነት በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡ ሰይጣኑ በደጋሚዉ ወይም በጠንቋዩ ሚስት፣ ልጆች፤ ንብረት እና ሌሎች ነገሮቹ ላይ ጉዳት ከማድረስ ወደ ኋላ አይልም፡፡
እንዲያዉም አስማተኛዉ አያዉቀዉም እንጂ በራሱ ላይ ሳይቀር ጉዳት ያደርስበታል፡፡
☞ የማይለቅ የራስ ምታት፣
☞ከፍተኛ የእንቅልፍ እጦት፣
☞በአስፈሪ ሁኔታ እና በድንጋጤ ከእንቅልፍ መባነን እና በመሳሰሉ አንግልቶች ያሰቃየዋል
☞ አንዳንድ ድግምተኞች ልጅ መዉለድ የማይችሉ መሀኖች ናቸዉ ይህም የሚሆነዉ ፅንሱ ገና ከማደጉ በፊት ሰይጣኑ ስለሚገድለዉ ነዉ። ይህ ነገር በድግምተኞች ዘንድ በጣም ከመታወቁ የተነሳ አንዳንድ ደጋሚዎች ልጅ ለመዉለድ ሲሉ የድግምት ስራቸዉን አርግፍ አድርገዉ የተዉ አሉ፡፡
#ክፍል 4⃣
ይቀጥላል....
አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5960