tgoop.com/Islam_and_Science/5955
Last Update:
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉 ሁለት 2⃣
አሁን ባለዉ ተጨባጭ ብዙሀኑ ሰው በሚባል መልኩ አሁን ላይ ድግምትን እንድ normal አድርገው ነው የሚጠቀሙት...እነሸህ ጋር ትልቅ ሰዉ ጋር ወልዮች ጋር እንሂድ እየተባለ ሳያቁት በማወቅም ባለማወቅም እየሄዱ ነዉ ..በማወቅም ባለማወቅም ጤነኛን ሰዉ እያጀዘቡ ይገኛሉ
#ለምሳሌ :- በጀመርኩት ጓደኝነት የፍቅር ጥያቄየን አትቀበለኝ ይሆናል እንዳታሳፍረኝ ብለው የፈሩ ወንዶች ድግምት አሰርተዉ ሴቶችን በድግምት እሱን እንድትወደዉ አድርገዉ የፈለጉት የብልግና ስራ ሲሰሩ ይታያሉ፡፡ የጨዋ ሰው ባህሪ በድንምት ይቀየራል ያ ሰው ምን ነካው?? ጥሩ አልነበረንዴ?? እስከሚባል ድረስ
☞የክፋት ጥግ የሚያሳይ ወንድ
☞ የብልግና ጥግ የምታሳይ ሴት ልጅ
☞ራሳቸዉን ስተዉ ለእብደት የሚጋለጡ ሰወች
☞አላህ የሰጣቸውን ሪዝቅ የተበታተነባቸው
☞ ራስን ለመቻል ሲጥሩ ስኬት የራቃቸው
የድግምት(ሲህር) ተጎጅዎች ብዙ ናቸው ብንል ማጋነን አይሆንም
ታዲያ ይሄ ድግምት ለዚህም ለወዳኛው አለም ታላቁ ሰው ነብዩ ሙሀመድ ካልቀረላቸው በእኛ በኖርማሎቹ ሰወችማ እንዴት ነፃ ልንሆን እንችላለን ??ነቢዩ ሙሀመድንኮ ያዛቸውና እርሳና ላከባቸው ነገሮችን እየደጋገሙ ሲሰሩት ማስታወስ እስከማይችሉ ድረስ በየሁዳ ድግምት ተሰቃዩ መቸም የነሱ ችግር ይዞ የሚመጣው እስከ ኡመቶቻቸው ሁሉ ነው፡፡ አላህ በህማቸው ድግምቱ የተደረገባቸውን ቦታ በመላኢኮች አማካኝነት የ ጠቆሟቸው... የነቢይ ህልም እውን ነውና እዚያ ቦታ ሂደዉ ቆፍረው አወጡት ውሀ አፈሰሱበት ከዚያ መፈወሻ ይሆን ዘንድ የቁርአን አንቀፆችን አወረደላቸው እንደዋናነት ለሩቃ ከሚቀሩ አንቀጾች መክቅክል ሱረሩ ኢኽላስና ሙአወዘተይ ናቸው ለዚህም ነው አላህ
✔ በሱረቱሩል ኢክላስ ውስጥ እንዲህ የሚለው
{{ በል እርሱ አላህ አንድ ነው እርሱ አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው አልወለደም አልተወለደም ለእርሱ ለአላህ አንድም ቢጤ አምሳያ የለውም። ይለናል
በዚህ የቁርዐን አንቀፅ ውስጥ ጅኖች በብዙ መልዕክት ተብትበው እና ቋጥረው ገብረው ሰውን አስገብረው ያደረጉትን ድግምት በብቸኛውን አንዱ አላህ ስም ሊፈታ ዘንድ ይህ የቁርዐን አንቀጽ የወረደው
✔ እንዲሁም በሱርውረቱል ፈለቅ ላይ እንዲህ ይለናል
#በል በፈለቅ ጌታ ጠበቃለሁ ንጋትን ከጨለማ ፈልቅቆ የሚያወጣ ማለት ነው
ከፈጠረው ተንኮል ሁሉ( ተንኮልና ድግምት አጠቃላይ መጥፎ ነገር የተፈጠረው ለፈተና ነው)
ለይሉ ድቅድቅ ብሎ በጨለመ ጊዜ የሚመጣን ተንኮል በአንተ ጠበቃለሁ በል
በክር የቆጣጠሩና የተፋፉ ከሚደግሙ ሴት ድግምተኞች በአንተ እጠበቃለሁ በል
የሚመቀኝው በተመቀኝ ጊዜም ያለን ተንኮል በአንተ እጠበቃለሁ በል ።
#የሰው_ልጅ ወደዚህ አለም ሲመጣ ብዙ አይነት ባህሪ አመንጭ ሆርሞኖች ይኖሩታል
🔸 የሚቀና መንፈስ
🔹 የሚመቀኝ መንፈስ
🔸 የሚወሰውስ መንፈስ
🔹መልካም የሚያስብበት መንፈስ
🔸 መጥፎ የሚያስብ መንፈስ እና ሌሎችም መንፈሶች አሉት፡፡ ታዲያ ሰወች የተንኮል አስተሳሰባቸውን መቆጣጠር ሲያቅታቸው
☞ሸራቸውን ተንኮላቸዉን መርጨት ይጀምራሉ
☞ይመቀኛሉ ይቀናሉ
☞ ጉዳትን ያደርሳሉ
☞ ድግምትን ይሰራሉ የነዚያን ተንኮል ሁሉ እንድንጠበቅ ዘንድ አላህ ይሄንን አያት አውርዶልናል
✔ ሶስተኛዉ አንቀፅ አናስ ነው የሰወች ምዕራፍ ማለት ሲሆን
በሰወች ተንከባካቢ በሆነው አምላካቸው(አላህ) እጠበቃለሁ በል
የሰወች ንጉስ በሆነው አላህ ጠበቃለሁ በል
ሰወች የሚያመልኩት አምላክ በሆነው አላህ ጠበቃለሁ በል (ከምን) ?
☞ ብቅ ጥልቅ በማለት የተመላለሰ ከሚወሰውስ ጎትጓች ተንኮል
ያ በሰወች ልብ ውስጥ ጎትጓች ኮሆነ ተንኮል ። ማነው ጎትጓቹ አካል ካልን?
☞ ከሰወችና ከጅኖች ወስዋሽ ጎትጓች አሳሳቾች።
ይህኛው አንቀፅ ደግሞ መግቢያውን ሀያል በሆነ የአላህ ስራና ባህሪ ከገለፀ በኋላ ከሰወች እና ከጅኖች ውስወሳ ተንኮል ብእሱ እንድንጠበቅ ይነግረናል የአላህ መልዕክተኛም እነዚህን አንቀፆች ደጋግመው ሲቀሩ ነበር የድግምቱ ስሜት ሙሉ በሙሉ የለቀቃቸው
✔ እንደዚሁም ሌላው ትልቁ የሲህርና ጅኖች መጠበቂያ የሆነው አንቀፅ አያተል ኩርሲ ነው አያተል ኩርሲ የአላህን ፍፁምነት የሚገልፅ አንቀፅ ስለሆነ አንድ ሰው እሱን ቀርቶ ከቻለ ውዱዕ አድርጎ( ባያደርግም )ከተንቀሳቀሰ ምንም አይነት ነገር አይጎዳውም
ማታ ሲተኛ ቢያነበው ሰይጣንም ይሁን ጅን አይቀርቡትም ቢቀርቡትም እንኳን እሱን የመጉዳት አቅም ይነፈጋሉ በዚያው አጀሉ ደርሶ ቢሞት ደግሞ አላህ ጀነትን ይወፍቀዋል
ሌላው ራስን ከእንደዚህ አይነት አደጋ ሊጠብቅ ሰበብ የሚሆነው ውዱዕ አድርጎ መንቀሳቀስ ነው ውዱዕ ማድረግ ሰይፍን ስሎ ወይንም በጣም ተጠንቅቆ እንደመሄድ ስለሚቆጠር ማንም ድግምት አድራጊ ለማድረግ ቢሞክር የውዱዑ በረካ ሰውየውን እንዳይጎዳው አላህ ሰበብ ያደርግለታል
🟢 እንዲሁም ሰወች መጥፎ ስሜት ሲሰማቸው ፍዘት ድብርትና የተለያዩ ነገሮች ድንገት ሲመጡባቸው ውዱዕ እንዲያደርጉ ይመከራል በቶሎ ከዚያ ስሜት ያወጣቸዋል፡፡ ከውዱኡ ጋር ሳይለያይ የሚመጣው ጉዳይ ደግሞ ሲዋክን ማዘውተር ነው ሲዋክ መጠቀም ጅንና ሰይጣንን ያርቃል ንፅህናውን ጠብቆ ንፁህ አፍ የያዘ ሰው በሲህር ተንኮል የመጠቃት ሀይል የለውም
✅ መተት ሲህር መኖሩን ማረጋገጫ ከነብዩ ሰዐወ ህይወት ጀባ ልበላችሁ፡፡
ዓኢሻ (ረዐ) እንዲህ ብለዋል፡- በኒ ዘረይዎ ከሚባል ጎሳ የተወለደ ለቢድ ኢብን አል አሪሶም የተባለ ሰው በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ደገመባቸው፡፡ በመተቱ ሳቢያ አንድን ነገር ሳይሰሩት የሰሩት ይመስላቸው ነበር
አንድ ቀን እኔ ቤት ሆነው ሳለ አላህን (ሱ.ወ) በጣም ለመነና እንዲህ አሉኝ፡ ዓኢሻ ሆይ! ስለለመንኩት ጉዳይ አላህ ልመናዬን እንደተቀበለኝ ታውቂያለሽን? ሁለት መላኢኮች ወደ እኔ መጡ፤ እንዱ በራሴ በኩል ተቀመጠ፡፡ ሌላኛዉ በእግሬ በኩል ተቀመጠ፡፡ ከዚያም አንዱ ለሌላኛው እንዲህ አሉ፡- "የዚህ ሰውዬ : ህመም ምንድን ነዉ? ሌላኛውም፦ “ተደግሞበት ነው አለ፡፡ የመጀመሪያዉም፡-ማን ነዉ የደገመበት?' ሲል ጠየቀ:: ያኛዉም፡- ለቢድ ኢብን አዕሶም የተባለ ሰው ነው መለሰለት፡፡ የመጀመሪያዉም፡- ሲል "በምንድን ነዉ (መተቱ) የተሰራዉ? ሲል ጠየቀ፡፡ ያኛዉም፡- በማበጠሪያ፣ ማበጠሪያው ላይ ባለዉ ጸጉራቸዉ እና በወንዴ የተምር ፍሬ ገለባ' ሲል መለሰ::
የመጀመሪያዉም (መተቱ) የት ነዉ ያለዉ?' ሲል ጠየቀ፡፡ ሌላኛዉም፡- ዝርዋን በምትባል የውሀ ጉድጓድ ዉስጥ ሲል መለሰለት፡፡ ከዚያም ነቢዩ (ሲዐ.ወ) ከጥቂት ባልደረቦቻቸዉ ጋር ሆነዉ ወደ ጉድጓዳ ሄደው ሲመለሱ እንዲህ አሉኝ “የጉድጓዱ ውሀ ልክ እንደተዘፈዘፈ የሂና ቅጠል (ደም) የመሰለ ነው። የቴምር ዛፏ አናቶች ደግሞ የሰይጣናት ራስ መስለዋል አስቀያሚ ናቸው:: እኔም፡- “(ድግምቱን) አታስወጡትም ነበር? አሰኳቸው፡፡ እሳቸዉም፤- በርግጥም አላህ አድኖኛል፡፡ በሰዎች ዉስጥ ተንኮል አንዲስሩሩ አልፈልግም አሉ ፡፡›› (ቡኻሪ ዘግበዉታል)👇👇
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5955