tgoop.com/Islam_and_Science/5952
Last Update:
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉 አንድ 1⃣
⚡️አንዳንድ ሰዎች የጂኒዎችን መኖር ክደዋል በዚህም ምክንያት መተት የለም ይለሉ፡፡
ግን በመተትና በጂኒዎች መካከል ጥብቅ ቁርኝነት አለ ..ጂኒዎችና ሰይጣናት የመተተኛ አይነተኛ ተዋናያን ናቸዉ፡፡
ጂኒዎች ከሰዎች እና ከመላኢካዎች የተለዩ ዓለም አላቸዉ፡፡ ማሰብ የሚችሉ አዋቂ ፍጡራን ናቸው ፡፡
በመርፌ ቀዳዳ መሹለክ የሚችሉ በሰዉ ደም ዝዉዉር ዉስጥ መንቀሳቀስ የሚችሉ ፍጥረት ናቸዉ፡፡
የሰዉ ልጅ ትክክለኛዉን እምነት መርጦ የመከተል ነፃ ፈቃድ እንዳለዉ ሁሉ ጂኒዎችም አላቸዉ፡፡ከሰዉ የሚለዩበት ዓይነተኛዉ መለያ የተፈጠሩት ከእሳት መሆኑና እነርሱ የሚያዩን እኛ የማናያቸዉ የመሆኑ ጉዳይ ነዉ፡፡
🔰 ከጂኒዎች ዉስጥ ተንኮለኛና ሰዎችን ወደተሳሳተ መንገድ የሚመሩት ሸይጧን ተብለዉ ይጠራሉ፡፡ ስለሆነም ሸይጧን ሁሉ ጂኒ ነዉ ነገር ግን ጂኒ ሁሉ ሸይጧን አይደለም፡፡
እናም ጂኖች መኖራቸዉን ከቁርአን ማስረጃ
☞ከጋኔን የኾኑን ጭፍሮች ቀርአንን የሚያዳምጡ ሲሆኑ ወደ አንተ ባዞርን ጊዜ አስታዉስ (አል-አህቃፍ 29)
በተጨማሪ
☞ አል-ረህማን 33
☞ አል-ጂን 1
☞አል-ማኢዳህ 91
☞ አል-ኑር 21
እንዲሁም በቁርአን ጂኒ የሚለዉ 22 ቃል ጊዜ...ጂኒዎች የሚለዉ ቃል 7 ጊዜ...ሰይጣን የሚለዉ ቃል 68 ጊዜ ...ሰይጣናት የሚለዉ ቃል 17 ጊዜ ተጠቅሰዋል፡፡
✅ አላህ በቁርአኑ እንደተናገረዉ
>>> ሰወች በነቢዩ ሱለይማን አለይሂ ሰላም የስልጣን ዙፋን በነበረው ነገር ተከተሉ ሱለይማን ደጋሚ አልነበረምና አልካደም ሰይጣኖች ግን ደጋሚ በመሆን በአላህ ክደዋል ይለናል
ነቢዩ ሱለይማን በምድር ላይ ስልጣንን በሰፊ እንዲቆናጠጡ ፈቅዶላቸው ነበረና ሰውን እንሰሳውን ጅኑን ተቆጣጥረው ያስተዳድሩ ነበር፡፡
ከእለታት አንድ ቀን በጅኖች አለም ድግምትን በመስራት ለሰወች በማስተማር እጅግ የተጠመዱበት ዘመን ነበረና ይህንን ተንኮል ለማስቆም ነቢዩ ሱለይማን የድግምትን መዛግብት በሙሉ ከጅንም ከሰውም ያለውን አሰባስበው በማይደፈረው ሱልጣናቸው ወንበር ስር ቀበሩት፡፡ ምክንያቱም የእምነት መፅሀፍ የተቀላቀሉ ቃላቶች ስለነበሩ ምናልባት በዚያ ዘመን ማቃጠል የማይቻልበት ዘመን ይሆናል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ዙፋናቸውን ማንም አይደፈረውም ጅኖች ከተጠጉት ያቃጥላቸዋል በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ነቢዩ ሱለይማን ህይወታቸው አለፈ፡፡
አመታት ተተካኩ ተንኮል ተንሰራፋ የሰይጣን ውስወሳ ጀመረ ...ሰወች ዳግም ሲህር ስለሚባለው ነገር ማሰብ ጀመሩ በዘመኑ የነበሩ የጅን ገባሪ ሰዎች በቂ የድግምት መረጃ በማጣታቸው ጅኖችን አማከሩ ጅኖች ደግሞ እኛ ብንነካው የሚያቃጥለን የድግምት እውቀት ታሽጎ የተቀመጠው የነቢዩ ሱለይማን ዙፋን ስር እንደተቀበረና ከሰዎች ውጭ ሌላ አካል ሊነካው እንደማይችል ለሰወች በመንገር ከነቢዩ ሱለይማን ዙፋን ስር የተቀበረውን የድግምት መፅሀፍ ሰወች አውጥተው ለጅኖች እንዲሰጧቸውና.... ጅኖች እዚያ ላይ ያለውን ነገር በማየት የተሻለ ድግምት ሊያደርጉላቸው እንድሚችሉ ለሰወች አሳምነው መፅሀፉን አስወጡት ይባላል፡፡
በሰወች የወጣውን የድግምት መፅሀፍ ጅኖች ተቀብለው የተለያዩ ድግምትን እንደ አዲስ አንሰራፍተው ማስተማር ማድረግ ጀመሩ፡፡
ለዚያም ነው በቁርአኑ ውስጥ ሱለይማን አልካደም ሰይጣኖች ግን ክደዋል ምክንያቱም ሰወችን ድግምት ያስተምራሉ የሚያስተምሩት ድግምት ደግሞ በሁለት ማላኢካዎች አማካኝነት ባቢሎን በሚባለው ምድር ሀሩትና ማሩት የተባሉ መላኢኮች ሰወችን ለመፈተን በማስተማር ሲመጡ ሰወች ተማሩ እነዚያ ማላኢኮች አንድንም ሰዉ አያስተምሩም ከማስተማራቸው በፊት እኛኮ ይሄንን የምናስተምራችሁ ለፈተና ነው አልማርም ይሄንን ተግባር ያለ አማኝ ነጃ ወጣ የተማረ ግን በፈተና ውስጥ ወደቀ በማለት ይብራሩላቸው ነበር፡፡
✅ በነወዊ ተፍሲር ደግሞ ሀሩትና ማሩት መላኢካዎች ሳይሆኑ ሁለት ንጉሶች ናቸው በማለት ይፈስሩታል ግን አብላጫዉ ለፈተና የተላኩ መላኢኮች ናቸው የሚል ያመዝናል... አሏሁ አዕለም.... እናም ከማስተማራቸው በፊት እኛ ፈተናዎች ነን ይህን ተምረህ አትካድ በማለት ይናገራሉ ፡፡ ሰዎችም ከሁለቱ የሚማሩት ነገር ባልና ሚስትን አጣልቶ ትዳርን የሚበትን ድግምትን ነው ግን ይሄንን ማድረጋቸው አላህ ካልፈቀደ በስተቀር ማንንም መጉዳት አይችሉም ይለናል አላህ በቁርዐኑ....
✔ አላህ የሚወደዉንም የማይወደዉን ይፈትነዋል...
ሲህር ድግምት እንኳን በሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ አሰርተዉባቸዋል እናም ነብዩ የተፈተኑበትን እኛም ተራ ሰዎች በየደረጃዉ ሊፈትነን ይችላል፡፡
ግን ድግምቱ ቢሰራ ቢላክ አላህ ኩን ካለለዉ የፈለገዉ ጠንቋይ ምንም እኛ ጋር ቢሰራ ቢልክ ምንም አያደርገን....
✔ ማወቅ ያለብን ነብዩላህ ኢብራሂም የተቀጣጠለዉ እሳት ለብዙ ቀናት ማቀጣጠያ ተሰብስቦ ሲቀጣጠል የተቀጣጠለዉ እሳት በሰማይ የምሄድን በራሪ ያስቀር ነበር እናም ነብዩላህ ኢብራሂምን በሩቅ በወስፈንጠር ላካቸዉና እሳቱ ሙሀል ቢገቡም አላህ ግን እሳቱን በርደን ወሰላማ አላ ኢብራሂም ብሎ እሳትን አዘዛት እናም እሳቱ ነብዩላህ ኢብራሂም እሳቱ ምንም ሳያደርጋቸዉ ቀረ...በርደን ብሎ ወሰላማን ባይጨምር ኑሮ ብርዱን አይችሉትም ነበር ብለዋል፡፡
☞ ነብዩላህ የኑስ አሳ ሆድ ዉስጥ ኑረዋል እናም አላህ የወሰነዉ ነዉ የሚሆነዉ....
በነብዩላህ ኢብራሂም ታሪክ ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ ... ሰዎች አንተን አንቺን ለመጉዳት ብለዉ ጠንቋይ ቤት ቢሄዱ ቢያሴሩ ቢጠቋቆሙ በመቶዎች በሺዎች ሁነዉ ክፋትን ቢያስቡ አላህ ከጎንህ ካለ በእሱ ተወከል ካለህ ስታገኝም ስታጣም ሲከፋህ ስትደሰትም ሚስጠራኛህ መመኪያህ አላህ ከሆነ ለምን ትንኮላቸዉ የተራራ ያህል ቢሆን አንተን አንቺን አይጎዳም ግን ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት መፈተሽ አለብን
🌀 በተዘዋዋሪ አላህ የሚወደዉን ባሪያ ይፈትነዋል ለምን ዱንያ የትንኝ ያህል ክንፍ ቦታ ስለሌላት አንዳንድ በደጋሚዎች በጂኖች ተልከዉ ሲመጡ በእኛም መዘናጋት ተጠቅመዉ አላህም እስኪ ባርያየን በዚህ ሙሲባ ይሸነፋል ወይስ እኔን ይዞ በኔ ተወክሎ በኔ ቃል ቃርአንን ይዞ ታግሎ የጠንቋይን የሳሂርን ትብትብ ያሸንፍ ወይም ታሸንፍ ይሆን?? ብሎ ሊፈትነን ይችላል፡፡ ይሄን ጊዜ ወደ ቁርአን ወደ ዚክር እንድንመልስ አላህ ጋር ያለንን ግንኙነት ጠበቅ አድርገን እንድንይዝ ሊያስታዉሰን ኢማናችን እንዲጨምር መልሶ እድሉን እየሰጠን ሊሆን ይችላል፡፡
ነብዩ ሰዐወ በሀዲሳቸዉ አላህ በጠረጠራችሁኝ ቦታ ታገኙኛላችሁ ብሏል እናም
🔸 ነገሮች አልሳካ ሲሉ በስራ ስንፍና ምክንያት ስንከስር👇👇
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5952