ISLAM_AND_SCIENCE Telegram 5931
በፈረንጆቹ በ1950ዎቹና በ1960ዎቹ አካባቢ የሴት ፍላጎት፣ መብትና ነፃነት አይደለም ሊከበር ቀርቶ አልታሰበም ነበር፡፡ ሴት ልጅ ያገባች ከሆነ የባሏ አገልጋይ፤ ለትዳር ካልደረሰች ደግሞ የእናቷ ረዳት፤  ወግ ሳይደርሳትና ዕድል ሳይገጥማት ሳታገባ ከቆየች ወይም ፈት ከሆነች ደግሞ በማህበረሰቡ የስድብ ናዳ ይወርድባታል፣ ትናቃለች፣ ትገለላች፡፡ ሴት ሆኖ መፈጠር ምን ያህል ከባድ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፡፡ በአሜሪካ እንኳን እ.ኤ.አ. በ1950 ዓ.ም. የነበረው ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተዘጋጀውን የኑሮ በዘዴ መማሪያ መፅሐፍ (Home Economics text book) ብናይ ያገባች ሴት የባሏን ፍላጎት እንዴት ማሟላት እንዳለባት የሚያስተምርና የሚተነትን ነበር፡፡ ሴት ግዴታዋና ሃላፊነቷ የበዛ ነገር ግን መብትና ነጻነቷ ያነሰ፤ ምንም ምርጫ ያልነበራት እንደነበረች እናቶቻችንን ማየት በቂ ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ በዘመናችን ያለችው ሴት በእናቶቻችን ዘመን ከነበሩት ሴት በብዙ መልኩ ትለያለች፡፡ ትናንት ፍላጎቷ የማይከበርላት፤ ዛሬ በአንድም በሌላም መንገድ ፍላጎቷ ይከበርላት ዘንድ አቅምና ጊዜ አግኝታለች፡፡ የዘመናችን አንገብጋቢውና አሳሳቢው ጉዳይ ግን ሴቶቹ ራሳችን የምንፈልገውን ነገር አለማወቃችን ነው፡፡ ራሳችንን አለማወቃችን የወንዶች ብያኔ ተጠቂ እንድንሆን አድርጎናል፡፡ ለጉብዝናችን ወይም ለቁንጅናችን የምስክር ወረቀት የምናገኘው ከወንዶቹ ነው፡፡ በዛም አለ በዚህ የወንዶች ስነልቦና ተጠቂ ሆነናል፡፡ በኢኮኖሚ ራሳችንን እየቻልን ብንመጣም በአስተሳሰብ ግን አሁንም የወንዶች ጥገኛ ነን፡፡ ራሳችንን በምግብ ብቻ ሳይሆን በሃሳብም ካልቻልን ከወንዶች ጭቆና አንተርፍም፡፡

መቼስ ሴትን እንደ እንደስነልቦና ምሁሩ ሲግመንድ ፍሮይድ ያጠናት የለም፡፡ ሰውየው ሴት ልጅ ገና ከልጅነቷ ጀምሮ ምን ዓይነት አስተሳሰብና ባህሪ ሊኖራት እንደሚችል፤ እንዲሁም ትክክለኛ ፍላጎቷ ምን እንደሆነ ለማወቅ የተመራመረ ነው፡፡ ለዚህ ነው ‹‹ሴት የምትፈልገው ምንድነው? What do women want›› በሚለው ጥያቄው የሚታወቀው፡፡

ሴት በሴት መቀናናት ያለ ነው፡፡ የማታስቀናም የማትቀናም ሴት የለችም፡፡ ሴት በወንድ ስትቀና ግን ሊያስገርም ይችላል፡፡ ፍሮይድ ይሄን በተመለከተ አንድ ጥናት ነበረዉ፡፡ ይሄ ጥናት ሴት ገና ከአፍላ እድሜዋ ጀምሮ አጎጠጎጤዎች ስታወጣ፣ የመራቢያ አካሏ እየዳበረ ሲመጣ፣ ለአቅመ ሔዋን ስትደርስና እንደ ወንድ አለመሆኗን ስታውቅ በወንዱ መቅናት ትጀምራለች ይለናል፡፡ መቅናት ከሴት ተፈጥሮ ጋር የተዋሃደ ይመስላል፡፡ ይሄ የስነልቦና ተመራማሪ ስለሴቶች ባህሪ ለማወቅ ብዙ ጥናቶችን ቢያከናውንም ሴቶች ግን እንቆቅልሽ እንደሆኑበት ነው ህይወቱ ያለፈው፡፡ የሚገርመው ሴት ልጅ አይደለም ለወንዱ ለገዛ ራሷ ግራ አጋቢ ፍጥረት መሆኗ ነው፡፡ ኤቭሊን ሌት (Evelyn Leite) የተባለች ታዋቂ የስነልቦና አማካሪ “Women” በተባለ መፅሐፏ ‹‹ፍሮይድ -- ሴት ምንድነው የምትፈልገው? -- የሚለው ጥያቄው ወንዱን ብቻ ሳይሆን ሴቷ ራሷ መልስ ያጣችለት ነው፡፡ (Freud’s question – What do women want – frustrates men, It also frustrates women)›› በማለት ትገልጻለች፡፡

ብዙዎቻችን ሴቶች ባላችን ወይም ምን እንዲያደርግልን ከመፈለጋችን በፊት እኛ የምንፈልገውን ቀድመን ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡ ሚስቶች ከባሎቻችን የምንፈልገው ነገር ብዙ ነው፡፡ ነገር ግን የምንፈልገውን ነገር በግልጽ አናውቀውም፡፡ ባሎችም ሚስቶቻቸው ምን እንደሚፈልጉ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን የሚስቶቻቸው ፍላጎት በየጊዜው የሚለዋወጥ በመሆኑ ግራ ተጋብተዋል፡፡ ሴት የራሷን አካላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ስሜታዊ እና ሌላም ፍላጎቷን ለይታ ካላወቀች እንዴት ብሎ ነው ባሏ ፍላጎቷን ሊያሟላ የሚችለው? ብዙዎቻችን ሴቶች ለይተን ባላወቅነው ፍላጎታችን ወንዶችን ተጠያቂ እናደርጋለን፡፡

ግራ የሚያጋባ ነዉ.....

tgoop.com/Islam_and_Science/5931
Create:
Last Update:

BY ISLAMIC SCHOOL

Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5931

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Write your hashtags in the language of your target audience. Clear The public channel had more than 109,000 subscribers, Judge Hui said. Ng had the power to remove or amend the messages in the channel, but he “allowed them to exist.” With the “Bear Market Screaming Therapy Group,” we’ve now transcended language. To delete a channel with over 1,000 subscribers, you need to contact user support
from us

Telegram ISLAMIC SCHOOL
FROM American