tgoop.com/Islam_and_Science/5811
Last Update:
ትምህርት ጀመርን እኔም መማር ጀመርኩኝ...አባቴም ዩኑፎርም የለም እኮ ልብስ ጫማ እና ፓርሳ መቀያየሪያ መግዣ ብር እያለ በጣም ብዙ ብር ይሰጠኛል......በዚህም ብር በጣም የሚያማምሩ ጫማዎች ልብሶች ፓርሳዎች ስለገዛሁኝ እቀያይራለሁ፡፡ በኔ ዉበት የተነሳ የትምህርት ቤት ወንዶች እኔን አይቶ ምራቁን የማይዉጥ ወንድ የለም ..
የሚገርማችሁ ኮሌጅ ለራሱ ገብቼ የአእምሮ ዲፕሬሽን አለቀቀኝም ከሰዉ ጋር አልቀላቀልም ብቸኝነት ምርጫየ ነዉ ከክላስ ዉጭ ላይብረሪ ነዉ የማሳልፈዉ...በዚህ ፊልድ ጥሩ ዉጤት ለማምጣት ቸክየ እየተማርኩ ነዉ
ወንድም ሴትም እኔ ጋር ጓደኛ መሆን ይፈልጋሉ ለምን በትምህርቴም ጎበዝ ስለሆንኩ ብዙ ሰዉ ጓደኛ እንሁን ይሉኛል ..ግን እኔ 10ክፍል ላይ መጥፎ ጓደኞች ሒወቴን ስላበላሹት ..አሁን ያሉት የሴትም የወንድም ጓደኞች እኔ በራሴ መፈተኛ ስፈተናቸዉ አይመጥኑኝም፡፡ ሴቶቹ ወሬያቸዉ አመለካከታቸዉ..ለትምህርት ያላቸዉ አመለካከት እንደ ጊዜ ማሳለፊያ ስለያዙት እነዚህ የክላስ ልጆች ጋር አብሮ ጓደኛ መሆን ልቤ አልፈቀደልኝም፡፡ትምህርቴ ላይ ጎበዝ ሆንኩኝ ስለማጠና የሚያስተሞሩን መምህሩ ጋር በጣም ተግባባን ፡፡
አንድ ቀን እኛ ክላስ አንዲት ጅልባብ የምለብስ ልጅ ስሟ መፍቱሀ ትባላለች ደግሞ አንዲት ክርስቲያን ልጅ አለችኝ ስሟም ብሩክታይት ትባላለች ሁለቱ አንድ ላይ መጥተዉ ከአንቺ መተዋወቅ እንፈልጋለን ብለዉ እጃቸዉን ዘረጉ....
ብሩክቲን አንግባባም እንጂ አቃታለሁኝ የእኔ እናት እና የእሷ እናት ጓደኛ ናቸዉ፡፡ ክላስ ዉስጥ ሁለታችን እንፎካከራለን ....መፍቱሀ ግን ሰነፍም ጎበዝም አትባልም መካከለኛ ናት ፡፡
......እኔም እሺ እልኩኝ
..... መፍቱሀም:- ሁሌም አንቺ ጋር መተዋወቅ እንፈልጋለን ዛሬ ደፍረን ለመተዋወቅ እኛዉ መጣን በጣም አድናቂሽ ነን ለትምህርትሽ ያለሽ ትኩረት በጣም አስደሳች ነዉ ለአላህ ብየ እወድሻለሁ ከአሁን ቡሀላ አንቺም ለአላህ ብለሽ ዉደጅኝ አለችኝ መፍቱሀ
......እኔም 10Q ችግር የለም ከአሁን ቡሀላ ጓደኞች እንሆናለን አልኳቸዉ
.....መፍቱሀም ስልክ ቁጥር እንለዋወጥ አንዳንዴ እንደዋወላለን አለችኝ....
ስልክ ቁጥሬን ሰጠሆት የሷንም Save አረኩት..አብሬም ለብሩክቲ ስልኬን ሰጠሆት
ስልኬን ልስጣቸዉ እንጂ ብዙም ትኩረት አላረኩም ለምን እስከ 10 በምማርበት ጊዜ ለኔ ሒወት መንገድ መሳት መጥፎ የሙስሊምም የክርስቲያንም ጓደኞች ነበሩኝ እነ መፍቱሀም ከዚህ ዉጭ ምንም አስቤ አላቅም
መፍቱሀ በቀን ሁለቴ ሶስቴ ትደዉልልኛለች የምናወራዉ ስለትምህርት በተጨማሪም ስለ ቂርአት እሷ የተለያዩ ኪታቦች እንደቀራች እና እኔም ቂርአት እንድቀራ ትመክረኛለች....,መፍቱሀ ሁሌም አብሽሪ ኪታብ መቅራት እኮ ቀላል ነዉ እኔ ስቀራ ብዙ አመት አልፈጀብኝም እያለች ...እየቀለደች እየሳቀች ሒወቷን ታጫዉተኛለች
አንድ ቀን መፍቱሀ ወደ አሱር አካባቢ ደወለችልኝና ነዋል ዛሬ ይዤሽ የምሄድበት ቦታ አለኝ እንገናኝ አለችኝ
.....እኔም እሺ አልኳት
....አሱርን ሰግደን ተገናኘን .... የት ነዉ የምንሄደዉ ብየ ሳልጠይቅ ወደ ምትሄድበት አብሬ ሄድኩኝ
....ጅማ ሪፈራል ሆስፒታል ሂደን የታመሙ ሰዎችን ዘይረን፡፡ ከሆስፒታል ስንመለስ በሌላ አካባቢ ወስዳኝ አቅማቸዉ የደከሙ ትላልቅ ሰዎች በስራ አግዘን እና ትንሽ ብር ሰጥተን እነሱም መርቀዉን ተመለስን፡፡ መፍቱሀ ከትምህርት ሰአት ዉጭ ዛሬ የምንሄድበት አለ እያለች ኸይር መስራት የቲሞችንን ጧሪ ቀባሪ የሌላቸዉን አዛዉንት የሆኑትን መዘየር ሁኗል ስራችን ...
የእኔ ቤተሰቦች ሀብታም ስለሆን ድህነትን አላቀዉም የተቸገሩ መኖራቸዉን ድህነት እንዴት ሰዉ እንደሚጎዳ ዘያራ በምንሄድበት ጊዜ አስተዋልኩኝ ...እኔም ልብስ ግዢ ጫማ ግዢ ተብሎ ከሚሰጠኝ ብር ላይ ለተቸገረ መስጠቱ ለኔ ደስታ ሆነኝ፡፡
መፍቱሀ የሴቶች ጀመአ አሚር ናት በወር በወር በመዋጮ የተቸገሩትን መርጠዉ ቋሚ የብር ወይም የአስቤዛ እርዳታ ይሰጣሉ .....እስኪ ሂደን አይተናቸዉ እንምጣ ትለኛለች...አብረን ሂደን ዘይረን እነሱ ጋር ተጫዉተን ብርም ከያዝኩኝ ለአንዳንድ ነገር ይሁናችሁ እያልኩ ብር ሰጥቼ እመጣለሁ.....
እኔም መፍቱሀ ጋር በዚህ የተቸገሩትን ዘያራ በምናደርግ ሰአት እራሴን እንድፈትሽ ከኔ የባሱ ብዙ መኖራቸዉን አስተዋልኩኝ..አልሀምዱሊላህ አልኩኝ..ከኔ ጀምሬ የበታችንን ብናይ አመስግነን ባልጠገብን ነበር ግን ምነ ይደረጋል የሰዉ ልጅ ዘንጊ ነዉ እንጂ በየእለት ተግባራችን ሰንት የማንሰማዉ የማናየዉ የለም ግን ስናመሰግን አይስተዋልም፡፡
ለመሆኑ ስንቶቻችን ነን በምንመለከታቸዉ የለያዪ ትዕይንቶች ልባችን ተነክቶ የአላህን ዉለታ አስታዉሰን የምናመሰግነዉ??? ወይም የምስጋና ሱጁድ የምናደርገዉ? ጥያቄዉ ለሁላችንም ይቆይ ራሳችን መልሰን እኛዉ እንረመዉ....
መፍቱሀ ለኔ ኸይር እንስራ እያለች የምታበረታታኝ ነች፡፡ አንዳንዴም ብሩክቲም አብራን ትመጣለች...ብሩክቲ ክርስቲያን ትሁን እንጂ አለባበሷ አስተሳሰባ እንደሙስሊሞች ነዉ፡፡ ክሪም ለብሰን ፀጉራችን ከታየ ሸፍኑ ፀጉራችሁ እየታየ ነዉ ትለናለች... የቱርክ የዱባይ ጠባብ ልብስ ለብሰን ስንሄድ ይሄ እኮ ሰዉነት ያሳያል ሒጃብ ልበሱ የምትል ...,አንዳንዴ የሶላት ሰአት ደርሶ እሺ እንሰግዳለን እያልን ወሬ ስናወራ መጀመሪያ ስገዱ እያለች ትገስፀናለች፡፡ ይገርማል የብሩክታያት ቅርብ ጓደኛዋ መፍቱሀ ብቻ ናት .ብሩክቲን የኢስላምን አደብ አስተምራታለች ፡፡
መፍቱሀም እኔን እኛ ጀመአ መግባት አለብሽ የምንገናኛዉ በሳምንት አንዴ ነዉ እያለች ብዙ ጊዜ ነገረችኝ..
...,,እኔ ሰዉ ጋር መቀላቀሉ ሌላ ጓደኛ መፍራቱን አልፈለኩም ግን መፍቱሀ ግድ እኛ ጀመአ ገብተሽ የዲን እህቶሽን ተዋዉቀሽ ኪታብ መጀመር አለብሽ እያለች ሁሌ ስለምትናገረኝ.....እሺ ቅዳሜ እንሄዳለን አልኳት
.......ቅዳሜ ደረሰ መፍቱሀ ጋር አብሬ ሬፍት ቫሊ ኮሌጅ በቅርብ ርቀት የሚገኘዉ ዓሊይ መስጊድ ጀመአቸዉ የሚገናኙበት ሄድኩኝ.....
በፊት አስረኛ ክፍል ስማር በመጥፎ ጓደኞች ተተብትቦ አላማየን እንዳልሳትኩኝ ዛሬ ኮሌጅ ላይ ደግሞ እንደ መፍቱሀ እና ብሩክቲ አይነት ምርጥ እህቶች እና ጓደኛ ሰጥቶኝ ...ትክክለኛ መስመር የያዝኩ ሁኛለሁ ኢስቲቃማዉን ይስጥሽ በሉኝ....
#ክፍል 1⃣3⃣
ይ......ቀ.......
......ጥ......ላ........ል
JOIN
´ www.tgoop.com/Islam_and_Science
www.tgoop.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5811