tgoop.com/Islam_and_Science/5802
Last Update:
ለነገሩ አይፈረድበትም አባቴ እዉነቱን ነዉ ከሁላችንም ልጆች እኔን በጣም ይወደኛል በፊት ጀምሮ አንቺ ባትኖሪ ይሄ ቤት እስከ አሁን ትዳሩ ይፈርስ ነበር ብዙ ቀን ብሎኛል፡፡
አባቴም ይሄንን ሀሳብ ከአጎቴ እንደሰማ ..,በሚቀጥለዉ ቀን አዲስ አበባ መጥቶ ወደ ጂማ ወሰደኝ....እኔን በዚሁ የምለየዉ ነዉ የመሰለዉ ...ነዋል ሁሌም ቢሆን ከጎኔ እንድትርቂኝ አልፈልግም አለኝ....
ሀምሌ ነሀሴ ክረምቱ ብርዱ አልፎ መስከረም ተተክቷል ትምህርት ተከፈተ ጓደኞቼ እየተማሩ ነዉ ፡፡
እኔ ግን ከቤት መዉጣት የለ እንደበፊቱ ጓደኞቼ ጋር መገናኘት የለ እቤት ታሽጌ ተሸሽጌ መዋል ጀምሪያለሁ.....በቃ ብዙ ነገር አስጠላኝ በሒወቴ አዘንኩኝ....አላህ ጋር በመጣላት ትልቅ ጦርነት ጀመርኩኝ ቀዷ እና ቀደር ነዉ ብየ መቀበል ሲገባኝ አላህን የተለያዩ ነገሮች እያነሳሁ ማማረር መዉቀስ ጀመርኩኝ...አላህን እንዴት ለምን እያልኩ ጥያቄ በጥያቄ ሁንኩኝ ይሄ ሁላ ፈተና ለኔ ለምን?? አልኩኝ....
>>>>ጓደኞቼ ማግባት ቢፈልጉ ትዳር ልመስርት ቢሉ የሚፈልጉት ነገር አላቸዉ ይሄዉም የሚፈለገዉ ድንግልና ነዉ የሚፈልጉትን ወንድ መርጠዉ ማግባት ይችላሉ ....እኔ እኮ ድንግል አይደለሁም በልጅነቴ አጥቸዋለሁ ..መልክ ቢኖረኝም እንዴት ብየ ነዉ ወንድ ሲጠይቀኝ የማገባዉ ?? በመልክ ብመረጥም ለትዳር ብቁ አይደለሁም ....ሰንት የማቃቸዉ ሴቶች ጂማ ላይ ከትዳር የሚፋቱት ቢክራ አይደለሸም እየተባለች ስትፈታ ስትባረር እያየሁ እንዴት እኔ ተስፋ ወኔ ይኑረኝ ??? ተስፋ ቆረጥኩኝ ደግሞም ወይ ትምህርቴን አልተማርኩ ከአስር ወደኩኝ ብማር እኮ ይሄን የልጅነቴን በደል የምነግረዉ የሚረዳኝ አገኝ ነበር ብየ ብቻየን መጨናነቅ ሆነ ስራየ የአእመሮ ጭንቀት ዲፕሬሸን ዉስጥ ወደኩኝ፡፡
ነብዩ ሙሀመድ ﷺእንዲህ ብለዋል:- በአላህ ዓይን ጠንካራዉ የሆነዉ አማኝ ከደካማዉ ይልቅ የበለጠና የተወደደ ነዉ፡፡ የሚጠቅማችሁን ነገር ለማግኘት ጥረት አድርጉ፡፡አንዳች መጥፎ ነገር ካጋጠማችሁ እርር ኩምትር በማለት "እንዲህ እንዲህ አድርጌ ቢሆን ኖሮ ይህ ነገር አያጋጥመኝም ነበር""አትበሉ፡፡ ከዚህ ይልቅ አላህ የሻዉ ነገር ሆነ ተፈፀመ በሉ፡፡ ""ቢሆን ኖሮ""የምትለዉ አባባል ሰይጣንን ታስደስታለች..ብለዉናል
.....አላህ ባመጣዉ በቀዷና በቀድር እንዳምን ልቦናዉን ማስተንተኑን ይስጥሽ በሉኝ
ከተወሰኑ ቀናት ቡሀላ አባቴ እቤት ነበር.. መኝታ ክፍሌ ሁኜ ተኝቼ ብዙ ነገር እያሰብኩኝ...አባቴ ነዋል ነዋል እያለ ሲጠራኝ ሰማሁኝ ....
...... አባቴ እተቀመጠበት ሳሎን ሄድኩኝ
.......አባቴም ነይ ከጎኔ ቁጭ በይ ዛሬ የማማክርሽ ጉዳይ አለኝ ...ዛሬ የምንማከረዉ ቀልድ አይደለም ስለወደፊት ሂወትሽ ነዉ.......የምጠይቅሽን ተረጋግተሽ ትመልሽልኛለሽ አለኝ..
....እኔም እሺ አልኩት
.......አባቴም ለወደፊት ምንድን ነዉ አላማሽ ?? ምን አስበሻል ?? በግል ኮሌጅ ገብተሽ በዲፕሎማ መማር ነዉ አላማሽ?? ወይስ አጥንተሽ ፕራይቤት ለመፈተን ነዉ ?? ወይስ ብር እና
ስራ ላመቻችልሽ እና ንግድ ዉስጥ መግባት ትፈልጊያለሽ ?? ወይስ ሌላ ያሰብሽዉ ካለ ንገሪኝ....... አለኝ
..........ይሄን ጥያቄ ሲጠይቀኝ ብቻየን ጭልጥ ያለ ሀሳብ ወሰደኝ....ወላሂ በጣም እልክ ተሰማኝ እንዴት እነዛ ሰነፍ ጓደኞቼ አልፈዉ እኔ እወድቃለሁ ?? እያልኩ አእምሮየ ጋር ማመላሰስ ጀመርኩኝ....
ግን መልሼስ ፕራይቤት ተፈትኜ ብወድቅስ ብየ ለሁለት ሀሳብ ተከፈልኩ.....
....አባቴን አሁን ላይ ምንም ማሰብ አልፈልግም መወሰንም አልችልም.... አልኩት
-----------------አባቴም፡- ነዋል ተረጋግተሽ እሰቢበት አንቺ እንድትጨናነቂ አልፈልግም...መማርም ከፈለግሽ ምን መማር እንደምፈልጊ ..ወደ ስራም መግባት ከፈለግሽ ብር ሰጥቼሽ ምን መስራት እንደምፈልጊ ..በተጨማሪም እኔ ካልኩሽ ዉጭ የራስሽ ሀሳብ እቅድ ካለሽ የአንድ ወር ጊዜ ሰጥቸሻለሁ...በአንድ ወር ዉስጥ አስበሽ ወስነሽ ትነግሪኛለሽ አለኝ.....
እኔም እሺ አባቴ ብየ ከአጠገቡ ተነስቼ መኝታ ክፍሌ ሂጄ ተቀመጥኩኝ.....
አባቴ እንዳለኝም አንድ ሀሳብ መጣልኝ....ጓደኞቼ የሚደርሱበት ደረጃ መድረስ አለብኝ ..ስለሆነም አጥንቼ ፕራይ ቤት ተፈትኜ ጥሩ ዉጤት አምጥቼ priparatory መግባት አለብኝ ...የኔ ችግር 10ክፍል ላይ በመጥፎ ጓደኞች ተከብቤ ተተብትቤ ስላላጠናሁ ስላልተዘጋጀሁ ነዉ እንጂ ካጠናሁ ከተዘጋጀሁ እኔ ጎበዝ ነኝ እኮ አቃለሁ...እያልኩ ያሳለፍኳቸዉ ስህተቴ ዋጋ ማስከፈሉን አወኩኝ....10ን ፕራይ ቤት ካለፍኩኝ ቡሀላ ዩኒቨርስቲ መመረቅ አለብኝ የሚል ሀሳብ በአእምሮየ ይደጋገም ይዟል፡፡
ከሁለት ቀን ቡሀላ አባቴ ወስኛለሁ ስለዉ ..ጊዜዉ ገና ነዉ በደንብ እሰቢበት አለኝ... ከአንድ ሳምንትም ቡሀላ ወስኛለሁ ስለዉ አባቴም በጭራሽ ይሄ የፍጥነት ዉሳኔ አይሆንም አንድ ወር ሰጥቸሻለሁ አንድ ወሩ ሲያልቅ እኔዉ ምን ወሰንሽ ብየ እጠይቅሻለሁ አለኝ፡፡
የተሰጠኝ አንድ ወር የማሰብ ጊዜ አለቀ....ከአንድ ወር ቡሀላ አባቴም ጠርቶ ምን ወሰንሽ ????አለኝ
....እኔም አባቴ አጥንቼ ተዘጋጅቼ ፕራይቤት ተፈትኜ ዉጤቴን አሻሽየ 11 ክፍል ለመግባት ወስኛለሁ አልኩት፡፡
....አባቴም ግን በደንብ አስበሽበታል እርግጠኛ ነሽ?? አለኝ
........እኔም አዎ አስቤበታለሁ እርግጠኛ ነኝ አልኩት
....አባቴም እሺ በሀሳብሽ ምንም አልልም ጣልቃ አልገባም ግን ይሄ ሀሳብሽ የራስሽ ሀሳብ ነዉ ..እራስሽ መጀመሪያ አስበሽ ወስኝ ብየሽ ወስነሻል የዘንድሮዉን አመት በአንቺ ሀሳብ በአንቺ ፍላጎት ተስማምቻለሁ፡፡ ነገር ግን በሚቀጥለዉ አመት ግን አንቺ ያሰብሽዉ ባይሳካ ፕራይ ቤት ዉጤት ባይመጣልሽ አንቺ ሒወት ዉስጥ መወሰን የምችለዉ እኔ ነኝ.... የዛን ጊዜ አንቺ ሳትሆኝ እኔ አባትሽን ያልኩሽን ብቻ ነዉ መታዘዝ እና መሆን የምትችይዉ ...በዚህ በኔ ሀሳብ ትስማሚያለሽ አትስማሚም ???አለኝ
.......እኔም ትንሽ ከአሰብኩኝ ቡሀላ በአባቴ ሀሳብ.......
#ክፍል 🔟
ይ......ቀ.......
.....ጥ.........ላ.........ል
: ❀ share
`·. www.tgoop.com/Islam_and_Science
www.tgoop.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5802