tgoop.com/Islam_and_Science/5793
Last Update:
ክረምት አልፎ ስምንተኛ ክፍል ተመዘገብኩ ..ስምንተኛ ክፍል እያለሁ እኛ ክፍል የሚገኙ ሴት ልጆች ኡስማንን ...ነዋልን እወድታለሁ ብልሀል ወይ ?? እሷ እኮ ሁሌ ኡስማን የፍቅር ደብዳቤ ሰጠኝ እወድሻለሁ እለኝ እያለች ትነግረናለች እዉነቷን ነዉ እንዴ ?? ብለዉ ይጠይቁታል
.....እሱ ግን መልሱ ዝምታ ብቻ ነበር
የኛ ክላስ ልጆች በዉሸት እኔ እና ኡስማንን በተለያየ በዉሸቱም በእዉነቱም ወሬ ለማጣላት የማይፈነቅሉት ዲንጋይ የላቸዉ ነበር ..
እነሱም ከእሷ ምን አለህ አንተ እኮ ብዙ ላይፍ ይጠብቅሀል ካልወደድካት ተዋት እያሉ ብዙ ነገር ካሳመኑት ቡሀላ በማላቀዉ ምክንያት በተለያዩ ወሬዎች ኡስማን እኔን ዘጋኝ......ኡስሚ በእኛ ክላስ የተቀነባበረ ወሬ ጆሮዉን ሞልቶ እኔን ጀርባዉን ሰጠኝ...
ኡስሚም በፊት ቁርአን ቤት እንገናኝ ነበር ከቁርአን ቤት ወጥቶ እቤቱ ሸህ ይዞ ኪታብ መቅራት ጀመረ....ትምህርት ቤት ስንሄድ አብረን ነበር የምንመለሰዉ ..አሁን ለብቻዉ በባጃጅ ሁኗል የሚመላለሰዉ ... በሁሉም አጋጣሚዎች እኔን እራቀኝ አንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ኡስማን ጋር ተጣላን...
እኔም ምን አጥፍቼ ነዉ የዘገሀኝ ምን አጥፍቼ ነዉ የተዉከኝ ??? ብየ አልጠየኩትም ዝም ሲለኝ ዝም አልኩት ሲዘጋኝ ዘጋሁት ........ልቤ ፍቅር እንደማይገዛዉ .. ማንንም ወንድ ወደ ልቤ እንደማይገባ አየሁት ..ለምን አንዴ ቶፊቅ ጉድ ሰርቶኛል ..ወንድ እንዳላምን አርጎኛል..........ኡስማን ጋር አብረን በሆንበት ጊዜ ለኔ ባለዉለታየ ብቸኝነት አይሰማኝም ነበር.... እወደዉ ነበር አልክድም ከመዉደዴ የተነሳ አልቅሼም ዱአ አድርጌያለሁ ኡስሚን ለኔ አርግልኝ ብየ ......ግን የኔ ልብ የፍቅር ልብ ማንንም መዉደድ እንደማይችል ተረዳሁኝ......አሁን አንድ ጓደኛ አለችኝ እንደ እኔዉ በልጅነቷ ክብሯን ያጣችዉ ናርዶስ ብቻ ናት.......
የሰባተኛ ክፍል ዉጤቴ መዉረዱ በጣሞ ስላናደደኝ አሁን ሀሳቤ እና አላማየ አንድ እና አንድ፡ብቻ ነዉ ይሄዉም ለሚኒስትሪ ጥሩ ዉጤት ይዞ ማለፍ እና አባቴን ማስደሰት ነዉ የምፈልገዉ.....
ሰምንተኛ ክፍል ላይ ትምህርቴ ላይ ብቻ ፎከስ ማድረግ ብቻ ሁኗል ትኩረቴ .....ከትምህርት ቤት ጓደኞቼም እንደበፊቱ የማይጠቀም የማይጎዳ የጊዜ ማሳለፊያ ወሬ ማዉራት ..አፍ መካፈት ዘመናይ ነኝ ከሚባሉት ከሁሉም ነገሮች እራኩኝ........ አልሀምዱሊላህ ሶላቴን ተከታትዪ ሰጋጅ ሁኛለሁ
ቁርአንም ምላሽ እየቀራሁ ነዉ፡፡
በተጨማሪም ትምህርት ቤታችን ያሉት ጎበዝ ሴት ተማሪዎች ጋር ላይብረሪ እየገባሁ ማጥናት ጀምሪያለሁ፡፡ እራሴን ለመቀየር ወገቤን ጠበቅ አርጌ ተነስቻለሁ... ግራ የገባኝ ነገር ቢኖር እኔ ሳጠና ናርዶስ በጭራሽ አላጠናም አለችኝ ...ናርዶስን ቀን በቀን ተስፋ ሳልቆርጥ ላይብረሪ እንግባ እናጥና ብላት ሁሌም ከአፏ የሚወጣዉ መልስ እምቢታ ብቻ ነዉ፡፡
ናርዶስ የሀብታም ልጅ ናት ቤተሰቦቿ ጅማ ከተማ ላይ ህንፃ እና ታዋቂ ሆቴል አላቸዉ ፡፡
ትጋብዘኛለች ...ናርዶስ ብር በጣም ታባክናለች አባቷ የወጭ እያለ ይሰጣታል ብዙም አያካብድም፡፡ ብር እንደፈለገች ስለሚሰጣት አዳዲስ ልብስ መልበስና የፈለገችዉን ምግብ መብላት መጠጣት የዘወትር ተግባሯ ነዉ ...
ከትምህርት ስንለቀቅ ብዙ ጊዜ ካፌ ትጋብዘኛለች
ናርድስ ስለምታባክነዉ ብር ግራ እየገባኝ ..ተይ ብር መበተኑ ማባከኑን ቀንሽ እያልኩ ሁሌ ብመክራትም፡ የእሷ መልስ ግን እኔ በዚህ ጊዜ የምፈልገዉ እራሴን ዘና አድርጌ መኖር ነዉ የምፈልገዉ በስንቱ ልጨናናነቅ?? መጨናነቅ ይበቃኛል.....በትምህርት ጥናትም መጨናነቅ አልፈልግም ከመጣ ዉጤት ይምጣ ካልመጣም የራሱ ጉዳይ.....ትለኛለች፡፡
አንድ ቀን ናርዶስን ብቻዋን ቁጭ ብላ ጭልጥ ያለ አለም የሄደች ትመስላለች ከአጠገቧ ሂጄ ናርዶስ ናርዶስ እያልኩ ብጠራት ልትሰማኝ አልቻለችም ..ከጎኗ ሁኜ ናርዶስ ብየ ፊቷን ነካ ሳረጋት ከእንቅልፍ እንደባነነ ሰዉ ብንን ብላ ነቃች
...እኔም፡- ግን ለምን እንደዚህ በሀሳብ እርቅሽ እስከምትሄጅ ታስቢያለሽ?? ብቻሽን ተቀምጠሽ በሀሳብ ከምትበታተኝ አብረን ላይብረሪ ገብተን እናጥና ለወደፊት እኔ እና አንቺ በልጅነታችን ህልማችን ቢወሰድም ...ለወደፊት ህልም ያለን ህልማችንን መመለስ የምንችል ልጆች ነን ....ባለፈዉ ስንመካከር እኮ እኛ አርአያ መሆን አለብን ብለን ሁለታችን ቃል ገብተናል ለምን እንደዚህ ተስፋ ትቆርጫለሽ ??? ብዙ ጊዜ ብር በመበተን በመዝናናት በመልበስ መደሰት ምን ይሰራልሻል ??? አልኳት
ናርዶስም :- >>>>>>>እኔ በልጅነቴ በአጎቴ እና በአባቴ ጓደኛ የደረሰብኝ በደል አሁን ድረስ ከአእምሮየ አልጠፋም .,ቀን ቀን ስንገናኝ ደስተኛ እመስልሻለሁ ሰዉ ጋር ተጨዋች እመስላለሁ ግን ማታ መኝታየ ላይ ተኝቼ የተኛ ሰዉ ብመስልም ንፁህ እንቅልፍ ከወሰደኝ ብዙ አመታት አለፈኝ... ሁሌ ለሊት ለሊት ሳለቅስ ነዉ የማድረዉ ምንም መረጋጋት አልቻልኩም፡፡ እቤቴ ምንም አልጎደለብኝም ቤታችንም ዉስጥ የምንኖረዉ በደስታ ነዉ ምንም የማስብበት የምጨነቅበት ነገር የለኝም፡፡ ግን ይሄ የልጅነቴ በደል ምንም ሊረሳኝ ሊለቀኝ ከአእምሮየ ልሰርዘዉ አልቻልኩም፡፡
ማታ ስተኛ እያለቀስኩ እየኖርኩኝ በቀኑ ደስተኛ ልምሰል ብየ ነዉ ...ትምህርት ለማጥናት ሞከርኩኝ ግን አእምሮየ ምንም ሊቀበልልኝ አልቻለም ...መፅሀፉን ስገልጠዉ ካላነበብኩት እምባየ የምማርበት መፅሀፍ ላይ ቢያርፍ ምን ጥቅም አለዉ ??ብላ ጥያቄየን በጥያቄ መለሰችልኝ ...,
በናርዶስ አነጋገር በጣም ተሰማኝ ምን ማረግ እችላለሁ ...እኔም የእሷ አይነት አደጋ በልጅነቴ ደርሶብኛል፡፡ አብሽሪ አላህ አለን ከማለት ዉጭ
የማይደርስ የለም ሚኒስትሪ ፈተና ደረሰ ተፈተንኩኝ ...........ከተፈተንኩ ቡሀላ ናርዶስ ጋር በእናቴ ስልክ እንደዋወላለን በሳምንት አልፎ አልፎ አንገናኛለን ......
የሚኒስትሪ ዉጤት ሲመጣ አባቴ ዉጤቴን ለማየት ቸኩሎ መጀመሪያ እኔ ነኝ ማየት ያለብኝ ብሎኝ ወደ ትምህርት ቤት ካርዴን ሊያመጣ ሄደ
የሚኒስትሪ ዉጤቴ አባቴ ይዞት መጣ .....በሩን ሲከፍተዉ አባቴ ጋር ፊት ለፊት ተያየን ....ምን ይለኝ ይሆን??? ጥሩ ዉጤት ነዉ ወይስ አይደለም ??"እያልኩ በቆምኩበት ጨንቀት ያዘኝ.......
#ክፍል 7⃣
ይ........ቀ......
......ጥ.......ላ.......ል
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
`·. www.tgoop.com/Islam_and_Science
www.tgoop.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5793