tgoop.com/Islam_and_Science/5787
Last Update:
ከልጅነት ጀምሬ የምቀራረበዉ ኡስማን ትምህርት ቤት አንድ ስለሆነ ቁርአን ቤትም እንገናኛለን እሱም ቁርአን ላይ ጠንክሯል፡፡ ቁርአናችንን እየተዉን እቤታቸዉ እየሄድን ባንጫወትም ግን እኔ እና እሱ የልጅነት ፍቅር ተብየ በሁለታችን ልብ ዉስጥ አለ
ኡስማን ጋር ከአንደኛ ክፍል እስከ ሰባተኛ ክፍል ድረስ ስንማር አንድ ትምህርት ቤት ስለነበርን የፍቅር ይሁን የልጅነት ነገር ይሁን አላቅም ኡስማንን ሳየዉ ፍዝዝ የማለት ልቤ እንደመደንገጥ ሰዉነቴ አልታዘዝ አልታዘዝ እንደማለት ይሆናል ፡፡ ግን ፍቅር ማለት ምን ማለት ነዉ??
በነብዩ ጊዜ የነበሩ ሱሀቦች ፍቅርን እንዲህ ነበር የተረጎሙት
★★★በአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጊዜ በኡሁድ ዉጊያ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ተገድለዋል የሚል ዜና መዲናን እየናጣት ነበር ..የመዲና ሰማይ በዚህ አሳዛኝ ወሬ በሀዘን አጥልሏል..መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ኡሁድ አቅጣጫ እየተመመ ነዉ
ከአንሶሮች መካከል የሆነችዉ ሱመይራ(ረ.ዐ) ሁለት ልጆቿ አባቷ ባለቤቷና ወንድሟ ሰማዕት መሆናቸዉን ተረዳች ..ሱመይራ እነዚህ ሁሉ ወገኖቿ ቢሞቱባትም በዚህ ሁሉ የሀዘን ዉርጅብኝ አልተናወፀችም ..እልቁንስ እሷን ያስጨነቃት በእዉነት የታወቀዉ የጓጓችለት አንድ ዜና አለ ይህም የነብዩ ሰ.ዐ.ወ በሒወት መኖር ነዉ
..በእርሳቸዉ ላይ የደረሰ አንዳች ክፉ ነገር አለ??በማለት ጠየቀች
...የነብዩ ባልደረባዎችም ለአላህ ምስጋና ይገባዉ እርሳቸዉ በሒወት ይገኛሉ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ አሏት
ሱመይራ እንዲህ አለች ፡-እሳቸዉን እስከማይ ድረስ እረፍት አላገኝም የአላህ መልዕክተኛን (ሰ.ዐ.ወ)አሳዩኝ አለች
እሳቸዉን እንዳሳዩዋትም በቀጥታ ወደ እርሳቸዉ በመሄድ የካባቸዉን ጫፍ ከያዘቼ ቡሀላ እንዲህ አለች
"""""እናቴና አባቴ መስዋት ይሁንለልዎ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!እርስዎ በሂወት እስካሉ ድረስ ሌላዉ ሁሉ ቀላል ነዉ ..ያ በነብዩ ዙሪያ የነበሩ የተባረከ ትዉልድ ለእርሳቸዉ ይህን የመሰለ ድካ የሌለዉ ፍቅር ይለግሳቸዉ ነበር ...እኛስ?? ፍቅርን በሰዉ አይደል የምናመሳስለዉ ???
እኔ ስድስተኛ ክፍል በምማርበት ጊዜ ኡስማን ጋር ብዙ ጊዜ ቁርአን ቤት እና ትምህርት ቤት እንገናኛለን ቁርአን እቀራለሁ እንጂ ሶላት አልሰግድም ለዚህም ምክንያት ቤተሰቦቼ ስገጅ ብለዉ ስለማያበረታቱኝ ነዉ ... ትምህርት ቤት ስሄድ ሱሪ እለብሳለሁ ..
ሱሪ በምለብስ ጊዜ ኡስማንም ቁርአን ቤት ስትመጪ ሒጃብ ትለብሻለሽ ትምህርት ቤት ደግሞ ሱሪ ትለብሻለሽ አንዴ ቃልቻ አንዴ ዱሪየ እስታይል አትከይ ከአሁን ቡሀላ ትምህርትም ስትመጪ ሱሪ ለብሰሽ እንዳትመጪ ብሎ ይቆጣኛል፡፡
....እኔም እሺ ከአሁን ቡሀላ አለብስም አልኩት
እኔ ከኡስማን ጋር ጊዜ ማሳለፍ እሱም እኔ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ደስ ይለዋል፡፡ ኡስማን ጋር ከትምህርት ቤት ስንመለስም ስንሄድም ተቃቅፈን ነዉ....የክላስ ልጆች ነዋል እና ኡስማን እኮ ይዋደዳሉ ተቃቅፈዉ ነዉ የሚሄዱት እያሉ ሁሌ ያወራሉ ፡፡ አዎ እዉነታቸዉን ነዉ የኡስማን ሰፈር ቆሎ በር አካባቢ ነዉ፡፡ አንዳንዴ እኔን አጂፕ ድረስ ይሸኘኛል
አሁን ድረስ የሚገርመኝ ሁሌ እቤቴ ስሄድ ሶላት ባልስግድም __ግን በዱአ አላህን በመለመን አምን ነበር፡፡ መስገጃ ቦታ ላይ ሱጁድ ወርጄ ስቅስቅ ብየ እያለቀስኩ ያረቢ ኡስማንን የኔ አድርግልኝ ኡስማን የኔ የወደፊት ባሌ አድርግልኝ አንዴ የፍቅር ጥያቄ ይጠይቀኝ እምቢ አልልም እንዲጠይቀኝ አርግልኝ እያልኩ አላህን እለምናለሁ ፡፡
ግን ቢጠይቀኝ ገና ልጅ ነኝ ምን እለዋለሁ??? እንዴ ሁለታችንም ልጆች ነን ትዳር የማይታሰብ ነዉ እንዴት ይሄንን ሀሳብ ልመኝ ቻልኩኝ??? ደግሞ ለኡስማን የተለየ አመለካከት ቢኖረኝም ወንድ ልጅ እንደ ቶፊቅ ጨካኝ ቢሆንስ እያልኩ ብቻየን የሀሳብ ማዕበል ወስዶ ይመልሰኛል ..ነገር ግን ኡስማንን መራቅ የማልችልበትም ደረጃ ላይ ነኝ፡፡
ትምህርት ቤቶች ላይ ጥንቃቄ ግድ ነዉ ትዉልዱ ገና ከአራተኛ ክፍል ጀምሮ ሌላ መስመር ይጀምራል...ቤተሰብ ልጄ ገና ህፃናት የሚለዉን የድሮ ተረት ትተዉ ልጅን እንደልጅ ሳይሆን እንደ እህትነት አርገዉ ቢቀርቡ የተሻለ ነዉ..አንድ ሰዉ ሁሌ የሚናገራት ንግግር ትዝ ይለኛል የሴት እና የአር ትንሽ የለዉም ይላል እዉነቱን ነዉ ሴት ልጅ ገና ልጅ ናት ቢባል በወንድ ልጅ አፍ መሸወዳ አይቀርም..አርም ትንሽ ብትሆን መሽተቱ አፍንጫ መረብሹ ስለማይቀር ወላጅ የትምህርት ቤት አዋዋልን ልብ ሊል ይገባል ባይ ነኝ፡፡
ኡስሚ አንዳንዴ እየቀለደ ነዋል አፈቅርሻለሁ እኮ ምናምን ሲለኝ እዉነት እየመሰለኝ ልቤ ድንግጥ ይላል ወይ የልጅነት ፍቅር ...
#ክፍል 5⃣
ይ.......ቀ.......ጥ
......ላ........................ል
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
`·. www.tgoop.com/Islam_and_Science
www.tgoop.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5787