tgoop.com/Islam_and_Science/5779
Last Update:
ከአንደኛ ክፍል ጀምሬ አንዲት ጓደኛ ያዝኩኝ ልጅቱም ፌሩዛ ትባላለች ...ፌሩዛ በትምህርቷ ጎበዝ ነች እኔም እንደ እሷ ጎበዝ መሆን የኔም የአባቴም ምኞት ነዉ ጓደኛየ ማድረግ ወሰንኩ ፡፡ ክፍላችን ዉስጥ ተሰሚነት ነበረኝ እኔ ከክላስ ልጅ አንድ ልጅ ጋር ከተጣላሁ የተጣላሇትን እሷን እንዳታወሩ ካልኩኝ የሚያወራት የለም ፡፡ እኔ የወደድኩትን ይወዳሉ የጠሉትን ይጠላሉ....እኔ የምጫወትዉን ይጫወታሉ እኔ የማይመቸኝን ጨዋታ አይጫወቱም ፡፡
ቁርአን ደግሞ መቅራት የጀመርኩት KG ተማሪ በነበርኩበት ሰአት ሲሆን ቁርአን የገባሁትም ጅማ ኑር (አጅፕ)መስጊድ ያለዉ ቁርአን ቤት ነዉ ..ገና አፌ መናገር ሲጀምር አባቴ ቁርአን እንድቀራ በቁርአን ጎበዝ እንድሆን ይመክረኝ ያበረታታኛል..ግን ምን ዋጋ አለዉ በአንድ ሰዉ ጥረት አይሆን..ቁርአን እንድቀራ እናቴ ትኩረት ስላልሰጠችኝ መድረሳ ቁርአን ለመቅራት እመላለሳለሁ እንጂ አሊፍ ባታ ሳ ጂም ብሎ ሁሉንም ፊደል ለመለየት ሶስት አመታት ፈጅቶብኛል፡፡
ቀን ማታ መሽቶ ነግቶ ሁሌ ሀሳብ የሆነብኝ ነገር የሰፈር ልጆች ልጫወት እነሱ ጋር ስሔድ አንቺ ጋር አንጨዋትም እያሉ እኔን ለብቻየ የሚያገሉኝ ነገር ሚስጥሩን ምክንያቱን ላዉቀዉ አልቻልኩም ..እንደ ልጅነቴ የሰፈር ልጆች ጋር የመጫወት እድል ላገኝ አልቻልኩም....እኔ ከእነሱ ጋር የማልጫወትበት ምክንያት ምንድን ነዉ ??? እያልኩ እራሴን ብጠይቅ መልስ ሊመጣልኝ አልቻለም..
አባቴንም ሁሌ ቀን በቀን እኔ ጋር አልጫወትም አሉኝ እያልኩ እነግረዋለሁ የአባቴ መልስ ግን ምንም ሊቀየር አልቻለም ...
....ተያቸዉ ልጆቹ ጋር አትጫወች የምትለዉ መልስ ብቻ ነዉ የሚመልስልኝ...ተለዋጭ መልስ ሊሰጠኝ አልቻለም
አንድ ቀን የሰፈር ልጆች ተሰብስበዉ ሲጫወቱ የሚጫወቱት ጨዋታ በጣም ደስ አለኝና ...እኔም በግድም ቢሆን ሂጄባቸዉ የሰፈር ልጆች ጋር ጨዋታ ጀመርን ....ልጅነት መቼም ጨዋታዉ ፈረሰ ዶቦዉ ተቆረሰ ከተባለ መጣላታችን አይቀርም አይደል...አንዲት የጎረቤታችን ልጅ ጋር ተጣላን ...ከዛም ከልጅቱ ጋር ሲያገላግሉን መሰዳደብ ጀመርን ....
........ተጣልተን ስንሰዳደብ እኔ የልጅነት አንቺ ማስጠሌ አይጥ እያልኩ ስሳደብ እሷ ግን የሰፈር ሰዉ በተሰበሰበት መሀል ከአእምሮ የማይዋጥ የሚዘገንን በልጅ አቅሜ መሸከም የማልችለዉ ስድብ ሰደበችኝ
....እኔም ይሄን ስድብ እንደሰደበችኝ ደነገጥኩ ... እሷ ጋር ስድብ መመላለስ አፍ መካፈቴን አቁሜ ስድቡን እያብሰለሰልኩ እየተገረምኩ እንዴት እንዲህ ብላ ትሰድበኛለች???እያልኩ ወደ ቤቴ ሄድኩኝ..
እቤት ስገባ የአላህ ነገር አባቴ ቁጭ ብሎ አገኘሁት...
ፊቴ መቀያየሬ መናደዴን ያየዉ አባቴ ምን ሁነሽ ነዉ ልጄ ፊትሽ ተቀያይሯል ሰዉ ጋር ተጣልተሻል እንዴ???? አለኝ
......እኔም አባቴ የጎረቤታችን ልጅ""" ........."""ብላ ሰደበችኝ እኮ አልኩት ..
.......ወዳዉ አባቴ ፊቱ ተቀያየረ ተናደደ እና ቁጭ ካለበት በመነሳት መኝታ ክፍል ገብቶ ሽጉጡን ከአስቀመጠበት አንስቶ ወዳዉ አቀባብሎ ከመኖሪያ ቤት ወጥቶ የሰደበችኝን ህፃኒቱን የኔኑ እኩያ በሽጉጥ ሊገላት ይፈልጋት ጀመር፡፡
አባቴ በጣም ተናዷል ጅማቱ ዉጥርጥር ብሏል....ልጅቱ መኖሪያ ቤት ሂዶ ነይ ዉጪ የት ነሽ ዛሬ እገልሻለሁ እያለ እየፈለጋት ነዉ...
ሰፈሩ በአንድ እግሩ ቆመ ..የኛ ጎረቤቶች በኛ ቤት አቅራቢያ የሚገኙ ዘመድ አዝማዶች ተሰብስበዉ ንዴት አብርድ እያሉ እየለመኑት ነዉ ...
አባቴን ተረጋጋ እባክህ ተብሎ በጓደኞቹ በዘመድ አዝማዶች በስንት ጉድ ተለምኖ ተመልሶ እቤቱ ገባ፡፡ ግን አባቴ ልጅቱን አለቃትም ሌላም ቀን ቢሆን በዚህ ሽጉጥ አናቷን ብየ ነዉ የምገላት እያለ ይደነፋል............
ማታ ተኝቼ ብቻየን ማሰብ ማሰላሰል ጀመርኩኝ አብረን የምንጫወት የሰፈራችን ልጅ እንዴት ልሰድበኝ ቻለች ???ይሄን ለጆሮ ለመስማት የሚዘገንን ስድብ እንዴት ሰደበችኝ ???አባቴስ ስነግረዉ ለምን እገላታለሁ ብሎ ደነፋ ???? እያልኩ ብቻየን ሳስብ አደርኩኝ....ግን ይሄን ስድብ እዉነት ነዉ ወይስ ዉሸት?? ማጣራት አለብኝ ብየ ወሰንኩ ...ግን ማንን ልጠይቅ ???
የምጠይቀዉ ሳጣ ሲጨንቀኝ አንድ ሀሳብ መጣልኝ ለምን የቤት ሰራተኛችንን አልጠይቃትም???ብየ አሰብኩኝ...እሷን ለመጠየቅ ወሰንኩ
የቤት ሰራተኛችንን ልጅቱ ለምን"""""""____"""""እንደዚህ ብላ እንደሰደበችኝ ጠየኳት ...ሰራተኛችን ለመንገር ፍቃደኛ አልሆነችም ... ግን እኔ ንገሪኝ እያልኩ አፋጥጬ ስይዛት የቤትሰራተኛችን እያለቀሰች ....,እንደዚህ አለችኝ.........
ልጅቱ የሰደበቻት ምን ብላ ነዉ ???? የተደበቀዉ ...ማንነት ምንድን ነዉ ???ለምን አባትየዉ ገና ነፍስ ያላወቀችን ልጅ አገላለሁ ብሎ ለምን ተነሳ ??? የተቆለፈዉ ሚስጥር ምንድን ነዉ ???
በሚቀጥለዉ ክፍል እናያለን
#ክፍል 2⃣
ይ....ቀ...ጥ.....ላ....ል
www.tgoop.com/Islam_and_Science
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5779