tgoop.com/Islam_and_Science/5773
Last Update:
📖 #የመራም_ማስታወሻ
ክፍል ~➊➑ የመጨረሻዉ ክፍል
✍ ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ
አንድ ቀን አብዲ የ12 ክፍል ያመጣሁትን ዉጤት ካርድ ይመለከተዋል
..... እህት ወንድሞችሽን ለማስተማር ብለሽ ያቋረጥሽዉን ትምህርት በዲግሪ መማር አለብሽ ብሎ በግል ኮሌጅ በኔዉ ምርጫ Acounting ተመዝግቤ እየተማርኩ ነዉ.....በቅርቡ ደግሞ የልጅ እናት መሆኔ ነዉ ነፈሰ ጡር ነኝ ..
የታገሰ መጨረሻዉ እንዴት አማረ!!! በህይወት ዘመናት የሚፈራረቁ ደስታና ሀዘን የህይወት ሁለት ገፅታዎች ናቸዉ ...ሁሌም ቢሆን ሀዘን በደስታ ሲተካ ደስታም በሀዘን ይቀየራል ሂወት እንደዚህ ነች ፡፡
አላህ ከታጋሽ እና ከአመስጋኝ ብራያዎቹ ያድርገን.....
ስኬት አጋጣሚ አይደለም ..ስኬት የአመለካከት ዉጤት ነዉ ..አመለካከት ደግሞ ምርጫ ነዉ፡፡ ስለዚህ ስኬት የምርጫ ጉዳይ እንጂ የዕድል ጉዳይ አይደለም...ስኬት በህወይወት ዉስጥ በደረስንበት ከፍታ ያህል አይለካም፡፡ ይልቅስ ስንወድቅ ምን ያህል ጊዜ ወድቀን ተነስተናል??በሚለዉ መልስ ያዘለ ጥያቄ ነዉ ስኬት የሚለካዉ ...ወድቆ የመነሳት ችሎታ ነዉ የኛን ስኬት የሚወስነዉ....
አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፡-"" እንዲሳካልህ የምፈልግ ከሆነ የዉድቀትህን ቁጥር እጥፍ አድርገዉ ..ሽንፈት የስኬት ረጅም ጎዳና ነዉ ብለዋል፡፡""
የስኬት ብቸኛዉ መለኪያ የሆነ ነገር መስራት ብቻ ከሆነ ..መዉደቅ የሚገፋን ወደ ፊት ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
ስኬትን ለማግኘት ብለዉ ብዙ ሴቶች ስኬት እየመሰላቸዉ ብዙ መጥፎ ሀራም ነገር ይሰራሉ ..በጭራሽ ይሄ የስኬት መንገድ ሊሆን አይችልም፡፡ ሴትነት በርካሽ መንገድ የሚረከስበት በሀራም መንገድ የሚሸቀልበት በአላማ በለለዉ ወንድ አላማዋን የምትስትበት አይደለም!!" ሴትነት ማለት በእሾህ የተከበበ እስር ቤት ነዉ..ማምለጥ የማይቻል ለመኖር ደግሞ አንዱ እሾህ ሲወጋ እየነቀሉ እያስታመሙ የሚኖርበት የስቃይ የፈተና ፆታ ነዉ ..ይሄን እስር ቤት በጣጥሰሸ ለመዉጣት መታገስ መሶበር በማስተዋል መራመድ እንጂ ያገኘሽዉ ጋር እነፍሳለሁ ካልሽ ...ያዉ ገለባ ንፋሽ ሁነሽ ትቀሪያለሽ ፡፡
እንደ እኔ ከችግር ጋር ከመከራ ጋር ማደግ ችግር እንዳይፈታ ያደረገ ስብዕና አልብሶ ያጠነክራል፡፡
አንድ ሰዉ በሆነ ነገር ከአንተ የተሻለ ከሆነ ምክንያቱ ሊሆን የሚችለዉ ከአንተ የበለጠ ብዙ ጊዜ የወደቀ እና ተስፋ ሳይቆርጥ ለሽንፈት ቦታ ሳይሰጥ ግቡ ላይ ደርሷል ማለት ነዉ፡፡ አንድ ሰዉ ከአንተ የባሰ ከሆነ ደግሞ ምክንያቱ አንተ ባለፍክበት የሚያሰቃይ የመማር ልምምድ ዉስጥ አላለፈም ማለት ነዉ፡፡
የዱንያ ኑሮ ሲኖር መኖራችን ካልቀረ ችግር የህይወት ጅራቱን ይዞ ወደሆላ ገትቶ የድህነት ጉረኖ ሊደፍቀን አይገባም እኛም ልንፈቅድለት መፍቀድ የለብንም ፡፡
እኔ ሳድግ በቤተሰብ ግጭት አእምሮ ተጨናንቆ ነበር
ከዛም እናቴ ስትሞት ያወረሰችኝ ጥንካሬን ተስፋ አለመቁረጥ ቅንነት እና የወንድም እህቴን ሀላፊነት ብቻ ነበር ከእናቴ መዉረስ የቻልኩት...ነገር ግን ተስፋ የቆረጠ ያገጠጠ የታረዘ የደከመ እኔነቴና ሰዉነቴ በጭራሽ እንዲታይ አላደረኩም እንደዉም የእህትና የወንድሞቼን አደራ ስለተቀበልኩ ብርታቱን ሰጠኝ
የጥንካሬ መለኪያ ሚዛን መሆን ያለበት ፊት ለፊት የገጠመን የህይወት ጥያቄ በአሸናፊነት መወጣት እንጂ ምክንያት በመደርደር በመሸሽና ተስፋ በመቁረጥ ለዚች ለማትረባ ዱንያ እጅ አልሰጥም ብየ በአላህ እገዛ ብዙዉን ያሳካሁ ይመስለኛል
ትናንት የነበረዉ ዛሬ የለም ..ዛሬ ያለዉ ችግሬ ጠንካራ ከሆንኩ ነገ የለም..ለመጣዉ ችግር ሁሉ በአላህ ተስፋ አርጎ አላህን ይዤ አልቸገርም አላህን ከያዝኩ ብቻ መሸሻ መንገድ እንዳለዉ ሁሌም እርግጠኛ ነኝ፡፡
ዉድ የተከበርሽዉ እህቴ ግን ክብርሽን ደረጃሽን እወቂዉ ሴትነት መልክሽን የሰዉነት ቅርፅሽን ችግር ያላየ የሚያምር እጅና እግርሽን ጠዋት ማታ በማጠብ በመዋዋብ ከቤት ስትወጪ የወንድ የሙገሳ ምላስ እና የመንገድ ላይ ፉጨት ፊሽካ ተጠባባቂ አትሁኝ ..ወይም በመኪና መንገድ በገበያ በሚዲያ ዉበትሽን የኔ ነዉ ብለሽ ስትበትኝም ዋዉ አምሮብሻል ስትባይ አመሰግናለሁ ..አይደል አልቀረብህም እያልሽ የወንድ የጫፍ ምላስ ኮመንት አንባቢ የአንቺ ዉበት መገለጫ ሲሆን ሊያሽሞነሙነሽ ልብሽ ጩቤ እንዲረግጥ መቼም አትፍቀጅለት ፡፡የሴት ልጅ ዉበት አላማዉን በረሳ ስራ በሌለዉ ወንድ የሚገለፅ አይደለምና...የአንቺን ዉበት የምወስኚዉ እራስሽ ነሽ አላማሽ የወንድ አድናቆት ከሆነ ኢነማል አእማሉ በኒያ ገና ከቤት ስትወጭ ጀምሮ ፊሽካ ይጀምርሻል በግ ሙቶ ተኩላ ቢያለቅስ ወይም አህያ ሙቶ ጅብ ለቅሶ ቢደርስ ጥቅም የለዉም ሲያደንቅ ፊሽካዉ ሁሉ አንድ ቀን መዘዝ ይዞብሽ ይመጣል፡፡ አባቶቻችን እንዲህ ይላሉ """አህያ ቢሰባ ምኑ ረባ ይቆያል እንጂ አህያ የጅብ ናት""" ተብሏል፡፡ እዉነት ነዉ...አህያ ቢሰባ ቢወፍር ቢያምር የኛ ማህበረሰብ መቼም ቢሆን ለምግብነት አይጠቀመዉም ..ጊዜ ይፈጃል ይቆያል አህያ ከልጅነት ጀምሮ እስከ እለተ ሞቱ ሲያገለግል ሲሸከም ሲገረፍ ይኖራል ከዛም ሲያረጅ ወይ ሲሞት አህያዋን የሚበላዉ ጅብ ነዉ ..እንደዉም አህያ ሲያረጅ ወደ ጫካ ማታ ተወስዶ ይጣላል ለምን ጅቦች እንዲበሉት፡፡ እናም እህቴ አንቺ የተከበርሽ ፍጡር ነሽ ግን በዉበትሽ የምትተማመኝ ከሆነ እንደዚህ እንደ አህያ ማንም የሚወጣብሽ ማንም አምሮብሻል እያለ ቸብ የሚረግሽ ማንም እየመጣ የስሜት ማብረጃ እንዳያደርግሽ ነገ ጂብ የሚበላዉ የአህያ ህይወት ለመኖር አትወስኝ...አህያስ የተፈጠረዉ ለዚሁ አላማ ነዉ ግድ የለም ተሸከመም ተመታም አርጅቶም ጅብ በላዉ እንስሳ ነዉ ነገ የዉመል ቂያማ አፈር ይሆናል ግን አንቺ ነገ የዉመል ቂያማ ተቀስቅሰሽ ለምትጠየቂዉ ጥያቄ ምን ብለሽ እንደምትመልሽ አስበሽ ታቂያለሽ???
በዉበትሽ ተጠቅመሽ ጥሩ አማች ለቤተሰብ ለማምጣት ብር ያለዉ ባል ላይ ለመዉደቅ ብለሽ የምሰሪዉ የመዋዋብ ስራ የሚገጥምሽ ከዉበት መራጭ ሴት አሳዳጅ የሆነ ወንድ ጋር እንደሆነ አዘንጊ..ዉበት አንቺ እንዳሰብሽለት ነዉ በዉበትሽ አድናቂሽ ከበዛ ከአንቺ ችግር አለ ማለት ነዉ ነገ
ይሄ የሚጨራመት የሚያሸበሽብ ዉበት የአንቺ እድሜ ሲገፋ በዉበት ብሎ የገባዉ አባወራ ሌላ ቆንጆ ሴት መፈለጉ አይቀርምና፡፡ ይልቅ ዉበት ይረግፋል የማያምር እጅሽን ፃፊበት ተማሪበት ስሪበት በዉበት ማሰብ አቁመሽ በጭንቅላትሽ አስበሽ ለሌሎች መድረስ ቻይ...የሚያምር እግርሽን ተራመጅበት ሂጅበት ባይሆን ሀራም ቦታ ሳይሆን ቂርአት ለመቅራት ዲነል ኢስላምን ለመማር ተራመጂበት የዛን ጊዜ የሚመጣልሽ የወደፊት አጋርሽ ዉበት ተመልካች ሳይሆን የአንቺን ዲን ስብዕና ጥሩ አመለካከት አይቶ ጎጆ ይቀልሳል የዘላለም ደስታ ነዋሪ ትሆኛለሽ..ካልሆነስ በዉበትሽ ያገባሽ ወንድ 90% የሚያስበዉ አለ ቆንጆ ያገባና በሬ ያረደ ብቻዉን አይበላም የሚለዉን አባባል መቼም ከአእምሮዉ ስለማይፍቀዉ ዉበት ብቻ አይቶ ካገባሽ ቤት ሁነሽ አያምንሽ ..ቤተሰቦችሽ ጋር ብትሄጅ አያምንሽ ..እሱ ሌላ ቦታ ቢሄድ አያምንሽም ለምን ሲያገባሽ ያገኘብሽ ፊትሽን እጅሽን እግርሽን አለስልሰሽ ቀብተሽ እንጂ ልብሽን በኢማን አጠንክረሽ አይደለምና ከዛስ ከዛማ
ካልተማመኑ ፍች ነዋ..የዉበት ወጥመዱ ቆንጆ ያገባና በሬ ያረደ ብቻዉን አይበላም በሚለዉ ፍች ይሆናል👇👇
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5773