tgoop.com/Islam_and_Science/5763
Last Update:
...... "እ አቤት" አልኩት በደከመ ድምፅ
........"ምን እያሰብሽ ነው? ርቀሽ ተጓዝሽ እኮ" አለኝ
...... "አረ ምንም አላሰብኩም እንዲሁ ተመስጨ ነው" አልኩት፡፡
...,, "እእ እኔ ደግሞ ስለኔ እያሰብሽ መስሎኝ" ሲለኝ የውስጤን በማወቁ ደነገጥኩ ..
....እንዴ ስለአንተ ምን አስባለሁ ??ከጎኔ ሆነህ ደግሞ!" ብየ የውሸት ፈገግ አልኩኝ፡፡ አሁንም ዳግም በመሀላችን ዝምታ ሰፈነ፡፡ በራሴ ምላሽ ተናደድኩ!!! ምናለ ስላንተ እያሰብኩ ነው ብለው ኑሮ??? እያልኩኝ በውስጤ " ወደ ቤት እንሂድ!?" አልኩት ስፈራ ስቸር " .......አንቺ ታሪክሽን ነገርሽኝ አንችስ እኔን ማወቅ አትፈልጊም???"አለኝ፡፡ ከራሱ በመምጣቱ ደስ እያለኝ "እፈልጋለሁ ግን እንዳረብሽህ ፈርቸ ነው ዝም ያልኩት" ብየ በደስታ ታሪኩን ለመስማት ጓጓሁ፡፡
አብደልከሪም ገና ንግግር ከመጀመሩ በፊት እንባ ተሽቀዳደመው፡፡ ሚስኪን የወንድ ልጅ እንባ ማየት ምንኛ ከባድ ነው!? እንባውን ሳይ ሆዴ በሀዘን ተላወሰ የምናገረው ጠፋኝ፡፡
" መሪ እኔ ማለት እናቴንም ሆነ አባቴን የማላውቅ እህት ወንድም የሌለኝ ብቸኛ የማደጎ ልጅ ነኝ! ተወልጄ ያደኩት ሳኡዲ ነው እናቴ እና አባቴ በስደት ከሀገር በወጡበት ሰአት ነው እህል ውሀ ያገናኛቸው፡፡ እናቴ እና አባቴ በተጋቡ ሰአት እናቴ ትስራባቸው የነበሩ ሰወች ማለትም የኔ አሳዳጊ ነበር መኖሪያ የሰጣቸው፡፡ ተጋብተው ብዙም ሳይቆዩ እኔ ተፀነስኩ ግን ምን ዋጋ አለው የአላህ ቀድር ሆነና አባቴ በመኪና አደጋ ሞተ፡፡ ይሄ ለእናቴ ከባድ የዱብእዳ ዜና ሆነባት ግን የአላህን ውሳኔ መሻር አይቻልም፡፡ እማ በሀዘን ብትቆራመትም እኔ ከተወለድኩ በኃላ ግን ደስተኛ ነበረች ሀዘኗን በእኔ ረሳች፡፡ እማ በኔ ደስተኛ ብትሆንም እኔ ገና በቅጡ እንኳን ራሴን ሳላውቅ ገና የ5 አመት ህፃን እያለሁ እማን ሞት ነጠቀኝ፡፡
እማ በሰው ሀገር ዘመድ ወዳጅ በሌለበት እኔን ጥላ ሞት ወደሷ መቅረቡን ስታውቅ ለአሰሪወቿ ነበር እኔን አደራ ብላ የሞተችው! ገና በልጅነቴ ክፉና ደጉን ለይቼ በማላውቅበት ሰአት እናቴን በሞት ሳጣ እጅጉን አዝኘ ነበር፡፡ አሳዳጊወቸ ሁለቱንም ወላጆቹን በሞት ያጣ የቲም ነው በማለት ለአላህ ብለው ነይተው ምንም ሳያጓድሉብኝ ከልጆቻቸው እኩል አድርገው አሳደጉኝ፡፡
እድሜየ እየጨመረ ሲመጣ ያኔ በልጅነቴ እናቴ ኢትዩጲያ ስንሄድ ቤተሰቦቼ ጋር ሀይቅ ነው የምንሄደው ትለኝ ነበር፡፡ "ሀይቅ ምንድነው" ብየ ስጠይቃት " የተወለድኩበት ሀገር ነው እዛ ትልቅ ሀይቅ ስላለ ሀገሩም በሀይቁ ስም ተጠራ እዛ ስንሄድ ከባህር እንደወጡ አሳ ትበላለህ በጀልባ ትሄዳለህ" ትለኝ የነበረው በህፃን አእምሮየ ውስጥ ታትሞ ቀርቷል፡፡
እናም እድሜየ እየጨመረ ሲመጣ አሳዳጊዎቼ ምርጫ ሁለት ሰጡኝ አንድ እዛው ሳኡዲ ውስጥ እንድኖር ሁለት ወደ ኢትዩጲያ መጥቸ መኖር እንደምችል እና መቋቋሚያ ገንዘብ እንደሚሰጡኝ ነገሩኝ፡፡ ኢትዩጲያን ከስሟ ውጭ ባላውቃትም የወላጆቼ ሀገር በመሆና እኔም ደግሞ ኢትዩጲያዊ እንጅ የአረብ ደም እንደለለኝ ስላወኩ ከአፈር ይልቅ ደሜን መረጥኩ እናም ወደ ኢትዮጲያ መጣሁ፡፡
..... አዲስ አበባ ላይ ቤት ንብረት አፈራሁ፡፡ ግን ሂወቴ ባዶ ነበር አንድም የኔ የምለው የምኖርለት ሰው የለም እማየ ስትናፍቀኝ የትውልድ ሀገሯ ወደ ሆነችው ሀይቅ በመጓዝ እናቴን በምናቤ እየሳልኩ ከሷ ጋር በሀሳብ ከጎኔ እንዳለች አድርጌ እዝናናለሁ፡፡ ሀይቅን እያካለልኩ ይሄ ልጅ የፋጡማ ልጅ ነው እሷን ይመስላል ብሎ አቅፎ የሚስመኝን ዘመድ በአይኔ እያማተርኩ እውላለሁ፡፡ ግን ይሄ ልጅ ዘመዴን መሰለኝ የሚለኝ ሰው እስካሁን አላገኘሁም! እኔ የቱንም ያህል ሰው ብራብ ግን መጥገብ አልቻልኩም ዘመድ ርቦኛል የቤተሰብ ፍቅር ርሀብተኛ ነኝ! ኢትዩጲያ ከመጣሁ ድፍን 4 አመት ሆነኝ ግን ርሀቤን የሚያስታግስልኝ አንድ እንኳን ዘመድ አላገኘሁም" ብሎ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡
ገና ሲተርክልኝ ጀምሮ የሚፈሰው እንባየ የሱ መንሰቅሰቅ ደግሞ እንደ አዲስ እንባየን አብዝቶ አወረደ፡፡ በእንባ ከመታጠብ ውጭ ቃል ከአፌ ማውጣት አቃተኝ፡፡ ንግግሩን ቀጠለ እናም ልክ እንደ ሁልጊዜው የእማን ናፍቆት ለማስታመም ሀይቅ ውየ ከሰአት ተመልሽ ከሚሴ ከተማ የሚገኝ አንድ በአላህ መንገድ ላይ ያገኘሁት የአኼራ ወንድም አለኝ እሱን ዘይሬ ንጋት ላይ ወደ አዲስ አበባ እመለሳለሁ ብየ አስቤ ነበር፡፡ የአላህ ቀድር ሁኖ ያኔ ሪምን መኪና ገጭቷት ሳይ አሳዘነችኝ እና ወደ ክሊኒክ ወሰድኳት ያኔ ገና ስትመጭ ከመኪና ስትወርጅ እንዴት ከመውደቅ ለትንሽ እንደተረፍሽ አየሁሽ ከአይንሽ የሚፈሰው እምባ ወደር አልነበረውም ለዛ ነበር እህቷ ነሽ ብየ የጠየኩሽ
በአንድ ጊዜ ተቀያይረሽ ስታንቂኝ ከምነግርሽ በላይ አሳዘንሽኝ በኃላ ደግሞ ወደ ቤት ስትሄዱ ባዶ እግርሽን መሆንሽን ሳይ በሪም በጣም ቀናሁ የኔን ሂወት ባዶነት የሚያስብልኝ ሰው አለመኖሩ ትዝ ሲለኝ ጩህ ጩህ ነበር ያለኝ፡፡ እናም እኔ የምናፍቀውን ፍቅር እናንተ ላይ ሳየው ዝም ብየ ልለያችሁ አልፈለኩም ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅሜ ልቀርባችሁ ፈለኩ፡፡ ሙከራየም ተሳካልኝ የበለጠ ደግሞ ቀርቤ ሳያችሁ የኔ የገንዘብ እና ሀብት ክምችት ትርጉም አልባ ሆነብኝ እኔ ውጭ ላይ ውድ የሚባል ነገር ላይ ከማወጣው ወጭ ይልቅ እናንተ ቤት መጥቸ የማገኘው ትልቅ ፍቅር ይበልጥብኛል፡፡
እማማየ እንደ እናቴ ሪም እንደ እህቴ አዩብ ደግሞ በቃ ልክ እንደ ልጄ" ሲል ሳቄን ለቀኩት "ምነው ምን ያስቅሻል ልጄ ስላልኩ ነው? ልጅኮ በጣም ስለምወድ ነው!!" አለኝ " እሺ ይሁንልህ ባለ ልጅ የአዩብ አባት" ብየ አሁንም ሳኩበት፡፡ እሱም እየሳቀ አንች ደግሞ አቀልጅ እንጂ መቼም መዉለዴ አይቀር አለኝ
....እንደዚህ እየተጨዋወትን በለንበት ሰአት ...እኔ በሱ ሂወት ውስጥ የሚኖረኝን ቦታ ሳይነግረኝ የስልክ ጥሪ አስተጋባ፡፡ ስልኩን አንስቶ ንግግር ጀመረ፡፡ ሳይነግረኝ ስላቋረጠው ስልክ ተናደድኩ ግን ንዴቴን በፈገግታ ደበኩት፡፡ ንግግሩን እንደጨረሰ " ወደ ቤት አንሄድም?" አልኩት "አሁን መሄድ እንችላለን" አለኝ ከተቀመጠበት እየተነሳ ጉዞ ወደ ቤት ጀመርን " መሪ ሶስት ቀን ያህል ለመቆየት አዲስ አበባ መሄዴ አይቀርም እዛ ትንሽ እኔን የሚፈልግ ስራ አለ እሱን አስተካክየ በቻልኩት ፍጥነት እመለሳለሁ!" ሲለኝ በጣም ደነገጥኩ
ክፍል ➊➎
ይቀጥላል ......
join👇
@Islam_and_Science
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5763