tgoop.com/Islam_and_Science/5760
Last Update:
📖 #የመራም_ማስታወሻ
ክፍል ~ ➊➌
✍ ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ
አንድ ቀን በስራ ሰአቴ እኔ ወደ ማስተናግድበት ካፌ ሁለት ሰወች ሲገቡ ተመለከትኩ ያየሁት ነገር አስደነገጠኝ ለተወሰኑ ሰከንዶች ድርቅ ብየ ቀረሁ፡፡
አዩ እና ልጁ ሲገቡ ተመለከትኩ ልቤ ምቱ ፈጠነ ስሜቴ ሁሉ ተዘበራረቀ ሰውነቴ በፍርሀት ራደ "እንዴ ምን ሁኜ ነዉ ይሄን ያህል??? ማንም ይምጣ ማን ስራየ ማስተናገድ ነው" ብየ ራሴን አደፋፍሬ አረጋጋሁ፡፡ እናም ወደ ተቀመጡበት ወንበር አመራሁ እና አዩን ሳምኩት "መሊ እእ አቢከሊይም እጄን መሪዉ ጋር ይዞ መኪና አስነዳኝ" አለኝ በደስታ እየተፍለቀለቀ "ጎበዝ የኔ ማር" ብየ በድጋሜ ሳምኩት በዚህ አጋጣሚ የልጁ ስም አብደልከሪም መሆኑን አወኩ፡፡
.....ወደሱ ዙሬ "ምን ልታዘዝ?" አልኩት " አሰላሙአለይኪ መራም" አለኝ ደነገጥኩ "ወአለይኩምሰላም ምን ላምጣልህ?" አልኩ ስለደነግጥኩ ቶሎ ከሱ መራቅ ፈለኩ " ጠቆር ያለ ማኪያቶ" አለኝ የአዩን ፍላጎት ሳልጠይቅ ቶሎ ተፈተለኩ፡፡
ግራ ገባኝ "ለምን ራሴን አስደነብራለሁ? እሱ ማነው?" አልኩና ለራሴ ያዘዘኝን ማኪያቶ እና ለአዩ በኔ ምርጫ ማንጎ ጭማቂ ይዠ ተመለስኩ፡፡ ኮስተር ብየ አስቀምጨ ተመለስኩ፡፡ ድጋሜ ወደዚህ ካፌ እንዳይመጣ በልቤ ዱአ አረኩ፡፡
ከስራ ወደ ቤት እንደተመለስኩ ሪም እና እማማየ ቡና አፍልተው ነበር፡፡ አዩ እንቅልፍ ወስዶታል፡፡ እኔም ልብሴን ቀይሬ ወደ ቡናው ተቀላቀልኩ፡፡ የሁለቱም ወሬ ስለ አብደልከሪም ነበር፡፡ ሪም ስለሱ ጥሩነት ስታወራ "ግን ማነህ አብደልከሪም!?" አልኩኝ በውስጤ ስለ መልካምነቱ እያነሱ ደጋግመው ስሙን ሲጠሩ ስለሱ የማወቅ ጉጉት አደረብኝ ግን እኔ ጋር ተነጋግረን ስለማናውቅ እንዴት ብየ እንደምቀርበው አላውቅም፡፡ የማላውቀው አይነት ስሜት ሲሰማኝ "እኔ ደክሞኛል በቃ ልተኛ የነገ ሰው ይበለን ደህና እደሩ" ብያቸው ከአዩ ጎን ተኛሁ፡፡
ጎኔ ቢጋደምም እንቅልፍ ግን ከአይኔ ራቀ ያኔ በቁጣ ተንደርድሬ ያነኩት ቀን የነበረውን እርጋታ አስታወስኩ፡፡ ከዛ ቀን ጀምሮ የነበረውን ሁኔታ በሀሳብ የኃሊት ተጉዤ መረመርኩ፡፡ "አብደልከሪም ግን ለምን ወደ ሂወታችን መጣህ!?" እያልኩ በለለበት ጥያቄ መልስ ከየት ይምጣ፡፡ ሪም ከጎኔ መጥታ ስትተኛ የተኛሁ መስየ አይኔን ጨፈንኩ፡፡ " መሪ አለሽ አልተኛሽም አውቅብሻለሁ እያሰብሽ ነዋ!?" አለችኝ
...... " አይ እንዲሁ እንቅልፍ እንቢ ብሎኝ እንጂ ምን አስባለሁ ብለሽ ነው?" አልኳት፡፡ ሪም ሳልናገር ገና አይታ የማስበውን ታውቃለችና ፈገግ አለች "አብደልከሪም እያሳሰበሽ አይደለም?" አለች፡፡
.....ደነገጥኩ አፌ እየተንተባተበ "ለምን ምን ስለሆነ?" አልኳት ይሄን ጥያቄ ለራሴ ጠይቄ መልስ ያጣሁለት ቢሆንም ዳግም እሷን ጠየኳት፡፡
......."መሪ አብደልከሪም በጣም የሚያሳዝን የታሪክ ባለቤት ነው! አንችን አውቅሻለሁ እህቴ ነሽ ሰው አትጠይም ሰው ወዳድ ነሽ አሁን ግን አብደል ከሪምን ስትሸሽው አይሻለሁ ያማለት ደግሞ የሆነ ስሜት ለሱ አለሽ ማለት ነው ሽንፈትን በመሸሽ ልታመልጭ እየሞከርሽ ነው! መልካምነት ሁሌም አሸናፊ ነው ለመልካምነቱ ብትሸነፊ ክፋት የለውም እማማየ ደግሞ ስለ ሁሉም ነገር ታሪካችንን ነግረውታል" አለችኝ፡፡
....... ሪም የልቤን አውቃ ስትነግረኝ በእጄ እጇን ይዠ" እህቴ አንች ልክ ነሽ አዎ ለሱ የተለየ ስሜት ይሰማኛል ስራ ቦታ የሚመጡ ባለሀብቶት ያላቸውን ኩራትና ንቀት ብዙ አይቻለሁ ግን አብደልከሪም ከዛ ተቃራኒ ሆነ የመጀመሪያ ቀን ቤት እንዳይገባ በጣም ፈልጌ ነበር ግን እሱ ከመኩራራት ይልቅ እንደውም ደስተኛ ነበር ሪም ግን ምን አይነት ሰው ነዉ ብየ ሰለሱ ለማወቅ ሳስብ ስሜቴ ይዘበራረቃል ሳየው ደግሞ ሰውነቴ ይርዳል እና ዳግም ወደኔ እንዳይመጣ ተኮሳትሬ ፊት እነሳዋለሁ እሽ ምን ላርግ!?" አልኳት፡፡ "ተረጋግተሽ ቅረቢው አሁን እንተኛ" ብላ አቅፋኝ ተኛች፡፡
እማማየ በጠዋት የመነሳት ልምድ ቢኖራቸውም ዛሬ ግን ከወትሮው ተለዩብኝ፡፡ በጠዋት ተነሱ ቤቱ ይዘጋጅ ቶሎ ቁርስ ስሩ ማለት ጀመሩ፡፡ እኔ ራሴን ስላመመኝ ሪምን ስሪ ብየ መልሸ ከአዩ ጋር ተኛሁ፡፡ በተኛሁበት ከአዩ ጋር ስጫወት ሪም "ተነሱ ቁርስ ደርሷል" ብትለንም ጨዋታችንን አላቆምንም ቢያመኝም አዩን ደስ እንዲለው ብየ ጨዋታየን ቀጥያለሁ፡፡
......ከውጭ "አሰላሙአለይኩም" የሚል የወንድ ድምፅ ሰማሁ፡፡ ድምፁን ስሰማ ደነገጥኩ ወደ ሪም ዞርኩ ሪም እኔን እያየች ነበር፡፡
..... አዩ "አቢከይም መጣ" ብሎ ሮጦ ተጠመጠመበት እማማየ "ግባ ልጄ ቁጭበል" ይላሉ "እዚህ ተቀመጥ" አለች ሪም፡፡ እኔ ብቻ አይጥ እንደ ጎረሰች ድመት ልሳኔ ተዘጋ፡፡ ከመኝታየ ተነስቼ ፊት ለፊት ከመፋጠጥ እንደተኛሁ መቅረትን መረጥኩ ቁርስ ሲበሉ ሪም በተኛሁበት ከኔ ጋር በላች፡፡
እማማየ የጠዋት ቡና ይወዳሉና ሁሌም ቡና ይፈላል፡፡ አዩብ ከአብደል ከሪም ጋር ይጫወታል እሱም ልክ እንደሱ እየሆነ ያጫውተዋል ከኃላ ሁኔታቸውን አይቼ ሳኩ፡፡ ቡናው ፈላ እኔ ግን አሁንም አልተነሳሁም፡፡ እማማየ ወደኔ ዙረው "አንች ልጅ ካልተሻለሽ ዝም አትበይ ወደ ሀኪም ቤት እንሂድ"አሉ፡፡"አይ ደህና ነኝ አሁን ይተወኛል" ስላቸው መራምን "አሟት ነው እንዴ?" ብሎ ጠየቃት፡፡
....."አወ ራሷን አሟታል ሱቢሂን በግድ ነው የሰገደችው" አሉት፡፡
ወደኔ ዙሮ " መራም ተነሽ ወደ ሆስቲታል እንሂድ መታየት አለብሽ" አለኝ፡፡
......"አረ አሁን ይተወኛል ለዚህ ደግሞ ሀኪም ቤት መሄድ አያስፈልግም ሪም ፓራሲታሞል ስጭኝ" አልኳትና መድሀኒቱን ወስጄ አረፍ አልኩ፡፡
...አብደል ከራም በተደጋጋሚ መሄድ አለብሽ ቢለኝም ባለመሄድ አቋሜ ፀናሁ... ትንሽ ሲቀንስልኝ ተነስቸ የቆሸሹ እቃወችን ማጠብ ጀመርኩ፡፡ እማማየ "እኔ ልጠበው አንች ተኝ" ቢሉኝም አልሰማኃቸውም፡፡
አብደልከሪም ከጎኔ መቶ ቁጭ አለ ምንም ሳይናገር የማጥበውን እቃ እያጠራ ያስቀምጥ ጀመር፡፡ "አረ ተወው ሂድ ተቀመጥ እኔ አጨርሰዋለሁ ትንሽ ናትኮ" ብለውም አልሰማኝም፡፡ ሰአቱ ሲሮጥ ለጉድ ነው፡፡ የዝሁር ሰላት ደረሰ ዝሁርን ሰግደን ምሳ በልተን እንደጨረስን 8 ሰአት ስራ መግባት አለብኝ እና ለመሄድ ስዘጋጅ......
አብደልከሪም "እንደዚህ አሞሽ ስራ ልትሄጅ ነው!?" አለኝ ድምፁ የሀዘን ቅላፄ አለበት፡፡
....." አወ ደህና ነኝኮ በሉ በቃ ደህና ዋሉ " ብየ ከቤት ልወጣ ስል "ቆይ ጠብቂኝ አሞሻል በዛ ላይ ፀሀይ ነው ባጃጅ ካጣሽ እንኳን ፀሀዩ የበለጥ ያሳምምሻል እኔ ላድርሰሽ"ሲለኝ ደንግጨ ሪምን ተመለከትኳት..............
የመራም ታሪክ ምዕራፍ ➊➍ ነገ ይቀጥላል
Join👇👇
https://www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL

Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5760