tgoop.com/Islam_and_Science/5743
Last Update:
📖 #የመራም_ማስታወሻ
ክፍል ~ ➏
✍ ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ
አባቴ ሱሱ ከአቅሙ በላይ ሆነበት የሚከፈለዉ ደመወዝ አልበቃዉ ሲል ማመን የሚከብድ ይሆናል ብለን አስበነዉ የማናቀዉ በአባቴ ሱስ ምክንያት ተከሰተ.......
ማለቁን በጉጉት ስንጠብቅ የነበረው የቤት ግንባታ አባቢ ከእማ ደብቆ ሽጦታል፡፡ እማ ይሄን ስትሰማ ምንም ማረግ አልቻለችም ሆዷ የብስ ቁስል ብሎ አምርራ አለቀሰች! ልቧ ደጋግሞ ቆሰለ፡፡ ከአባቢ ጋር ለመለያየት ወሰነች ግን ምን ይደረግ እናቴ ነፍሰ ጡር ነች.... እርዚቅ በአላህ እጅ ነዉ ብላ የምታምን ሴት የወሊድ መቆጣጠሪያ መዉሰድ የለባትም እናንተም አድጋችሁ ጎጆ ስቀልሱ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንዳትወስዱ ልጅን አላህ ይሰጣል እሱዉ በእርዚቁ ያሳደገዋል ትለን ነበር... ኡሚ በሆዷ ያለው ፅንስ ከመወለዱ በፊት መለያየት አትችልም፡፡ አባቢ ቤት አልፎ አልፎ ይመጣል ለኛ ግን አለመምጣቱ ሰላም ይሰጠናል፡፡
ኡሚ እርግዝናው በጣሙን ከብዷታል እንደበፊቱ የሚንከባከባት ሰው ዛሬ ከጎኗ የለም፡፡ ጎረቤቶቻችን ግን ያዝኑላታል፡፡ በየአቅማቸው ያገኙትን ያማራትን እየሰሩ ያመጡላታል፡፡ በተለይ ደግሞ እማማየ " አይዞሽ ትንሽ ቀን ነው ልጆችሽ ይደርሱልሻል ጠንክሪ" እያሉ ያፅናኗታል፡፡
ቀን ቀንን እየተካ የጊዜ መቁጠሪያ ሰለዳ ከወር ወር እየተሽጋገረ ይሄው እኔም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ለመሆን በቃሁ፡፡ የፈይሲ ምትክ መፅናኛ ይሆነን ዘንድ ዳግም አዩብ ተወለደ፡፡ ሚስኪን አዩብ ፍቅር ጓዙን ጠቅልሎ ከመጣ በኃላ ዳግም ፍቅርን ሊመልስልን ይሆን የመጣው!? ብየ ራሴን ጠየኩ፡፡ አባቢ አዩብን ሲያይ ፊቱ በደስታ አበራ ግን ምን ዋጋ አለው፡፡ የተጠናወተው ሱስ አቋሙን አሽመድምዶ አልፈስፍሶታል! ሀላፊነትን መሸከም አይችልም፡፡ አባቢ ጥሩ ሞዴል መሆን ስላልቻለ ይሄን የተበላሸ ማንነት እያየ ማደጉ ለአዩብ ጥሩ ስላልሆነ ኡሚ ከአባቢ አርቃ ብቻዋን ማሳደግ ጀመረች፡፡ አባቢም አልተቃወመም " ከኔ የሚማመው ጥሩ ነገር የለም ልጄን አንች አሳድጊው" ብሎ ፈቀደላት፡፡
እማ ብቻዋን ሶስት ልጆችን ማሳደግ ፍርጃ ሆነባት፡፡ እንደበፊቱ ስራ ለመቀጠር ጊዜው አልፏል አሁን ድፕሎማ በድግሪ ተተክቷል፡፡ ለዚህ ደግሞ የእናቴ የሂወት ቀማኛ ሌባ እኔ ነኝ! ምክንያቱም እኔ በመወለዴ ምክንያት ነው ኡሚ ስራ ያቆመችው፡፡ ከስራ ሁሉ በላጭ እኔን አድርጋ መረጠችን! ታዳ ያኔ በፍቅር አታልየ የሰረኩዋትን ሂወት ዛሬ እንዴት ልመልስላት!?
እማ ለኛ ስትል እኛን ለማኖር ብላ የቀን ስራ መስራት ጀመረች እንጀራ መጋገር ልብስ ማጠብ ቤት ማፅዳት የእማ ቆሚ ስራዋ ሆነ፡፡
በትምህርት እንዳንሰንፍ ትመክረናለች፡፡ " እናተ ጠንክራችሁ ተማሩና ስራ ስትይዙ ከዚህ ሂወት ገላግላችሁ ታሳርፉኛላችሁ!" ትለናለች፡፡ እኔም ሆንኩ ሪም በትምህርታችን አንታማም፡፡ ለማሚ ስል እሷን ከዚህ ሂወት ለመገላገል ስል ከወትሮው በበለጠ መልኩ ጠነከርኩ፡፡
ከትምህርት ሰአት ውጭ ቆሎ፣ ስካር ድንችና የተቀቀለ እንቁላል ከ11 ሰአት በኅላ መንገድ ዳር እየሸጥኩ ኡሚን ማገዝ ጀመርኩ፡፡ ሪም አዩብን መንከባከብና መጠበቅ ስራዋ ነው፡፡ ቅዳሜና እሁድ ደግሞ የቤት ፅዳቱን እኔ እሰራለሁ፡፡ ኡሚ የምትሰራላቸው ሰወች በፊት የነበራትን ሂወት ስለሚያውቁ ያዝኑላታል፡፡ በተለይ ደግሞ ወይዘሮ ጥሩወርቅ በጣም ያዝኑልናል ከደመወዟ በላይ ጨምራ ነው የምትሰጣት ከዛ በተጨማሪ ደግሞ ሽሮ፣በርበሬ፣ የጤፍ ዱቄት እንጀራ በጋገረች ቁጥር እንጀራም ይሰጡናል፡፡ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ስራ ባይኖራቸውም ልጆቻቸው አንቀባረው ያኖሯቸዋል፡፡ ከባለቤታቸው ከአቶ አለማየሁ ጋር በተንጣለለ ጊቢ ውስጥ ከአምስት ተከራይ ጋር ይኖራሉ፡፡
እኔም እሁድ ቀን የወ/ሮ ጥሩወርቅን ቤት ለማፅዳት በጧት ሄድኩኝ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ልጃቸው ጋር ጀርመን ሂደዋል፡፡ አቶ አለማየሁ ደግሞ ሁሌም እሁድ እሁድ ቤተክርስቲያን የመሄድ ልምድ ስላላቸው በጧት የነሱን ጨርሸ ወደ ሌላ ለመሄድ አስቤ ነበር፡፡
ቤቱንም ጊቢውንም አፅድቸ እንደጨረስኩ ለመሄድ የጊቢውን በር ስከፍት አቶ አለማየሁ ጋር ፊት ለፊት ተገጣጠምን......
የሰዉ ልጅ ኑሮ አንዱን ሲይዙት ሌላዉ ይጎላል .. ጎዶሎዉን ለመሙላት ሲባል ደግሞ ባልጠበቁትና ባልገመቱት ሰአት ከሌላ አዲስ ችግር ጋር ያላትማል፡፡
አይ የኔ መከራ አለማለቁ....
አቶ አለማየሁ ምን አስበዉ ይሆን ???
#ክፍል ➐
ይቀጥላል
join👇👇
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5743