tgoop.com/Islam_and_Science/5717
Last Update:
#እኔ_ሆይ_ተይ_በቃ 🤦♀
#የቆራጧ_ሴት_ማስታወሻ_በግጥም ✍
እኔ ሆይ ተይ በቃ እራስሽን አትደልይ
ገብቶሽ እንዳልገባው እውነትን አትከልይ
••• ትናንት •••
ለማይሆንሽ ፍቅር
ይሆናል በማለት ደክመሻል ታመሻል
የራስሽን ትተሽ ስለሰው ኑረሻል
መሳቅ ሲኖርብሽ ተክዘሽ በማልቀስ
እድልሽን ስትረግሚ ወዲህም በመውቀስ
ከደስታ ተጣልተሽ ተላምደሽ ከብሶት
መከረኛ ጎንሽ ናፍቆ ድሎት ምቾት
ከሰው በመገለል በብቸኝነት ጎን
አንገትሽን ደፍተሽ ገፍተሻል ብዙ ቀን
አሁን ያ ቀን አልፏል
አንቺ ግን ቁመሻል
ለምን? ለምን ? ለምን ? 🤔
እንዴትስ በዚህ ልክ እኔነትሽን ጣልሽ
ነቅተሽ እንዳልነቃ ካላንቀላፋሁ አልሽ
•••• ትናንት ••••
መሄድ ቻልኩ ብለሽ መድረሻሽን ሳትለይ
እንዲሁ ስትጓዥ በግምት መንገድ ላይ
ሳደርሽ ሲመሽብሽ ድካም ስታተርፊ
በዋዛ ፈዛዛ እድሜንሽን ስትገፊ
ድሮን አባክነሻል ፈቅደሽም ጥለሻል
አዎን ሀቁ ይህ ነው ልቦናሽም ያውቃል
••• ትናንት ••••
ያለቦታሽ ሁነሽ ከማይሆንሽ ስፍራ
ቅን የዋህነትሽ ተቆጥሮ እንደተራ
እንደ ሞኝ ተስለሽ በጅላጅል ቀለም
ወርደሽ ከደረጃሽ ቁመሽ ከሰው አለም
ሲያወሩሽ እያመንሽ
ሲያዙሽ እያደረግሽ
እንዳሉሽ እየሆንሽ
ያንቺን ሂዎት ጉዞ ሌላ እየወሰነው
አንቺ እንዳንቺ ሳትኖሪ ጊዜን አባከንሽው
ዛሬ ግን ይበቃል
ግቢ ለራስሽ ቃል
ያለፈውን ንቀሽ ቆጥረሽ እንዳበቃ
እንዳዲስ ለመኖር ወስኝ አሁን በቃ
ከመጣሽው መንገድ ይግባሽ ከንቅፋቱ
ንቂ ከቅዠትሽ ተፋጠጭ ከውነቱ
ላንቺ አይመጥንሽም ሳይኖሩ መሞቱ
ተንቀሳቀሽ እኔ ወደፊት ተራመጅ
የተወሽን ትተሽ ከአቻሽ ተሰደጅ
በተኖረ ታሪክ ባለፈ ትዝታ
መጪውን አትጋርጅ
አዎ አሁን ይበቃል 🚶♀
እኔ ሆይ ተይ በቃ እራስሺን አትደልይ
ገብቶሽ እንዳልገባው እውነትን አትከልይ
#ሼን ✍
Join👇
https://www.tgoop.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Share with your friend now:
tgoop.com/Islam_and_Science/5717