IBNUMUNEWOR Telegram 882
በመውሊድ ላይ ስለሚፈፀመው ጭፈራ ዑለማዎች ምን እንዳሉ ታውቃለህ?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
በመውሊድ በዓላት የተከበሩ የአላህ ቤቶች በጭብጨባ፣ በውዝዋዜና በጭፈራ ክብራቸው ይደፈራል፡፡ ይሄ ደግሞ አላህ እንዲህ ሲል ከሃዲዎችን ከወቀሰባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው፡-
(وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَیۡتِ إِلَّا مُكَاۤءࣰ وَتَصۡدِیَةࣰۚ)
"በቤቱ (በከዕባ) ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡" [አልአንፋል፡ 35]

የአራቱም መዝሀብ ተከታዮች ይህንን ድርጊት ያወግዛሉ፡፡ በጭብጨባ፣ በውዝዋዜና በጭፈራ “ወደ አላህ እቃረባለሁ፣ ዒባዳህ ነው” የሚል እምነት አደገኛ ብልግና ነው፡፡ እንዲያውም ይሄ ከክርስቲያኖች የተኮረጀ ጥመት ነው፡፡ ዛሬም ዝላይና ጭፈራን አምልኮት ያደረጉት ጴንጤዎች ናቸው፡፡ ሃያሉ ጌታ እንዲከበሩና ስሙ እንዲወሳባቸው ባዘዘባቸው መስጂዶች ውስጥ ድቤ መደብደብ፣ ማጨብጨብና መጨፈር እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው፡፡ ይህን ቆሻሻ ተግባር መቃረቢያ አድርጎ ማሰብ ደግሞ የለየለት ጥመት ነው፡፡ እንዲያውም ኢብኑል ጀውዚይ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
وقد نفر جماعة من المتصوفة خلقًا من الخلق عن الكسب، وأوحشوا بينهم وبينه، وهو دأب الأنبياء والصالحين، وإنما طلبوا طريق الراحة، وجلسوا على الفتوح، فإذا شبعوا، رقصوا، فإذا انهضم الطعام، أكلوا، فإذا لاحت لهم حيلة على غنيٍّ، أوجبوا عليه دعوةً، إما بسبب شكر، أو بسبب استغفار. وأَطَمُّ الطامات ادعاؤهم أن هذا قربةٌ! وقد انعقد إجماع العلماء أن من ادعى الرقص قربة إلى الله تعالى، كفر،
“ከሱፍያ የሆኑ ክፍሎች በርካታ ህዝቦችን ስራ ከመስራት አርቀዋል፡፡ በሱ (በስራ) እና በነሱ መካከል ባይተዋርነትን አንግሰዋል፡፡ ግና ስራ የነብያትና የደጋጎች ፈለግ ነው፡፡ እነዚህ የፈለጉት ግን የእረፍትን መንገድ ነው፡፡ በየምግቡ ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ሲጠግቡ ጊዜ ይደንሳሉ፡፡ ምግቡ ሲፈጭ ይበላሉ፡፡ በሃብታም ላይ የሆነ ብልጠት ሲገለጥላቸው በምስጋና ወይም በንስሃ ስም ግብዣ እንዲያዘጋጅ ግድ ያደርጉበታል፡፡ ከመዐቶቻቸው ሁሉ የከፋው መዐት ግን ይህንን (ጭፈራ) መቃረቢያ (ዒባዳ) አድርገው መሞገታቸው ነው፡፡ ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው እንደሚከፍር በርግጥም የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጥሯል፡፡” [ሶይዱል ኻጢር፡ 168]

ኢማሙ ማሊክ፡- “እኛ ዘንድ ሱፍያ የሚባሉ ሰዎች አሉ፡፡ በብዛት ይበሉና ከዚያ ያንጎራጉራሉ፡፡ ከዚያም ተነስተው ይጨፍራሉ” ሲሏቸው “ህፃናት ናቸው?” ብለው ጠየቁ፡፡ “አይደሉም” አሏቸው፡፡ “እብዶች ናቸው?” ሲሉ “አይደሉም፡፡ ሸይኾች ናቸው” አሏቸው፡፡ “እኔ ከኢስላም ሰዎች ይህን የሚሰራ አንድም አልሰማሁም” አሉ፡፡ [ተርቲቡል መዳሪክ: 2/53]

አቡበክር አጦርጡሺም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “የሱፍያ አካሄድ ቦዘኔነት፣ መሀይምነት እና ጥመት ነው፡፡ ኢስላም ማለት የአላህ ቁርኣንና የመልእክተኛው ሱንና እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ዳንስና ውዝዋዜ የመጀመሪያ የፈጠሩት የሳሚሪ ባልደረቦች ናቸው (በነብዩ ሙሳ ዘመን)፡፡ ያኔ ድምፅ ያለው የወይፈን አካልን አምላክ ሲያደርግላቸው ጊዜ መጥተው ዙሪያውን ይጨፍሩና ይወዛወዙ ነበር፡፡ ማለትም ጭፈራ የከሃዲዎችና የወይፈን አምላኪዎች ሃይማኖት ነው፡፡ የነብዩ ﷺ እና የሶሐቦቻቸው ጉባኤ ልክ ከራሳቸው ላይ ወፍ ያረፈ እስከሚመስል መረጋጋት ነበራቸው፡፡ እነዚህን ሰዎች አሚሩ መስጂድ ውስጥም ይሁን ሌላ ቦታ ከመፈፀም ሊከለክላቸው ይገባል፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ከነሱ ጋር ሊካፈል፣ በጥፋትም ላይ ሊያግዛቸው አይፈቀድለትም፡፡ የማሊክም፣ የአቡ ሐኒፋም፣ የሻፊዒይም፣ የአሕመድም፣ የሌሎችም ሙስሊም ምሁራን መዝሀብ ይህን ነው የሚያዘው፡፡” [ተፍሲሩል ቁርጡቢ፡ 11/238]

አልዒዝ ኢብኑ ዐብዲሰላምም፡- “ጭፈራ ቢድዐ ነው፡፡ አእምሮው ጎደሎ የሆነ እንጂ አይፈፅመውም” ይላሉ፡፡ [ፈታዋ አልዒዝ ኢብኑ ዐብዲስሰላም፡ 318-319]

ይህንን ይዘን በየመውሊዱ መስጂድ ውስጥ አግድም ተሰልፈው፣ ድቤ እየደለቁ፣ ለፉጨት የቀረበ ድምፅ እያወጡ፣ ቀረርቶ በመሰለ ድምፅ እያላዘኑ የሚወዛወዙ የጠመጠሙ መሃይማንን አስቡ፡፡ ከአላህ ቤት ጭፈራ ዲን ሆኖ ሲቀርብ ተመልከቱ፡፡ አላሁል ሙስተዓን!!

ከ “መውሊድ፤ ታሪክ፣ ግድፈት፣ እርምት” መፅሐፍ ተነካክቶ የተወሰደ

tgoop.com/IbnuMunewor/882
Create:
Last Update:

BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/882

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Those being doxxed include outgoing Chief Executive Carrie Lam Cheng Yuet-ngor, Chung and police assistant commissioner Joe Chan Tung, who heads police's cyber security and technology crime bureau. It’s easy to create a Telegram channel via desktop app or mobile app (for Android and iOS): Don’t publish new content at nighttime. Since not all users disable notifications for the night, you risk inadvertently disturbing them. To upload a logo, click the Menu icon and select “Manage Channel.” In a new window, hit the Camera icon. 1What is Telegram Channels?
from us

Telegram Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
FROM American