tgoop.com/IbnuMunewor/7938
Last Update:
ተምረህ ሞተሃል!
~
ተምረህ ነው ለካ
ጤናን ሚያቃውስ - ቅጠል የምትበላ
ቢድዐ 'ሚያማልህ - ሱናን የምትጠላ
ተምረህ ነው ለካ
ሙታን የምታመልክ ሺርክ 'ምታቦካ
ከማስረጃ ያልቅ አጉል ፍልስፍና ያደረገህ ነካ
ተምረህ ነው ለካ
ተውሒድ ሚያልብህ ሱና 'ሚወብቅህ
ተምረህ ነው ለካ
ሺርክ 'ሚጣፍጥህ መረጃ የሚያንቅህ
ተምረህ ነው ለካ
ደሊል 'ሚከብድህ - ሐቅ 'ሚያስጨንቅህ
ተምረህ ነው ለካ
ወንጀል እንደ ጀብዱ ውጭ የምታሰጣ
ኹራፋ ምታሳድ፣ ባዳ 'ምትሳለም የሆንከው ፈጣጣ
ተምረህ ነው ለካ እምነትና ባህል የምታደባልቅ
ተምረህ ነው ለካ
ራስህን በከንቱ፣ አጉል 'ምትቆልል፣ ሌሎችን የምትንቅ
ተምረሃል ለካ!
መማርህ ነው ለካ!
አረቄ ሆኖብህ የሚያወላግድህ
ጉራ የሚንጥህ ፅንፍ 'ሚያስረግድህ
ተምረህ ነው አሉ
ራስህ ፀንፈህ፣ ሁሌ ባንድ አቅጣጫ፣ በፅንፍ የምትከሰው
የራስህን ጀሌ፣ እሽሩሩ እያልከው፣ ሌላውን ከማዶ የምታራክሰው
ቢመርህም ዋጠው!
መማር ይጥቀም እንጂ፣ አይሆንም ዋስትና፣ ለማያስተውሉ
ጠፍጥፈው ለሰሩት፣ ግዑዝ ቁስ አም ^ላኪ፣ ስንት ሊቆች አሉ?
ለላም የሚሰ ^ግዱ፣ ኮምፓስ ጠፍቶባቸው፣ የሚን ቀ ዋለሉ።
ተምረህ ሞተሃልi ድንቄም መማርii
l
ማስታወሻነቱ መማራቸው አረቄ ሆኖባቸው ጥንብዝ፣ ጥብርር ላደረጋቸው፣ እኛ ያላማሰልነው ወጥ አይጣፍጥም ለሚሉ ሁሉ ይሁን።
* ምስሉ ላይ ያለው የአሳ ዝርያ በአማርኛ እንፉሌ በእንግሊዝኛው Blowfish ይባላል። ስያሜው የመጣው ባላንጣዎቹን ለማስፈራራት ራሱን እንደ ፊኛ በአየር ወይም በውሃ ወጥሮ ከትክክለኛ ቁመናው የበለጠ ግዙፍ መስሎ ለመታየት የሚሞክር በመሆኑ ነው። ውስጡ ግን ባዶ ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 13/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)


Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7938