tgoop.com/IbnuMunewor/7936
Last Update:
ዶሪሖችን ማስወገድ
~
የባሰ ፊትና የማይከሰት ከሆነ ከአላህ ውጭ የሚመለኩ ቀብር ላይ የተገነቡ ቤቶችን፣ ግንባታዎችን፣ ዛፎችን፣ ... አፈራርሶ ማስወገድ ይገባል። ይሄ ነው የነብያት ሱና። ይሄ ነው የነብዩ'ላህ ኢብራሂም ተግባር። ለሙሽ ^ሪኮች ምን ነበር ያሏቸው?
{ وَتَٱللَّهِ لَأَكِیدَنَّ أَصۡنَـٰمَكُم بَعۡدَ أَن تُوَلُّوا۟ مُدۡبِرِینَ (57)}
እነሱ ዞር ሲሉ ሊያፈራርሱላቸው በመሀላ አስረግጠው ነገሯቸው። አውርተው አልቀሩም። ይሄውና፡
فَجَعَلَهُمۡ جُذَ ٰذًا إِلَّا كَبِیرࣰا لَّهُمۡ لَعَلَّهُمۡ إِلَیۡهِ یَرۡجِعُونَ (58)}
"(ዘወር ሲሉ) ስብርባሪዎች አደረጋቸው፡፡ ለእነሱ የሆነ አንድ ታላቅ (ጣዖት) ብቻ ሲቀር ወደርሱ ይመለሱ ዘንድ (እርሱን ተወው)፡፡" [አልአንቢያእ፡ 57 - 58]
የነብያችን ﷺ አስተምሮትም እንዲሁ ነበር። የሰለፎቻችንም ተግባር እንዲሁ ነበር። አቡል ሀያጅ አል አሰዲይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
قَالَ لِي عَلِيُّ بْنُ أَبِي طَالِبٍ : أَلَا أَبْعَثُكَ عَلَى مَا بَعَثَنِي عَلَيْهِ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ؟ ( ... وَلَا قَبْرًا مُشْرِفًا إِلَّا سَوَّيْتَهُ)
"0ሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ እንዲህ ብሎኛል፦ 'የአላህ መልእክተኛ ﷺ በላኩብኝ አምሳያ አልክህምን? { ...ከፍ ያለ ቀብር አይተህ (ከሌሎች ቀብሮች ጋር እኩል) ሳታስተካክለው እንዳታልፍ!}' " [ሙስሊም፡ 969]
ባይሆን በደመ ነፍስ መወሰን አይገባም። እርምጃ ከመውሰድ በፊት ጉዳዩ ምን ሊያስከትል እንደሚችል በደንብ ማጤን ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)


Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7936