tgoop.com/IbnuMunewor/7934
Last Update:
{ فَإِن تَنَـٰزَعۡتُمۡ فِی شَیۡءࣲ فَرُدُّوهُ إِلَى ٱللَّهِ وَٱلرَّسُولِ إِن كُنتُمۡ تُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡیَوۡمِ ٱلۡـَٔاخِرِۚ }
"በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ፣ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ከሆናችሁ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት።" [አኒሳእ፡ 59]
መውሊድን ወደ ቁርኣንና ሐዲሥ ስንመልሰው አንድም መሰረት የለውም። ነገር ግን አይናቸውን በጨው አጥበው ሰለፎቹ የማያውቁትን የፈጠራ ትርጉም ይሰጣሉ። የሸሪዐ ማስረጃ ውስጥ ከሌለ ደግሞ ቢድዐ ነው ማለት ነው። ቢድዐ ደግሞ የፈለገ ቢያሽሞነሙኑት ጥመት ነው። ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ፦
من ابتَدَعَ في الإسلامِ بِدعةً يَراها حَسنةً فقد زَعَمَ أنَّ مُحَمَّدًا خانَ الرِّسالةَ! لأنَّ اللهَ يَقولُ: الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ، فما لم يَكُن يومَئِذٍ دينًا فلا يَكونُ اليَومَ دينًا
“በኢስላም ውስጥ አዲስ ነገር (ቢድዐ) ፈጥሮ መልካም ነው ብሎ ያሰበ ሰው፣ በእርግጥ ሙሐመድ መልእክታቸውን አጉድለዋል ብሎ ሞግቷል። ምክንያቱም አላህ፡ ‘ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለእናንተ ሞላሁላችሁ’ ብሏልና። ስለዚህ በዚያን ጊዜ ሃይማኖት ያልነበረ ነገር፣ ዛሬ ሃይማኖት ሊሆን አይችልም።” [ዳሪሚ፡ 141]
መውሊድ ያኔ ዲን አልነበረም። ስለዚህ ዛሬ የዲን ክፍል ሊሆን አይችልም። ደግሞም ኋላ የመጡ ዓሊሞች ንግግር በተለየ ገላጋይ ዳኛ የሚሆንበት አመክንዮ የለም። የፈቃጆቹ ወሕይ፣ የከልካዮቹ ረእይ የሚሆንበት ሁኔታ የለም። አሁንም ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ “ከአላህ መልእክተኛ በኋላ ንግግሩ የሚያዝለትና የሚመለስበት ያልሆነ አንድም የለም” ይላሉ። [ጃሚዑ በያኒል ዒልሚ ወፈድሊሂ፡ 2/91]
[ሐ]፦ የፈቃጅ ዝርዝራቸው ራሱ ጤነኛ አይደለም!
* ከፊሎቹ ሶሐቦችን ጨምሮ እንደ ኢማሙ ማሊክ ያሉ ቀደምት አኢማዎችን በመሳደብ የሚታወቁ እንደ ከውሠሪ ያሉ ሙ ^ጅ ^ ሪም ጀ -ህ ^ሚዮች ናቸው። እነዚህን ማን ከቁም ነገር ይቆጥራል?! (ይህንንና ተከታዮቹን ነጥቦች እመለስባቸዋለሁ ኢንሻአለህ።)
* ከፊሎቹ ከመውሊድ በከፋ የአላህን ሲፋት ማስተባበል፣ ኢርጃእ፣ በቀደር ጉዳይ ላይ ጀብር፣ የመሳሰሉ ጥፋቶች ያሉባቸው አሻዒራዎች ናቸው። ካሉባቸው ከባባድ የዐቂዳ ችግሮች አንፃር መውሊድ ቀላሉ ነው ሊባል ይችላል። ልክ የ0ቂዳ ጥፋቶቻቸውን እንደማንቀበለው ቢደዐ የሚደግፉ ንግግሮቻቸውንም አሽቀንጥረን እንጥላለን። የቁርኣንና የሱናን ዟሂር መልእክት መውሰድ የኩ ^ f ^ር መሰረት ነው የሚሉ እንዲሁም ቁርኣን በሐቂቃ የአላህ ንግግር አይደለም የሚሉ አሻዒራዎች ጠሞ አጥ ^ማሚዎች ናቸው!
* ከፊሎቹ ለሙታን አምልኮ የሚሟገቱ፣ ኢብኑ ተይሚያንና ኢብኑል ቀዪምን ከኢስላም በማስወጣትና በመዝለፍ የሚታወቁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዑለማኦች ያወገዙትን ኢብኑ ዐረቢና መሰሎቹን ታላላቅ የአላህ ወሊዮች ናቸው የሚሉ አፈን ^ ጋጮች ናቸው።
* ከፊሎቹ እንደ ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ከሢር ያሉ በስማቸው የተቀጠፈባቸው እንጂ የመውሊድ ድግስን ለመደገፋቸው ማስረጃ የማይቀርብባቸው ናቸው።
* ከፊሎቹ ቢድዐነቱን አስረግጠው የደገፉ ሲሆኑ እንደ ጭፈራ፣ የሴትና ወንድ ቅልቅል፣ ወዘተ ጥፋት ካለበት እንደማይደግፉ በግልፅ የተናገሩ ከመሆናቸው ጋር ነው ዛሬ ላለው ነውረኛ የመውሊድ አከባበር በስማቸው የሚነግዱባቸው።
ስለዚህ የነዚህ አካላት የመውሊድ ደጋፊዎች ዝርዝር እንዲሁ ቢከፍቱት ተልባ ነው። ከቁም ነገር የማይቆጠር። በመጨረሻም በታላቁ ኢማም አውዛዒይ አደራ ፅሁፌን እቋጫለሁ። እንዲህ ነበር ያሉት፦
اصبِرْ نَفسَكَ على السُّنَّة، وقِفْ حَيثُ وقَفَ القَومُ، وقُلْ بما قالوا، وكُفَّ عَمَّا كَفُّوا عنه، واسلُكْ سَبيلَ سَلَفِك الصَّالِحِ؛ فإنَّه يَسَعُكَ ما وَسِعَهم
"ራስህን በሱና ላይ አፅና። ሰዎቹ (ሶሐቦቹ) ከቆሙበት ቁም። እነሱ ያሉትን በል። ከታቀቡት ነገር ታቀብ። የደጋግ ቀደምቶችህን መንገድ ተጓዝ። ለነሱ የበቃቸው ይበቃሀልና።" [ሒልያ፡ 6/144]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 12/1447]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)


Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7934