tgoop.com/IbnuMunewor/7933
Last Update:
የመውሊድ ደጋፊ ምሁራን ዝርዝር ሲፈተሽ
~
መውሊድን የፈቀዱ ዓሊሞች ብለው የስም ዝርዝር የሚለጥፉ ሰዎች አሉ። ይህን የሚያደርጉት ጉዳዩን ዝቅ ሲል ቀላል የፊቅህ ርእስ አድርገን እንድንመለከት፣ ከፍ ሲል ደግሞ የብዙሃን ዑለማእ ድጋፍ ያለው ለማስመሰል ነው። ሁለቱም ግን የሚያስኬድ አይደለም። ሁለቱንም ነጥቦች በየተራ እንመልከት።
1ኛ ነጥብ - መውሊድ ቀላል ጥፋት አይደለም።
አብዛኛው የመውሊድ አከባበር ላይ ግልፅ የሺርክ ተግባራት እና ሌሎች ጥፋቶች በሚፈፀሙበት እውነታ ጉዳዩን ቀላል የፊቅህ ልዩነት አድርጎ ማቅረብ እነዚህ አካላት ሺርክ የማይጎረብጣቸው እንደሆኑ፣ ባስ ሲልም የሺርክ ደጋፊዎች እንደሆኑ ነው የሚያሳየው። መውሊድ የሚፈፀምባቸው እጅግ ብዙ ቦታዎች ዶሪሕ አለባቸው። በቀብሩ ዙሪያና አካባቢው የሚፈፀሙ የሺርክ ተግባራት ሲበዛ ዘግናኝ ናቸው። ከመስጂድ ውስጥ ከሚያዜሟቸው መንዙማዎችም ውስጥ ሺርክ ያለባቸው ብዙ ናቸው። በመስጂድ ውስጥ የሚፈፀሙ ጭፈራዎችም ከመውሊድ ጋር እጅና ጓንት ሆነው የተሰፉ ናቸው። ባጭሩ መውሊድ ከነዚህ ጥፋቶች የመፅዳት እድሉ እጅግ የመነመነ እንደሆነ ከነቃፊ ባልተናነሰ ደጋፊ ዑለማዎች ሳይቀር የገለፁት ሐቅ ነው። ምሳሌ ልጥቀስ፡-
1. ሀይተሚ፡- “ከፊሎቹ (መውሊዶች) ሸር የለባቸውም። ግን ይሄ አልፎ አልፎ ነው ያለው” ይላል። [አልፈታወል ሐዲሢያህ፡ 109]
2. ሙሐመድ ዒሊሽ፡- “ለነብዩ ﷺ መውሊድ ማዘጋጀት የተወደደ አይደለም፣ በተለይ ደግሞ የድምፅን ቅላፄ ከፍ ዝቅ እያደረጉ እንደመቅራትና እንደ ዘፈን ያለ የተጠላ ነገር ያካተተ ከሆነ። በዚህ ዘመን ደግሞ ከዚህ ይቅርና ከዚህ የከፋ ከሆነም ነገር አይተርፍም።” [ፈትወል ዐልዪል ማሊክ፡ 1/171]
ጭፈራ ሲኖርስ? ሲዩጢ እንዲህ ይላል፡-
“ከነዚህም (ከቢድዐዎች) ውስጥ የሆነው በመስጂድ ውስጥ የሚፈፀም ጭፈራ፣ ዘፈን፣ ድቤ መምታት፣ መሰንቆና ሌሎችም የሙዚቃ መሳሪያዎች ናቸው። ይህንን ከመስጂድ ውስጥ የፈፀመ ሊባረርና ሊደ - በ ^ደብ የሚገባው ጠ ^ማ^ማ ሙብ ^ ተዲዕ ነው። ምክንያቱም አላህ እንዲልላቅ ያዘዘውን ነገር እያቃለለ ነውና። … (ከመስጂድ ውስጥ) የዘፈነ ወይም የጨፈረ ቅጣት የሚገባው የሆነ ጠሞ አጥ ^ማሚ ሙብ ^ተዲዕ ነው።” [ሐቂቀቱ ሱና ወልቢድዐ፡ 191]
በሃገራችን በታዋቂ ቦታዎች ያለው አከባበር ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ እንዳለ ይሄ ነው። ከተበላ፣ ከተጠጣ፣ ጫት ከተቃመ በኋላ ከዚያ የሺርክ መንዙማ፣ ጭፈራ፣ የሴትና የወንድ ቅልቅል፣ ዝላይ፣ ማናፋት ነው የሚከተለው። ከዚያ አብዛኛው ሱብሒ የለ፣ ዙህር የለ ተኝቶ ነው የሚውለው።
አከባበሩ የተጠቀሱት ጥፋቶች ባይኖሩበት ራሱ ከቢድ0ነት አያልፍም። ማስረጃ የሌለው ዒባዳ ቢድዐ ነው። ቢድዐ ደግሞ በነብዩ ﷺ አንደበት ጥመት ተብሎ ተገልጿል። [ሙስሊም፡ 867] ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ "ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው፤ ሰዎች መልካም አድርገው ቢያስቡትም" ብለዋል። [አልኢባናህ፡ 205] እንዲያውም የሆነ ሰው ከጎናቸው አስነጠሰውና "አልሐምዱ ሊላህ፣ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ!" አለ። በዚህን ጊዜ ኢብኑ ዑመር "እኔም ምስጋና ለአላህ፣ ሰላም ደግሞ ለአላህ መልእክተኛ ይሁን እላለሁ። ይሁን እንጂ የአላህ መልእክተኛ በዚህ መልኩ አይደለም (ስናስነጥስ እንድንል) ያስተማሩን። ይልቁንም በየትኛውም ሁኔታ 'አልሐምዱ ሊላህ' እንድንል ነው ያስተማሩን" አሉት። [ቲርሚዚ፡ 2738] ኢማሙ ማሊክም ለኢሕራም መነሻ ዘልሑለይፋን ጥሎ ከነብዩ ﷺ ቀብር ሊያደርግ ያሰበውን ሰው "እንደሱ አታድርግ፡፡ እኔ ፈተናን እፈራልሃለሁ!" ነው ያሉት። [ሒልየቱል አውሊያእ፡ 6326] እንጂ "ይሄ ቀላል ነው፤ ምን ችግር አለበት?" አይደለም ያሉት።
2ኛ ነጥብ - ዝርዝራቸው እርባና ያለው ማስረጃ አይደለም! ለምን?
[ሀ]:- መውሊድ የብዙሀን ዑለማእ ድጋፍ የለውም። እንዴት? በረጅሙ የኢስላም ታሪክ ቢፈተሽ:-
1- ድፍን የሶሐባ፣ የታቢዒይ እና የአትባዑ ታቢዒን ትውልድ መውሊድን አላከበረም። እነዚህ ሶስት ትውልዶች ማለት ነብያችን ﷺ "ከሰው ሁሉ በላጩ የኔ ትውልድ ነው። ከዚያም የሚቀጥለው፤ ከዚያም የሚቀጥለው" ብለው የመሰከሩላቸው ናቸው። [ቡኻሪ፡ 2652] [ሙስሊም፡ 2533]
2- እንደ ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ አቡ ዳውድ፣ ... ያለ ድፍን ቀደምት የሐዲሥ ምሁራን ትውልድ መውሊድን አላከበረም። ዛሬ እናንተ በጉልበት ለመውሊድ ማስረጃ የምታደርጓቸውን ሐዲሦች የዘገቧቸው እነዚህ ናቸው። ከናንተ በላይ የሚያውቁ፣ ከናንተ በላይ ነብዩን ﷺ የሚወዱ ከመሆናቸው ጋር አንዳቸውም መውሊድ አላከበሩም።
5- ከነ ኢብኑ ዐባስ፣ ሙጃሂድ፣ ይዞ አምስት፣ ስድስት ክፍለ ዘመን ብትቆጥሩ አንድም የቁርኣን ሙፈሲር መውሊድን አላከበሩም። ዛሬ እናንተ በፈጣጣ ለመውሊድ ማስረጃ የምታደርጓቸውን የቁርኣን አንቀፆች ከናንተ በላይ የሚያውቁ ከመሆናቸው ጋር አመታዊ ጭፈራ ልማዳቸው አልነበረም፡፡ ለነብዩ ﷺ የነበራቸው ውዴታ ከናንተ ያነሰ ሆኖ ይሆን?
6- የአራቱ መዝሀቦች ኢማሞች (አቡ ሐኒፋ፣ ማሊክ፣ ሻፊዒይ እና አሕመድ) መውሊድን አላከበሩም። በነሱም በተከታዮቻቸውም የፊቅህ ኪታቦች ውስጥ ስለ መውሊድ አከባበርና ዋጋው የሚያትት አንድ ርእስ (ባብ / ፈስል / ኪታብ) የለም። የናንተን ያህል ዲኑን ስለማያውቁት ይሆን?
7- በዘመናት ውስጥ ከተተካኩት የሙስሊሙ ዓለም መሪዎች ውስጥ:- ኹለፋኡ ራሺዲን፣ በኑ ኡመያ፣ መሰረታቸውን በግዳድ ላይ ያደረጉት በኑል ዐባስ፣ ሰልጁቆችም እንዳለ መውሊድን አላከበሩም።
8- እንደ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪ፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲ፣ ... ያሉ የአሽዐሪያና የማቱሪዲያ መስራቾችና ቀደምት ተከታዮቻቸው መውሊድን አላከበሩም።
8- እንደ አቡ ዐብዲረሕማን አሱለሚ፣ ቁሸይሪ፣ አቡ ሓሚድ አልገዛሊ፣ ጀይላኒ፣ ... ያሉ ቀደም ያሉ ሱፍዮችም መውሊድን አላከበሩም። ለነብዩ ﷺ ውዴታ ስላልነበራቸው ይሆን?
9- የነብዩን ﷺ ሲራ የከተቡ ቀደምት ፀሐፊዎች ለምሳሌ ኢብኑ ኢስሓቅ፣ ኢብኑ ሂሻም፣ ዋቂዲ፣ ኢብኑ ሰዕድ፣ በላዙሪይ፣ ጦበሪ፣ ሱሃይሊይ፣ ... አንዳቸውም መውሊድን አላከበሩም። ጉዳዩን ስለማያውቁት? ወይስ ስለማይወዷቸው?
10- እንዲሁም ቀደም ብለው የነብዩን ﷺ ሸማኢሎች የከተቡ እንደ ቲርሚዚይ፣ አቡ ኑዐይም አልአስበሃኒ፣ ቃዲ ዒያድ፣ በይሀቂ፣ ወዘተ . አንዳቸውም መውሊድን አላከበሩም።
ይሄ ሁሉ እልፍ አእላፍ ዑለማእ ብዙሃን ሳይሆን የትኛው ዝርዝር ነው ብዙሃን የሚሆነው? የሰለፎቹን ኢጅማዕ በመጣል ከ7ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ የመጡ አካላትን እየዘረዘሩ "ብዙ ነን" የሚል የህፃናት እንቁልልጭ ውስጥ መግባት ሞኝነት ነው። የምትጠቅሷቸው ሁሉም ቢደመሩ ከሶሐባ ትውልድ ጋር የሚነፃፀር የላቸውም።
[ለ]፦ የምትዘረዝሯቸው ዓሊሞች ብዙሃን አይደሉም እንጂ ቢሆኑስ?
ከመቼ ጀምሮ ነው የቁጥር ብዛት መለኪያ የሆነው? እነ ሐሰን ታጁ፣ ኣደም ሙሐመድ እና ኢስሓቅ እሸቱ ያሉ ደፋሮች ከሰለፍ እስከ ኸለፍ ያለፉ ዑለማዎችን ረጋግጠው ለዘፈን ጥብቅና ሲቆሙ የብዙሃን ዑለማእ ተግሳፅ አልገታቸውም። ለመውሊድ የሚዘረዝሯቸው እንዳለ ሙዚቃን ያወግዛሉ። ቢሆንም ደንገጥ እንኳን አይሉም። እነዚህ የዘፈን ጠበቆዎች ደጋፊ ዓሊሞች ጭምር ቢድዐነቱን ለሚመሰክሩበት የመውሊድ ጉዳይ ግን ከሀሰተኛ "ብዙሃን" ጀርባ ያደፍጣሉ። ሁለቱም ቦታ ላይ ሚዛናቸው ስሜታቸው ነው። እንጂ ለማስረጃም ለብዙሃንም ደንታ ያላቸው አይደሉም። በተረፈ የዲን ጉዳይ በወሕይ እንጂ እንደ ፓርላማ በእጅ ብልጫ የሚወሰንበት አይደለም። አላህ እንዲህ ይላል:-
BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)


Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7933