IBNUMUNEWOR Telegram 7925
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
"ኑሩን ከኑሩ ኸለቀው ጀሊሉ"
~
ይሄ ንግግር ሱፊዮች አካባቢ ተደጋግሞ የሚሰማ ነው። ምን ማለታቸው ነው?
* "ኑሩን" ሲሉ ነብዩን ﷺ ማለታቸው ነው።
* "ጀሊሉ" ሲሉ አላህ ማለታቸው ነው።
* "ከኑሩ" ሲሉ ከአላህ ኑር ማለታቸው ነው።
* ኸለቀው = ፈጠረው

ጥቅል መልእክቱ:-
አላህ ነብዩን ﷺ ከራሱ ኑር (ብርሃን) ነው የፈጠራቸው እያሉ ነው።
አንዳንዶቹ ይህንን መነሻ በማድረግ በግልፅ ነብዩ ﷺ የአላህ ክፍል (ጁዝእ/ part) ናቸው ብለዋል። ይሄ መሰረተ-የለሽ እምነት ነው። ለዚህም በተለያዩ ነጥቦች ምላሽ መስጠት ይቻላል።

1- ነብዩ ﷺ ምንም አይነት መለኮታዊ ድርሻ የላቸውም። ፍጡር ናቸው። ባሪያ ናቸው። ባሪያ ደግሞ የአላህ ክፍል ሊሆን አይችልም። መልእክተኛ ናቸው።

2- ነብዩ ﷺ ከኑር (ከብርሃን) ነው የተፈጠሩት የሚሉ አካላት መሰረተ ቢስ ወሬ እንጂ አንድም የቁርኣንም ይሁን የሐዲሥ መረጃ ማቅረብ አይችሉም።

3- በአፈጣጠር በኩል ነብዩ ﷺ እንደሌላው የአደም ዘር ሰው ናቸው። እዚህ ላይ ጥርጣሬ ሊገባን አይገባም። አላህ እንዲህ ሲል አዋጅ እንዲናገሩ አዟቸዋል፦

{قُلۡ إِنَّمَاۤ أَنَا۠ بَشَرࣱ مِّثۡلُكُمۡ}
" 'እኔ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ' በላቸው።" [ከህፍ፡ 110]

4- ወላጆቻቸው እና ዘር ማንዘራቸውም የሚታወቁ ናቸው። እሳቸውን ጨምሮ ሁሉም እንደ ሌላው የሰው ዘር የአደም ዘር ናቸው። አደም ከጭቃ መፈጠራቸው ግልፅ ነው።

5- ነብዩ ﷺ ሞተዋል። ስለዚህ "ከአላህ ኑር ነው የተፈጠሩት፣ የሱ ክፍል (ጁዝእ/ part) ናቸው'' የሚል ሰው የአላህ ክፍል ሙቷል እያለ ነው። ይሄ ሰቅጣጭ ድምዳሜ ነው። ለነገሩ እነዚህ ሰዎች የነብዩን ﷺ መሞትም ሊከራከሩ ይችላሉ። የሱፊያ እምነት በብዙ ነጥቦች ከ0ቅል ጋር የተኳረፈ እምነት ነው። እንኳን ነብዩን ﷺ ፤ በየመንደሩ ያሉ ሸይኾች ሲሞቱ "አልሞቱም፤ ሌላ አገር ወጥተዋል" እያሉ የሚያምኑ ብዙ ናቸው። ለማንኛውም ነብዩ ﷺ መዲና ሞተው ሶሐቦች አጥበው፣ ከፍነው፣ ሶላተል ጀናዛ ከሰገዱባቸው በኋላ ዓኢሻ ቤት ውስጥ ቀብረዋቸል። አላህም ሟችነታቸውን እንዲህ ሲል አስረግጦ ተናግሯል:-

{إِنَّكَ مَیِّتࣱ وَإِنَّهُم مَّیِّتُونَ}
"አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው።" [አዙመር: 30]

"ሲሞት እንገላገለዋለን" ሲሉ ለነበሩ ጠላቶችም ''እርማችሁን አውጡ እሱ አይሞትም" አይደለም ያላቸው። ይሄውና ምላሹ፦
{وَمَا جَعَلۡنَا لِبَشَرࣲ مِّن قَبۡلِكَ ٱلۡخُلۡدَۖ أَفَإِی۟ن مِّتَّ فَهُمُ ٱلۡخَـٰلِدُونَ (34) كُلُّ نَفۡسࣲ ذَاۤىِٕقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ}
"(ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም። ታዲያ ብትሞት እነሱ ዘውታሪዎች ናቸውን? ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት።" [አልአንቢያእ፡ 34-35]

ማምታቻ:-
-
ነብዩ ﷺ ከኑር (ከብርሃን) ነው የተፈጠሩት የሚሉ አካላት አንድ እንዲህ የሚል የሚያቀርቡት "ሐዲሥ" አላቸው፦

أولُ ما خلق اللهُ نور نبيِّكَ يا جابرُ
"መጀመሪያ አላህ የፈጠረው የነብይህን ኑር (ብርሃን) ነው፣ ጃቢር ሆይ!"

ግና ይሄ ወሬ በየትኛውም የሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ የማይገኝ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው። [አሓዲሡን ሙንተሺረህ ላ ተሲሕ፡ ቁ. 393]
ሱፊዩ አሕመድ አልጉማሪ ራሱ መሰረተ ቢስ የፈጠራ ወሬ እንደሆነ ገልጿል።

(ኢብኑ መነወር፣ መስከረም 16/ 2015)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor

tgoop.com/IbnuMunewor/7925
Create:
Last Update:

BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/7925

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Avoid compound hashtags that consist of several words. If you have a hashtag like #marketingnewsinusa, split it into smaller hashtags: “#marketing, #news, #usa. The administrator of a telegram group, "Suck Channel," was sentenced to six years and six months in prison for seven counts of incitement yesterday. Concise Telegram message that reads: "Bear Market Screaming Therapy Group. You are only allowed to send screaming voice notes. Everything else = BAN. Text pics, videos, stickers, gif = BAN. Anything other than screaming = BAN. You think you are smart = BAN. bank east asia october 20 kowloon
from us

Telegram Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
FROM American