IBNUMUNEWOR Telegram 34
በሸይኹል አልባኒ እና “መውሊድ ይፈቀዳል”
በሚል ሰው መካከል የተደረገ ድንቅ ቃለ-ምልልስ
ሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ፡- የተከበሩትን ነብይ ልደት ማክበር ኸይር ነው ሸር?
ሰውየው፡- ኸይር ነው፡፡
ሸይኹል አልባኒ፡- መልካም፡፡ ይህንን ኸይር የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እና ሰሐቦቻቸው አያውቁትም ነበር?
ሰውየው፡- አይ፡፡
ሸይኹል አልባኒ፡- “አይ” ማለትህ አይበቃኝም፡፡ “ይሄ ነገር ኸይር ከሆነ ከአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እና ከሰሐቦቻቸው ይሰወራል ተብሎ ፍፁም የማይታሰብ ነው” ልትል ይገባል፡፡ እኛ ኢስላምንም ኢማንንም በሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መንገድ እንጂ በሌላ አላወቅነውም፡፡ እሳቸው የማያውቁትን ኸይር እንዴት ልናውቅ እንችላለን? ይሄ ፍፁም የማይሆን ነገር ነው!!
ሰውየው፡- የነብዩን ልደት ማክበር እሳቸውን በማሰብ የሚፈፀም ነው፡፡ ይሄ ደግሞ እሳቸውን ማክበር ነው፡፡
ሸይኹል አልባኒ፡- ይቺ የምናውቃት ፍልስፍና ነች፡፡ ከብዙ ሰዎችም እንሰማታለን፡፡ ከኪታቦቻቸውም አንብበናታል፡፡ ግን ግን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰዎችን ወደ ኢስላም ሲጣሩ ወደ ኢስላም በሙሉ ነው የተጣሩት ወይስ ወደ ተውሒድ?
ሰውየው፡- ወደ ተውሒድ::
ሸይኹል አልባኒ፡- አዎ መጀመሪያ የተጣሩት ወደ ተውሒድ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ሰላቶች ተደነገጉ፡፡ ከዚያ ፆም፡፡ ከዚያ ሐጅ፡፡ በዚህ መሰረት ቀጠለ፡፡ አንተም በዚህ ሸሪዐዊ ሱና መሰረት እርምጃ በእርምጃ ተጓዝ፡፡ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የማያውቁት ኸይር በፍፁም እንደማይኖር ተስማምተናል፡፡ ኸይርን ሁሉ ያወቅነው በመልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መንገድ አማካኝነት ነው፡፡ ይሄ መቼም እጅግ ግልፅ ከመሆኑ የተነሳ ማንም አይወዛገብበትም፡፡ እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚጣራጠርን ሙስሊም አይደለም ብዬ ነው የማምነው፡፡ ይህን አባባል ከሚደግፉ የመልእክተኛው ሐዲሦች ውስጥ ((ወደ አላህ የሚያቃርባችሁ ሆኖ ሳላዛችሁ የቀረኝ ነገር የለም)) የሚለው ይጠቀሳል፡፡ እናም መውሊድ ኸይር ከሆነ ወደ አላህ የሚያቃርበንም ከሆነ የግድ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያመላከቱን ነው ማለት ነው፡፡ ነው ወይስ አይደለም? እኔ እያንዳንዱ የምናገረው ቃል ሳያሳምንህ እንድትስማማ አልፈልግም፡፡ “ይቺ ነጥብ አላረካችኝም” የማለት ሙሉ ነፃነት አለህ፡፡
ሰውየው፡- እየተረዳሁህ ነው፡፡
ሸይኹል አልባኒ፡- ጀዛከላሁ ኸይረን፡፡ እንግዲያው ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ((ወደ አላህ የሚያቃርባችሁ ሆኖ ሳላዛችሁ የቀረኝ ነገር የለም)) እንዳሉ አሳልፈናል፡፡ ይህን መውሊድ ማክበር “ይፈቀዳል” ለሚል ሁሉ እንዲህ እንላለን፡- “ይሄ መውሊድ እንደናንተ እምነት ኸይር ነገር ነው፡፡ እንግዲያው ወይ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አመላክተውናል ወይ ደግሞ አላመላከቱንም ማለት ነው፡፡” “አመላክተውናል” ካላችሁ ((ማስረጃችሁን አምጡ እውነተኞች ከሆናችሁ)) እንላለን፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞ መቼም አይቻላቸውም፡፡ የመውሊድ ደጋፊዎች የሚፅፉትን አይተናል፡፡ “ጥሩ ቢድዐ ነው” ከማለት ባለፈ ማስረጃ አይጠቅሱም፡፡ የመውሊዱ ደጋፊዎችም ተቃዋሚዎችም በመልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመንም በክቡራን ሰሐቦች ዘመንም በታላላቅ መሪዎች ዘመንም እንዳልተከበረ ይስማማሉ፡፡ ነገር ግን የሚያከብሩት ሰዎች “መውሊድ ውስጥ ምን ችግር አለበት? ነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለማስታወስ ነው፣ በሳቸው ላይ ሰለዋት ለማውረድ” ወዘተ. ይላሉ፡፡ እኛ ግን “ኸይር ቢሆን ኖሮ ይቀድሙን ነበር” እንላለን፡፡ አንተ እራስህ ((ከሰዎች ሁሉ በላጩ የኔ ዘመን ትውልድ ነው፡፡ ከዚያም የሚከተሏቸው፤ ከዚያም የሚከተሏቸው) የሚለውን የመልእክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲሥ ታውቃለህ፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት ሰሒሕ ሐዲሥ ነው፡፡ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመን ማለት እሳቸውና ሰሐቦቻቸው የኖሩበት ጊዜ ነው፡፡ ቀጥለው የመጡት ታቢዖች ናቸው፡፡ ከነሱ የቀጠሉት ደግሞ አትባዑት-ታቢዒን ናቸው፡፡ እዚህም ላይ ምንም ውዝግብ የለም፡፡ በእውቀትም በተግባርም እኛ ልንቀድማቸው የምንችለው ኸይር ሊኖር ይችላል ብለህ ታስባለህ? ሊሆን ይችላል?
ሰውየው፡- ከእውቀት አንፃር የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዘመናቸው ላሉ ሰዎች “መሬት ትዞራለች” ብለው ቢናገሩ
ሸይኹል አልባኒ፡- ይቅርታ! ባታስቀይስ ደስ ይለኛል፡፡ እኔ የጠየቅኩህ ሁለት ነገር ነው፣ እውቀትና ተግባር፡፡ ከማስቀየስህ በመነሳት አንድ ነገር ግልፅ ላድርግ፡፡ እኔ የማወራህ እውቀት ሸሪዐዊ እውቀትን እንጂ ለምሳሌ ህክምናን አይደለም፡፡ የዛሬ ዶክተር ከኢብኑ ሲና ይበልጣል፡፡ ምክኒያቱም ከረጅም ዘመናት እጅግ በርካታ ተሞክሮዎች በኋላ ስለመጣ ነው፡፡ ባይሆን ይህ እውቀቱ በራሱ አላህ ዘንድ አያስሞግሰውም፡፡ በምርጥነቱ ከተመሰከረለት ትውልድም አያስበልጠውም፡፡ የሚያስሞግሰው በሚያውቀው እውቀት ብቻ ነው፡፡ እኛ ግን እያወራን ያለነው ስለ ሸሪአዊ እውቀት ነው ባረከላሁ ፊክ፡፡ ይህን ልታጤን ይገባል፡፡ ስለዚህ “እኛ ከነሱ የበለጠ ልናውቅ እንችላለን ብለህ ታምናለህ?” ብየ ስጠይቅህ እያልኩ ያለሁት ሸሪዐዊ እውቀትን ነው እንጂ እንደ ጂኦግራፊ፣ ስነ-ፈለክ፣ ኬሚስትሪና ፊዚክስ ያሉ ተሞክሯዊ እውቀቶችን ማለቴ አይደለም፡፡ ምሳሌ ውሰድ በዚህ ዘመን ያለ አንድ በአላህና በመልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የማያምን ከሃዲ በነዚህ የእውቀት ዘርፎች ከማንም በላይ ሊያውቅ ይችላል፡፡ ታዲያ ይህ እውቀቱ ወደ አላህ መቃረቢያ (ዙልፋ) ይሆነዋልን?
ሰውየው፡- አይሆነውም፡፡
ሸይኹል አልባኒ፡- ስለዚህ አሁን የምናወራው ስለዚህኛው የእውቀት ዘርፍ አይደለም፡፡ የምናወራው በራሱ ወደ አላህ ስለሚያቃርበን እውቀት ነው፡፡ ከአፍታ በፊት መውሊድን ስለማክበር እያወራን ነበር፡፡ ጥያቄውን እንመልሰው፡፡ ዳግም ሳታስቀይስ መልሱን በግልፅ እንደማገኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እናም በተሰጠህ አእምሮና ግንዛቤ ስታስበው በመጨረሻው ዘመን ያለነው እኛ ከሰሐቦች፣ ከታቢዖችና ከሙጅተሂድ አኢማዎች የበለጠ ሸሪዐዊ እውቀት ሊኖረን ይችላል ብለህ ታምናለህን? ወደ መልካም ስራና ወደ አላህ በመቃረብስ ከነኚህ መልካም ቀደምቶች እንቀድማለን ብለህ ታስባለህ?
ሰውየው፡- ሸሪዐዊ እውቀት ስትል የቁርኣን ተፍሲር ማለትህ ነው?
ሸይኹል አልባኒ፡- በቁርኣኑ ተፍሲርም ከኛ የበለጠ አዋቂዎች ናቸው፡፡ በመልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲሥ ማብራሪያም ከኛ የበለጠ አዋቂዎች ናቸው፡፡ ባጠቃላይ የሸሪዐ እውቀት እነሱ ከኛ የበለጠ አዋቂዎች ናቸው፡፡
ሰውየው፡- ቁርኣን ተፍሲርን በተመለከተ ምናልባት በመልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመን ከነበረው የዛሬው ሳይበልጥ አይቀርም፡፡ ለምሳሌ ((ተራሮችንም ስታይ የደመና አስተላለፍ የሚያልፉ ሆነው ሳለ የቆሙ ናቸው ብለህ ታስባለህ፡፡ የአላህ ጥበብ ነው! ሁሉን ነገር ያስዋበ ጌታ! እርሱ በምትሰሩት ሁሉ ውስጥ አዋቂ ነው)) (አን-ነምል፡ 88) የምትለዋን የቁርኣን አያ በተመለከተ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዘመናቸው ለነበረ አንድ ሰው “መሬት ትዞራለች” ቢሉ አንድ የሚያምናቸው ይኖር ነበር? አንድም ሰው አያምናቸውም ነበር?!!
ሸይኹል አልባኒ፡- ስለዚህ ቅር እንዳትሰኝና ሁለተኛ እያስቀየስክ እንደሆነ እንመዝግብልህ፡፡ ወንድሜ እኔ የምጠይቀው ጥቅል እንጂ ነጠላ ነገሮችን አይደለም፡፡ በጥቅሉ ስንጠይቅ፡- ኢስላምን በጥቅሉ ማነው የበለጠ የሚያውቀው?
ሰውየው፡- እሱ ግልፅ ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም

tgoop.com/IbnuMunewor/34
Create:
Last Update:

BY Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Share with your friend now:
tgoop.com/IbnuMunewor/34

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Unlimited number of subscribers per channel With Bitcoin down 30% in the past week, some crypto traders have taken to Telegram to “voice” their feelings. "Doxxing content is forbidden on Telegram and our moderators routinely remove such content from around the world," said a spokesman for the messaging app, Remi Vaughn. Other crimes that the SUCK Channel incited under Ng’s watch included using corrosive chemicals to make explosives and causing grievous bodily harm with intent. The court also found Ng responsible for calling on people to assist protesters who clashed violently with police at several universities in November 2019. Select: Settings – Manage Channel – Administrators – Add administrator. From your list of subscribers, select the correct user. A new window will appear on the screen. Check the rights you’re willing to give to your administrator.
from us

Telegram Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
FROM American