🩺 በዓልና ጤና 🩺
በአገራችን በዓላት የሚከበሩት በስጋና በአልኮል መጠጦች እንዲሁም በተለያዩ ባህላዊ ምግቦች ነው። ታድያ አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር እንዲሆንልን እየተመኘሁ 'ዓመት በዓልና ጤና' በሚል ርእስ ትንሽ ልበላቹ !
👨⚕️ በበዓል ግዜ ስብ የበዛባቸው ምግቦች ማዘውተር የተለመደና የብዙ ኢትዮጵያውያን ልምድ ነው።
ለመሆኑ ስብ ምንድነው? ስብ በኬሚካላዊ አገላለጽ ትራይግሊሰራይድ (triglyceride) በመባል የሚታወቅ የኦርጋኒክ ውህድ ነው። ትራይግሊሰራይድ በግላይሰሮል እና በሶስት ፋቲ አሲዶች (3 fatty acids) የተሰራ ነው። ስብ ለሰውነታችን በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ዋና ዋና የምግብ አይነቶች (macronutrients) አንዱ ሲሆን ከሚሰጠን ጥቅሞች የተወሰኑ ስናይ፤
✍️ስብ የሃይል ምንጭ በመሆን ስብ ሰውነታችን ሃይል እንድያገኝ ይረደናል። አንድ ግራም ስብ ከፕሮቲን እና ከካርቦሃይድሬት በሁለት እጥፍ የሚበልጥ ሃይል (ካሎሪ) ይሰጣል።
✍️እንደ ቫይታሚን A, D, E, እና K የመሳሰሉ ጠቃሚ ቫይታሚኖች ለማጓጓዝ ይጠቅመናል። በስብ ውስጥ የሚሟሙ ቫይታሚኖች (fat-soluble) ስለሆኑ ሰውነታችን እነዚህን ቫይታሚኖች በአግባቡ እንዲጠቀምባቸው ስብ ያስፈልገዋል።
✍️የሰውነታችን ሙቀት መቆጣጠሪያ ሁኖ ያገለግለናል። የሰውነት ሙቀት እንዳይቀንስ ይረዳል።
✍️የሰውነት ሴሎችን መገንቢያ ሁኖ የሰውነት ሴሎች ግድግዳ ላይ አስፈላጊ አካል በመሆን ይረዳናል።
🩺 ታድያ ስብ ይሄን ያክል ጥቅም ካለው እንዴት ለጤናችን ጉዳት ያስከትላል? መቼ ነው ስብ የጤና እክል የሚፈጥረው?
ስብ የጤና እክል የሚፈጥረው በሁለት መንገድ ከፍለን ማየት እንችላለን። በመጠንና በዓይነት!
ስብ ጤናማ ስብ (Unsaturated Fats) እና ጤናማ ያልሆኑ ስቦች (Saturated and Trans Fat) ብለን በዓይነታቸው ለሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን።
👨⚕️ ጤናማ ስቦች የሚንላቸው በዋናነት የሚገኙት እንደ አቮካዶ፣ ለውዝ፣ የዓሳ ዘይት፣ የወይራ ዘይት እና የሱፍ አበባ ዘይት ባሉ ምግቦች ውስጥ ነው። የደም ኮሌስትሮል መጠንን በመቀነስ የልብ ጤናን ይጠብቃሉ። እነዚህ ስቦች በብዛት መወሰድ ለጤና ችግር አይዳርጉም።
👨⚕️ ጤናማ ያልሆኑ (Saturated and Trans Fats) የሚንላቸው ስቦች የሚገኙት ደግሞ እንደ ቀይ ስጋ፣ ቅቤ፣ አይብ፣ የአሳማ ስጋ (bacon) እና በንግድ የተዘጋጁ ምግቦች (processed foods) ውስጥ ነው። እነዚህን ስቦች ከመጠን በላይ መውሰድ የደም ኮሌስትሮልን መጠን ከፍ በማድረግ ለልብ በሽታ፣ ለደም ግፊት እና ለሌሎች የጤና ችግሮች ይዳርጋሉ። በተለይም ትራንስ ስብ (Trans fats) በከፍተኛ ሁኔታ ለጤና ጎጂ ነው።
🩺 ሌላው ስብ በምንጠቀምበት መጠን እንዴት ይወሰናል?
ጤናማ ስብም ቢሆን ከመጠን በላይ መውሰድ የጤና እክል ይፈጥራል።ስብ ከፍተኛ ካሎሪ ስላለው፣ ከሚያስፈልገን በላይ ስንመገብ ክብደት መጨመር ይከተላል። ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት ደግሞ ለስኳር በሽታ፣ ለደም ግፊት፣ ለልብ በሽታ እና ለመገጣጠሚያ ህመም ይዳርጋል።
በአጠቃላይ፣ ለጤናችን ትኩረት መስጠት ከፈለግን የምንጠቀመው ስብ አይነት ላይ መጠንቀቅ እና ጤናማ ያልሆኑ ስቦችን መቀነስ አስፈላጊ ነው። እንዲሁም ማንኛውንም አይነት ምግብ ከመጠን በላይ መውሰድ ለጤናችን ጠቃሚ አለመሆኑን ማስታወስ ይገባል።
🩺 ለመሆኑ ስብ የበዛበት ምግብ አዘውትሮ መጠቀም ምን ዓይነት በሽታ ልያስከትል ይችላል?
👨⚕️ በዓል ምክንያት በማድረግ ስብ የበዛበት ምግብ በብዛት የመመገብ ባህል ያለን ማሕበረሰብ ስለሆንን ለጤናችን ተስማሚ በሆነ ዘዴ መመገብ እንዳለብን እየገለፅኩ ለጤና ጎጂ የሆኑ ስቦች፣ በተለይም የሞሉ ስቦች (saturated fats) እና ትራንስ ስቦች (trans fats) በብዛት ሲወሰዱ የሚያስከተሉትን ዋና ዋና ጉዳቶች እንመልከት።
1. የልብ እና የደም ስር ስርዓት ችግሮች
✍️የኮሌስትሮል መጠን በመጨመር ስብ የበዛባቸው ምግቦች በደም ውስጥ ያለውን “መጥፎ” ኮሌስትሮል (LDL) መጠን ይጨምራሉ። ይህም የደም ስሮች ግድግዳ ላይ ስብ እንዲከማች ያደርጋል፣ የደም ስሮችን በማጥበብና በማደናቀፍ የደም ዝውውርን ይቀንሳል።
✍️የደም ግፊት በመጨመር የደም ስሮች መጥበብ እና መደናቀፍ የደም ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል። ይህ ደግሞ ለልብ ህመም፣ ለስትሮክ እና ለሌሎች የደም ዝውውር ችግሮች ያጋልጣል።
2. ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና ተያያዥ ችግሮች
✍️የካሎሪ ብዛት በመጨመር ስብ ከሌሎች ንጥረ ነገሮች (ከካርቦሃይድሬት እና ፕሮቲን) በሁለት እጥፍ የሚበልጥ ነው። ብዙ ስብ መመገብ በቀላሉ ከመጠን በላይ ካሎሪ እንዲወሰድ ያደርጋል፣ ይህም የሰውነት ክብደት እንዲጨምር ያደርጋል።
✍️ኢንሱሊን መቋቋም (Insulin resistance) እና የስኳር በሽታ ያስከትላል። ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለኢንሱሊን መቋቋም (insulin resistance) ዋና መንስኤ ነው። ይህ ደግሞ ሰውነት ኢንሱሊንን በአግባቡ እንዳይጠቀም ያደርገዋል፣ ይህም ለዓይነት 2 የስኳር በሽታ ያጋልጣል።
3. የጉበት ችግሮች
✍️ፋቲ ሊቨር (Fatty liver) እንዲፈጠር ያደርጋል። ስብ የበዛባቸው ምግቦችን በብዛት መመገብ ስብ በጉበት ውስጥ እንዲከማች ያደርጋል። በተደጋጋሚና ለብዙግዜ ስብ የበዛባቸው ምግቦች ስንመገብ ወደ ጉበት መቆጣትና ጉዳት ሊያመራ ይችላል።
4. የካንሰር ተጋላጭነት
✍️አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ የሳቹረትድ ስቦች እና ትራንስ ስቦች በብዛት የሚገኙባቸውን ምግቦች መመገብ ለተለያዩ የካንሰር አይነቶች፣ በተለይም ለአንጀትና ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድልን እንደሚጨምሩ ይገልፃሉ።
ስብ የበዛባቸው ምግቦች በመቀነስና ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት በመከተል ከላይ ከዘረዘርኳቸው በሽታዎችና ተዛማጅ የጤና እክል ራስዎና ቤተሰብዎ ይጠብቁ።
መልካም አዲስ ዓመት!
➛ አዘጋጅ -ፍስሃ አባይ (medical student)
➛አርታኢ - ዶ/ር አብርሃ አስፋ (intern)
➛ዋቢዎች (Reference -
1. The World Health Organization (WHO)
2. The Centers for Disease Control and Prevention (CDC)
3. The American Heart Association (AHA)
4. የኢትዮጵያ ምግብ-መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ (Ethiopia: Food-Based Dietary
5. Prevent and Reverse Heart Disease by Dr. Caldwell B. Esselstyn
@HakimEthio

❤19👏8👍1
tgoop.com/HakimEthio/36124
Create:
Last Update:

BY Hakim

Share with your friend now:
tgoop.com/HakimEthio/36124