HISCULHEROFETHIOPIA Telegram 5734
Forwarded from Bketa @¥
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
          አሜን
"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"         
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
                   ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም

     🛎  ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲

           አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥር በዚች ቀን የከበሩ ጻድቃን ሠለስቱ ደቂቅ አናንያ አዛርያ ሚሳኤል የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው።

❖ እሊህም ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮአቄም ልጆቹ ናቸው ዳንኤልም የእኅታቸው ልጅ ነው በምርኮ ጊዜም ከእስራኤል ልጆች ጋራ ተማርከው ወደ ባቢሎን ወረዱ፤ ከእስራኤል ልጆች ምርኮ ውስጥ በመብልና በመጠጥ እያስተማረ አሳድጎ በሠራዊቱ መካከል ጭፍሮቹ ያደርጋቸው ዘንድ ነውር ነቀፋ የሌለባቸውን ወጣቶች ንጉሥ መረጠ፤ እሊህም ከተመረጡት ውስጥ የተቆጠሩ ሆኑ የእኅታቸው ልጅ ዳንኤልም፤ ምግባቸውን በሚሰጡአቸው ጊዜ አረማውያን ከአረዱአቸው ውስጥ መብላትን አልወደዱም ከንጉሥ ማዕድም ከሚመጣ ከሥጋው እንዳያበላቸውና እንዳያጠጣቸው አለቃውን ለመኑት።

❖ እግዚአብሔርም በባለሟሎች አለቃ ፊት ቸርነቱን አደረገላቸው፤ የባለሟሎች አለቃም ንጉሡ ጌታዬን እፈራዋለሁ የምትበሉትንና የምትጠጡትን ምግባችሁን ስለ አዘዘ ከባልንጀሮቻችሁ እናንተን ከስታችሁ ቢያያችሁ ንጉሥ ራሴን ይቀጣኛል አላቸው፤ በእነርሱ ላይ የተሾመ አሚሳድን እንዲህ አሉት እኛን ባሮችህን ዐሥር ቀን ፈትነን ከምድር ዘር ሽምብራን ይስጡን እንበላ ዘንድ ውኃንም እንጠጣ ዘንድ፤ ቃላቸውንም ሰምቶ ዐሥር ቀን ፈተናቸው ዐሥር ቀንም ከአለፈ በኋላ የንጉሡን ማዕድ ከሚመገቡ ከእነዚያ ልጆች ይልቅ ሰውነታቸው ወፍሮ መልካቸውም አምሮ ታየ።

❖ ከዚህ በኋላ አሚሳድ የሚበሉትን ምግብ የሚጠጡትን ወይን እየወሰደ ለአራቱ ሁሉ ልጆች ሽምብራ ይሰጣቸው ነበር፤ እግዚአብሔርም ዕውቀትንና ጥበብን መጻሕፍትን በማንበብ ሁሉ ማስተዋልን ሰጣቸው፤ ከዚህ በኋላ ንጉሥ ያዘዘው ቀን በተፈጸመ ጊዜ ወደርሱ አመጡአቸው የባለሟሎችም አለቃ ወደ ንጉሡ ወደ ናቡከደነፆር አገባቸው።

❖ ንጉሡም ጠየቃቸው በሰው ሁሉ ዘንድ እንደ አናንያና እንደ ዳንኤል እንደ ሚሳኤልና እንደ አዛርያ ያለ አልተገኘም በንጉሡም ፊት ቆሙ፤ ንጉሡም የፈለገውን የምክርና የጥበብን ነገር ሁሉ በግዛቱ ካሉ ጠንቋዮችና አስማተኞች ሰዎች ሁሉ ይልቅ በነሳቸው ዘንድ ዐሥር እጥፍ አገኘ፤ ንጉሡም እጅግ ወደዳቸው በባቢሎን አገር ሁሉ ላይ ገዢዎች አድርጎ ሾማቸው።

❖ ንጉሥም ጣዖትን ከወርቅ ባሠራ ጊዜ ሰዎችን ሁሉ እንዲሰግዱለት አዘዛቸው፤ ሦስቱ ልጆችም ለዚያ ጣዖት ባልሰገዱ ጊዜ የሚቀኑባቸው ወደ ንጉሥ ነገር ሠርተው በንጉሥ ፊት አቀረቧቸው ስለ አልሰገዱለትም ጠየቃቸው እነርሱም እኛስ ለሠራኸው ለወርቅ ምስል አንሰግድም አሉት፤ ንጉሥም ተቆጥቶ ከምትነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ።

❖ እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ የእሳቱን ነበልባል አጠፋው በጥዋት ጊዜ እንደሚቀዘቅዝ በእሊህ በሦስቱ ልጆች ዘንድ እንደ ጥዋት ውኃ ቀዝቃዛ አደረገው፤ ከዚያም የእሳቱ ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ከፍ ከፍ ብሎ በውጪ ያሉትን አቃጠላቸው እሊህን ሠለስቱ ደቂቅን ግን ምንም አልነካቸውም፤ ይህን ድንቅ ሥራ አይቶ በፊታቸው ሰገደ የሰማይና የምድር ፈጣሪ እግዚአብሔርንም አመነ ለእሊህም ልጆች ሹመታቸውን ከፍ ከፍ አድርጎ ክብርን ጨመረላቸው።
❖ ከዚህም ዓለም የሚወጡበት ጊዜ ሲደርስ በበዐታቸው እየጸለዩ ሳሉ ሰግደው ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ፤ ወዲያውኑ ታላቅ ንውጽውጽታ በባቢሎን አገር ሆነ፤ ንጉሡም ፈርቶ ስለ ምን ይህ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ብሎ ዳንኤልን ጠየቀው ነቢይ ዳንኤልም ይህ ሦስቱ ልጆች ስለ አረፉ ከዓለም ለመውጣታቸው ምልክት ነው ብሎ ነገረው።
❖ ንጉሡም ወደርሳቸው ደርሶ ታላቅ ኀዘንን አዘነ ከዝሆን ጥርስም ሦስት ሣጥኖችን እንዲሠሩላቸው በሐር በግምጃ ልብሶች ገንዘው ቅዱሳኑን በሣጥኑ ውስጥ እንዲያኖሩአቸው አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዛቸውም አደረጉ፤ ሁለተኛም የወርቅ ሣጥን ሠርተው እርሱ በሚሞት ጊዜ ሥጋውን በውስጡ አድርገው በከበሩ ሠለስቱ ደቂቅ መካከል እንዲያኖሩት አዘዘ እንዲሁም አደረጉለት።

❖ ከዚህ በኋላ የከበረ አባት አባ ቴዎፍሎስ በእስክንድርያ ሊቀ ጵጵስና በተሾመበት ወራት በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ሠራ ሥጋቸውን ወደዚያች ቤተ ክርስቲያን ሊያመጣ ወዶ ሥጋቸውን እንዲያመጣለት አባ ዮሐንስ ሐፂርን ወደ እርሳቸው ሀገረ ባቢሎን ላከው፤ ወደ ባቢሎን ሀገርም በደረሰ ጊዜ ወንዞቿን አየ በውስጧ ከቶ ሰው አልነበረም የወርቁ ምስልም በዚያ አለ፤ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም የቅዱሳን ሥጋ ወደአለበት አደረሰው የንጉሡም ሥጋ በመካከላቸው ነበረ፤ ሥጋቸው በአለበትም ቦታ ሰገደ፤ እንዲህም ብሎ በማልቀስ ጸለየ የከበራችሁ አባቶቼ ሆይ የከበረ አባት ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ በስማችሁ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ሥጋችሁን በውስጧ ሊያኖር እኔን ልኮኛልና ከእኔ ጋራ ትሔዱ ዘንድ ፈቃዳችሁ ይሁን።

❖ በዚያን ጊዜ እንዲህ የሚል ቃል ከሥጋቸው ወጣ ለሃይማኖት አባት ለአባ ቴዎፍሎስ እንዲህ በለው የድካምህን ዋጋ እግዚአብሔር ይስጥህ ነገር ግን እኛን እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ሥጋዎቻችን ከንጉሡ ሥጋ እንዳይለዩ እግዚአብሔር ስለአዘዘን ከዚህ አንወጣም ድካሙንም ከንቱ አናደርግም፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ በምትከብርበት ዕለት በሌሊት መብራቶችን ይሰቅሉ ዘንድ እንዲአዝ በውስጣቸውም ዘይትና ፈትል እንዲያደርጉ በእሳት ግን አይለኩሱአቸው፤ እኛም ከዚያ ደርሰን በእኛ የእግዚአብሔር ኃይል በዚያ ይገለጣል ብለህ ንገረው አሉት።

❖ አባ ዮሐንስ ሐፂርም ተመልሶ እንደነገሩት እንዴትም እንዳዘዙት ሁሉንም ለአባ ቴዎፍሎስ ነገረው እርሱም ሠለስቱ ደቂቅ እንዳዘዙ አደረገ፤ በዚችም በግንቦት ወር በዐሥር ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱ በምትከብርበት ሌሊት የከበሩ ሠለስቱ ደቂቅ ተገለጡ ያለ እሳትም መብራቶችን አበሩ ሊቀ ጳጳሳቱና ለዚህ ጸጋ የታደሉ ሁሉ በቤተ ክርስቲያኒቱ እርከን ላይ ሲዞሩ ሠለስቱ ደቂቅን አዩአቸው በየአይነቱ በሆነ ደዌ የታመሙ ብዙ በሽተኞችም ከቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ መገለጥ የተነሣ ያን ጊዜ ተፈወሱ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

🛎 በዚችም ቀን አብርሃም ፀራቢ በሰማዕትነት አረፈ ይህም ቅዱስ የሰማዕት ቴዎድሮስ ገዳም ተብላ ከምትጠራ ከመርቅያስ አገር ሰዎች ነው፤ ወላጅ እናቱም የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን ሃይማኖት እንዲማር ለመምህር ሰጠችው፤ ጌታችንም ዐይነ ልቡናውን ገልጦለት ትምህርቱን ሁሉ የቤተ ክርስቲያንንም ሕግ ተማረ።

❖ ከዚህም በኋላ መጾም መጸለይና መስገድ ጀመረ ዘጠኝ ዓመትም በሆነው ጊዜ ከደንጊያ የሚሠራ የውኃ መሔጃ መጥረብን ተማረ በዚህም ብዙ ገንዘብ አከማቸ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች የሚመጸውት ሆነ፤ በአንዲት ዕለትም በሌሊት ሲጸልይ የዚችን ዓለምና በውስጧ ያለው ሁሉ ኃላፊ መሆኑን አሰበ፤ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ ስም ምስክር ሆኖ መሞትን ወደደ።

tgoop.com/HISCULHEROFETHIOPIA/5734
Create:
Last Update:

BY ኢትዮጵያ

Share with your friend now:
tgoop.com/HISCULHEROFETHIOPIA/5734

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Step-by-step tutorial on desktop: More>> Polls The visual aspect of channels is very critical. In fact, design is the first thing that a potential subscriber pays attention to, even though unconsciously. End-to-end encryption is an important feature in messaging, as it's the first step in protecting users from surveillance.
from us

Telegram ኢትዮጵያ
FROM American