tgoop.com/HAKiKA1/1477
Create:
Last Update:
Last Update:
ትውስታ አይለቀኝም። ለእያንዳንዱ ትውስታ ደግሞ ታሪክ ነውና ዋጋ እሰጣለሁ። ዋጋ ያለውን ነገር ዋጋ ስሰጥ ደግሞ እንደዛ የሆነልኝን ሰው ስወድ ከልቤ ነው። መወደድ ደግሞ አንዳንዴ ለተወዳጁ ሰው አጉል ኩራትን ይሰጣል። አጉል ኩራት ንቀት ናት። ንቀት ደሞ የትዕቢት እናት ናት። ትዕቢት ሰይጣናዊ ነው ፍቅርን አያሳይህም። ፍቅር ከተከለለብህ ደሞ ወዳጅህ የሚታይህ ላንተ ጥቅም አልባ ሆኖ ነው። ወዳጅህን "ዞር በልልኝ" ትለዋለህ። "ለምን ምን አጠፋሁ?" ይልሀል። ምክንያት መስጠት ሲያቅትህ ትናደድና የባሰ ትጠላዋለህ "በቃ ከመንገዴ ዞር በል" መልስህ ይሆናል። ተገርሞ/አዝኖ/ተናዶ ዞር ይልልሀል። ደግ ወዳጅንና/ደግ ባልንጀራን ማጥበቅ በፈጣሪ የተወደደ ሆኖ ሳለ፤ ሰይጣናዊ አስተሳሰቦች በአይምሮዋችን ሲንከላወሱ ፍቅርንም ወዳጅንም ያሳጡናል። "ሰውን መውደድ ስህተት እንደሆነ" ውስጥህ ከነገረህ...ያውልህ ሰይጣን በግራህ በኩል እየተደሰተ፤ ፈጣሪ በቀኝ በኩል በእዝነት እየተመለከተህ ...
#ሰው_ሲወዱት_ያብዳል
Abrham F. Yekedas
@HAKiKA1
BY አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

Share with your friend now:
tgoop.com/HAKiKA1/1477