tgoop.com/EthiopianReporterAmharic/5678
Last Update:
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የውጭ ድጋፍ ሲያገኙ በ15 ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቁ የሚያስገድድ አዋጅ ተዘጋጀ
#Ethiopia:
ባለሥልጣኑ ያገደው ድርጅት ወደ ፍርድ ቤት መሄድ አይችልም
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከውጭ ወይም አገር ውስጥ ከሚገኝ የውጭ አካል የፋይናንስ ድጋፍ ሲያገኙ፣ በ15 ቀናት ውስጥ ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እንዲያሳውቁ የሚያስገድድ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጀ፡፡
በሥራ ላይ በሚገኘው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 የታዩ ክፍተቶችን ለማስተካከልና ዘርፉን ይበልጥ ለማጠናከር፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ እንዲሁም የድርጅቶቹ እንቅስቃሴ የሕዝብንና የአገርን ጥቅም ያረጋገጠ እንዲሆን ለማድረግ ተብሎ ማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡
የማሻሻያ አዋጁ ድርጅቶቹ ዓላማቸውን ለማሳካት ከየትኛው ሕጋዊ አካል ገንዘብ የመጠየቅ፣ የመቀበልና የመጠቀም መብት እንዳላቸው ገልጾ፣ ከውጭ አገር ወይም በአገር ውስጥ ከሚገኝ የውጭ አካል የፋይናንስ ድጋፍ ሲያገኙ ግን ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ደንግጓል፡፡ በዚህም ድጋፉን ካገኙበ...
ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/142766/
----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ https://bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ https://bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ https://bit.ly/3Ruxsyv
የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
BY ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)
Share with your friend now:
tgoop.com/EthiopianReporterAmharic/5678