tgoop.com/Enatachn_mareyam/18405
Last Update:
†
🕊 💖 ዼጥሮስ ወዻውሎስ 💖 🕊
🕊
[ እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ዼጥሮስ ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ]
❝ ስማቸው ጴጥሮስና እንድርያስ ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ፣ ፊልጶስና በርተሎሜዎስ ፣ ቶማስና ማቴዎስ ፣ ታዴዎስና ናትናኤል ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ማትያን በመባል ለሚጠሩ ለ ፲፪ ቱ የመድኅን ሐዋርያት ሰላምታ ይገባል። ❞
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
❝ አቤቱ በስምኽ የሰበኩ ፤ በታላቅ መከራ በረኀብና በጥም ፤ በብርድና በመራቆት ፤ በመውዛትና በመድከም ፤ ከነገሥታትና ከመኳንንት ዘንድ ተፈርዶባቸው መከራን በመቀበል በምድር ኹሉ ውስጥ የቃልኽን መዝገብ ስለዘሩ ስለነዚኽ ደቀ መዛሙርትኽ ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ ፤ በእሳት በመከራ የተቀበለ አለ ፤ በጦርም የተወጋ አለ ፤ በሰይፍም የተቆረጠ አለ ፤ በመንኰራኲርም የተፈጨ አለ ፤ በደንጊያም የተወገረ ፤ በበትርም የተቀጠቀጠ አለ ፤ ስለነርሱ ብለኽ ማረኝ አስበኝም ፤ ስለሥቃያቸው ስለመቸገራቸውና ስለደማቸው ብለኽ የእኔን የአገልጋይኽን የዕዳ መጽሐፌን ቅደድ ፤ አሜን። ❞
[ ተአምኆ ቅዱሳን ]
ሕዝብ ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡራን አዕማደ ቤተክርስቲያን ፣
ሰመየ ስሞሙ ደቂቀ ብርሃን ጴጥሮስ ወጳውሎስ።
† 🕊 እንኳን አደረሰን 🕊 †
🕊 💖 🕊
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/18405