tgoop.com/Enatachn_mareyam/18100
Last Update:
†
† 🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊 †
[ ክፍል ሠላሳ ስምንት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
❝ ስንወድቅ አጋንንት ፈጥነው ያጠቁናል ፣ ተገቢ ባይሆንም ቅሉ ተገቢ እንደ ሆነ በማስመሰል የተባሕትዎ ሕይወትን ይዘን እንኖር ዘንድ ያሳስቡናል፡፡ የጠላቶቻችን ዓላማ በውድቀታችን ላይ ቍስልን ለመጨመር ነው፡፡
ያለ ሐኪም የተፈወሱ ጥቂት ናቸውና ሐኪሙ ይረዳህ ዘንድ ችሎታ እንደ ሌለው ሲነግርህ ፣ ቀጥሎ ወደ ሌላው ዘንድ መሄድ ይገባሃል፡፡ እንግዲያውስ ማንኛውም መርከብ የሰለጠነ ነጂው አብሮ ሳለ የስጥመት አደጋ የሚያጋጥመው ከሆነ ነጂው [ ቋትለኛው ] ሳይኖር ሲቀር ፈጽሞ ይጠፋል ብለን ስንናገር ከእኛ ጋር በመቃረን የሚያስብ ማን ነው?
ከመታዘዝ ትሕትና ይገኛል ፣ ከትሕትናም መቲረ ፈቃድ [ ፈቃድን መተው ] ይገኛል ፤ ስለ ትሕትናችን ብሎ ጌታ የሚያስበንና ከጠላቶቻችን የሚያድነን ነውና፡፡ [ መዝ.፻፴፭ ፥፳፫ ] ስለዚህ ከመታዘዝ ፈቃድን መተው ይገኛል ብለን መናገርን የሚከለክለን የለም ፣ በዚህ የተነሣ የትሕትና ግብ ተገኝቶአልና ነው፡፡ ሙሴ የሕግ መጀመሪያ እንደ ሆነ ሁሉ ትሕትናም የመቲረ ፈቃድ መጀመሪያ ነው ፤ ማርያም ምኩራብን ፍጹም [ የተሟላ ] እንዳደረገች ሴት ልጅም እናቷን ፍጹም [ የተሟላ ] ታደርጋለች፡፡ ❞
[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]
🕊 💖 🕊
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/18100