tgoop.com/Enatachn_mareyam/18087
Last Update:
🕊 † 🕊
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ስለእኛ ይህን ሁሉ ገንዘብ አደረገ ! ]
🕊 💖 🕊
❝ እግዚአብሔር አብን በመልክ የሚመስለው በባሕርይ የሚተካከለው እርሱ ቀምቶ እግዚአብሔር የሆነ አይደለም ራሱን አዋርዶ የተገዢ [ የአዳምን ] ባሕርይን ገንዘብ አደረገ እንጂ ተብሎ እንደ ተጻፈ። [ ፊልጵ.፪፥፮ ና ፯ ]
መለኮትስ እንደ ሰው በድንግል ማሕፀን ያለ የዕለት ፅንስ መሆን በድንግል ማሕፀን ሳለ በሰማይም በምድርም ምሉ ነው ፤ ለፅንሱ ወራት ዘጠኝ ወር እስኪፈጸም ድረስ እንደ ሰው ሁሉ በየጥቂቱ አደገ። [ ሉቃ.፪፥፬፯ ]
ከዚህ በኋላም የእግዚአብሔርን ቃል ከእርስዋ በነሳው ሥጋ ወለደችው ፤ በጨርቅ ጠቅልላ በበረት አስተኛችው ፤ ፍጹም መለኮቱ የሰውን ሥጋ ተዋሐደ ተብሎ እንደ ተጻፈ ፤ ሰው ሆኖ ሠላሳ ዘመን እስኪመላ ድረስ በአካል ፥ በጥበብ ፤ በሕዋሳት መጽናት በየጥቂቱ አደገ። [ ሉቃ.፪፥፶፪ ። ቆላ.፪፥፱ ]
በየጥቂቱ ያደገ መለኮት አይደለም በሰማይም በምድርም ምሉእ ነውና ፤ በሁሉ በሰማይም በምድርም የመላው እንዴት ያድጋል ?! ከተዋሐደው ሥጋ ጋር አንድ አካል ፤ አንድ ባሕርይ ነውና በየጥቂቱ ማደግን ገንዘብ አደረገ እንጂ። [ መዝ.፻፫ [፻፪)፥፳፪ ። ኢሳ.፷፮፥፩ ። ግብ.ሐዋ.፲፯፥፵፱ ]
ከኃጢአት ብቻ በቀር እንደ እኛ በሥራው ሁሉ ተፈተነ ፤ ተራበ :ተጠማ : ደከመ : አንቀላፋ : በላ ጠጣ : አለቀሰ : ተከዘ : አዘነ : ታመመ : ሞተ : ተገነዘ : በመቃብርም ተቀበረ። እግዚአብሔር ቃል በተዋሐደው በሥጋ ስለእኛ ይህን ሁሉ ገንዘብ አደረገ ። ❞
[ 🕊 ቅዱስ ቄርሎስ 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
BY አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
Share with your friend now:
tgoop.com/Enatachn_mareyam/18087